ETHIO12.COM

የአማራ ክልልን የትጥቅ ትግል የሚመሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ” ኢትዮጵያ የአማራ ብቻ ናት” ማለታቸው ቁጣን አስነሳ

” ኢትዮጵያን ባህሏን ቋንቋዋን መንግሥቷን ዕምነቷን የቀረፅነው እኛ አማሮች ነን”

ሻለቃው ” ኢትዮጵያ የአማራ ናት” ሲሉ ይደጋግማሉ። አክለውም ” ኢትዮጵያን የገለጽናት ‘Define’ ያደረግናት እኛ ነን” በማለት አማራ ብቸኛ የኢትዮጵያ ባለቤት የሆነበትን መጠን ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ የምትባለዋን አገር ለዓለም ያስተዋወቀው አማራ መሆኑን ሲገልጹ ” የሸበረቀውን ባህላችንን ለዓለም ያስተዋወቅነው እኛ ነን” ብለው ነው። በዚሁ ንግግራቸው ታዲያ ሌሎች ” የኢትዮጵያ ልጆች ነን” የሚሉትን ሁሉ ስፍራ እንደሌላቸው መግለጻቸው አንድ ላይ ተዳምሮ ቅሬታና ቁጣ እያስነሳ ነው።

ሰማኒያዎቹን እያዘለሉ ያሉት አዛውንቱ የቀድሞ መኮንና የዕርዳታ ኮሚሽነር ከረሃብተኛ ጉሮሮ ዘፈው አገር መክዳታቸውን የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች በወቅቱ በማስረጃ እንደዘገቡ ይታወሳል። የኢትዮጵያን መከላከያ በማፍረስና መሪ አልባ በማድረግ ከሻዕቢያ ጋር መስጥረው ክህደት እንደፈጸሙም በማስረጃ ይከሰሳሉ። እሳቸውም አንዳንዶቹን ክስ ሳያስቡት ማመናቸው አይዘነጋም። ከተደበቁበት ወጥተው ለኢሳቱ ሲሳይ አጌና ቃላቸውን ሲሰጡ እንደ ዛሬው “የነጻነት ታጋይ” እንደሚሆኑ አስበው አልነበረምና በግንቦት ስምንቱ የኢትዮጵያ ምርጥ ጀነራሎችና መኮንኖች የበላውና እንዲከሽፍ ተደርጎ በተወጠነው መፈንቅለ መንግስት ውስጥ ሱዳን ድረስ በመሄድ ግንኙነት ያደርጉ እንደነበር፤ መጨረሻ ላይም ወታደር ማቅረብ ሲገባቸው ሳያቀርቡ ጀነራሎቹ ስብሰባ ላይ እያሉ ተከበው እንዲያልቁ ምክንያት ተደርገው የሚከሰሱት ጀነራል “ሸሽተው” ከአገር ሲወጡ እንዳገኟቸው በጀብድ ገልጸው ነበር። ጠያቂና መርማሪ ያጣው የዲያስፖራ መናጆ በስካር አገሩን ዳግም እንዲህ ላሉ ከሃጂ ለመስጠት አቅሉን ስቶ ኪሱን ሲገለብጥ ማየት የበርካቶችን ስሜት የጎዳ ሆኗል።


ሴረኛው የስልጣን ጥመኛ! By Solomon Gadissa

ማታ ማታ ከሻዕብያ ጋር ያለውን ግኑኙነት ከበርካታ ሀገር ወዳድ መኮንኖች ሪፖርት ደርሷቸው ነበርና ጉዳዩን ለውይይት አቀረቡት። ሆኖም ከተስፋዬ ገብረ ኪዳን ጀምሮ የደንነት ሚኒስቴሩ ተስፋዬ ወልደ ስላሴ ሌሎችም ከጄኔራሉ ጋር ቅራኔ ስላላቸው ነው በሚል አድበሰበሱት።


ዳዊት ወልደጊዮርጊስ – የጸረ ኢትዮጵያዊነት መገለጫ

ወታደርነቱን ሳይገፋበት የኤርትራ አስተዳዳሪ፣ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ወዘተ የተለያዩ ሥልጣን ላይ ከቆየ በኋላ ኢትዮጵያን ለምዕራባውያን በሯን ወለል አድርጋ እንድትከፍት የሚያደርጋት ሤራ ዋና ጠንሳሽ ሆነ። ይህንኑ እንዲያመቻች “ወታደሩ” ዳዊት የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ዋና ኮሚሽነር ተደረገ።


ሰሞኑንን “ትግሉን እንመራለን” ከሚሉት ሚዲያዎች መካከል አንዱ በሆነው ላይ ሲናገሩ ኦሮሞ ኢትዮጵያ ላይ ቅንጣት መሬት እንደሌለው በገሃድ አመልክተዋል። ” የኦሮሞና ትግሬ ጎረቤት ሆኖ አማራ በሰላም ሊኖር አይችልም” ሲሉ የሩዋንዳን ምሳሌ አጣቅሰዋል። አማራ ከኦሮሞና ትግሬ ጋር ጎረቤት ሆኖ መኖር እንደማይችል ገልጸው ” ተመልከቺ ሩዋንዳን” ብለው በዛው የተደረገውን የዘር ማጽዳት ጭፍጨፋ አጣቀሱ።

ይህ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ ብቸኛ ባለቤት አማራ ሰለሆነ። እሳቸው እንደሚሉት ሌሎች ምንም አይነት አስተዋጾም ሆነ ተሳትፎ ሊኖራቸው አይገባም። ” በምንፈልገውና በምንፈቅደው” ሲሉ ኢትዮጵያን ዳግም የማዋቀርና የመጠቅለል ዓላማ እንዳላቸው ይፋ አድርገዋል። ይህ ንግግራቸው ነው ” ዳግም ሽርጣም መባልን አልፈቅድም። የአማራ ህዝብ በአደባባይ እነዚህን ሰዎች እንደሚቃወም ማስታወቅ አለበት። ሊወክሉት አይችሉም” የሚል ድምጽ የተሰማው።

ሻለቃ ዳዊት “ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው” ሲሉ ባሰራጩት ጽሁፍ …. ከስልጣን ይልቀቁና አማራ ወይንም ኦሮሞ ያልሆነ ሰው ስልጣኑን ይረከብ። ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ያለው ችግር በአማራና በኦሮሞ መካከል ያለው ፉክክርና በሁሉም ዘርፍ ያለው ሽሚያ ነው።ወደ ሽግግር ሊያመጣን የሚችል መሪ ያስፈልገናል። ሁለተኛ ያለን አማራጭ ደግሞ፤ እሺ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቆዩ የሚባል ከሆነ ሕገ-መንግሥቱ ፈርሶና የኢህአዴግ ፓርላማ ተበትኖ እሳቸው በአዋጅ አሸጋጋሪ ሆነው የሃገሪቱን አጀንዳ ይዘው መሄድ አለባቸው።

አዛውንቱ የስክንድር ነጋ አለቃ ” አገራችንን ለማንም አሳልፈን አንሰጥም” በማለት ከላይ የጠቀሱትን ሌሎችን አገር አልባ የሚያደርግ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ትግሉ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። አማራና ትግሬን ማስወገድ ለአማራ ከስጋት የመላቀቅና የሰላም ዋስትናው እንደሆነ ያመለከቱት የፋኖ ጥምረት መሪ በሰላም ተበትኖ በየክልሉ ለሚኖር የአማራ ህዝብ ስጋት እንደሆኑ ከየአቅጣጫው እየተገለጸ ነው።

በኢትዮጵያ ከ12 ሚሊዮን በላይ የአማራ ተወላጅ የሚባሉ በሰላም ከጎረቤቶቻቸው ጋር እንደሚኖሩ የሚገልጹ ” ሻለቃ ዳዊት ለዚህ ህዝብ ስጋት ናቸው” ብለዋል። አማራ ከሁሉም ወገኖቹ የተዋለደ፣ አብሮ የኖረ፣ በአገረ ምስረታ እንደ ሁሉም ኢትዮያዊ የራሱ ሚና ያለው፤ አገር ወዳድ፣ ደግና ያለውን የሚያካፍል፣ ሰላማዊ ህዝብ መሆኑ እየታወቀ በዚህ መልኩ ጎረቤት አላባ እንዲሆን መመኘት እጅግ አስነዋሪ እንደሆነ በርካቶች ገልጸዋል። የሰሙትን ማመን ያቃታቸው ጥቂት አይደሉም።

ይህ ማስተባበያ ሊቀርበበት የማይችለው የሻለቃው ንግግር ” የአፋርን ህዝብ ሳይሆን ግመሎቹን የናቀ፣ አማራ ሲወረር የተዋደቁና ደማቸውን የከፈሉትን ያሳዘነ የታሪክ ግድፈት፣ የታሪክ ጠባሳ ነው” የሚሉ “ሌሎች ይህን ተከትለው ክፋትን በማሰራጨት ሻለቃው አገር ለማተራመስ የተቀበሉትን አጀንዳ ተጋባራዊ እንዳናደርግ” ሲሉ መክረዋል።

” ሻለቃው አብዷል” ያሉ ” የሚያሳዝነው ቆሻሻ ላይ እንደተከመረ ዝንብ ይህን ዕብድ የሚያዳምጡ ወደ ቀልባቸው ለመመለስ ጊዜ መውሰዳቸው ነው” ሲሉ የሻለቃ ዳዊትን የጀርባ ታሪክ እንዲመረመሩ አሳስበዋል። ይህን ማድረግም ለውሳኔ እንደሚረዳ ገልጸዋል።

ሻለቃ ዳዊት ከለውጡ በፊት ” የኢትዮጵያ አንድነት መሰላል የሆኑት አማራና ኦሮሞ ናቸው” ሲሉ የተድመጡበት ቪዲዮ ከዚሁ ከአሁኑ ቪዲዮ ጋር ተቀላቅሎ ” በአንድ ራስ ሁለት ምላስ” በሚል ርዕስ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ነው። በሌላ ቪዲዮ ደግሞ ” ኢትዮጵያን የመሰረቱዋት አምራና ትግሬ ናቸው” ሲሉ በዚሁ የተቀናበረ መረጃ ላይ ተካቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሻለቃ ዳዊት ላደራጁት ሃይል መሳሪያና ሎጂስቲክ የሚያዘጋጀው አገር እጁን ቢሰበስብ እንደሚሻለው ከመንግስት በኩል ጥብቅ ማስተንቀቂያ መሰጠቱ ታውቋል። አንድ እግሩን አዲስ አበባ በውዳጅነት ስም ተክሎ ኢትዮጵያን የሚያተራምሱ ሃይሎችን የሚያደራጀውና የሚመራው ሃይል እጁን ካልሰበሰበ ኢትዮጵያ ራሷን ለመከላከል ለትገደድ እንደምትችል ተመልክቷል።


Exit mobile version