Site icon ETHIO12.COM

የአገር መከላከያ በወገኖቹ የተከዳበት ቀን ” አይረሳም!” እንዳይደገም ትውልድ ሁሉ ያስበዋል!!

“ሠራዊቱ በወገኖቹ የተካደበትን ቀን ሁሌም እንዳይደገም እንዘክረዋለን” ፦ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

“እንዳይደገም ሁሌም እንዘክረዋለን” በሚል መሪ ቃል ሰሜን ዕዝ የተጠቃበት 3ኛ ዓመት የመታሰቢያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ደንበር እየጠበቀ ሰብል እየሰበሰበ የአንበጣ መንጋን እያባረረ ኮቪድ ወረርሽኝን በመከላከል አሰተዋጽኦ አበርክቶ በድካም ጋደም ባለበት በወገኖቹ ተክዶ ጥቃት የተፈፀመበት እና በኢትዮጵያ ታሪክ ጥቁር ጠባሳ የተመዘገበበት ቀን ነው ብለዋል የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።

በአለም ታሪክ ለግል ስልጣንና ጥቅም ዘርና ወገን ለይተው ራሳቸው ባደራጁት የራስን ጠባቂ እና ጋሻ የሆነ ሠራዊት በጭካኔ በመጨፍጨፍ ሀገርን ያለጠባቂ መስቀረትና መንግስትን ለመጣል ሙከራ የተደረገበት ለኢትዮጵያ መከራ ጥሎ ያለፈ ቀን መሆኑን ያነሱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ መከላከያ ሠራዊቱ በትግራይ ክልል ትሞህርት ቤቶችን እየገነባ የጤና ኬላ እየሠራ እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን እያስፋፋ አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች አስተምሮ ለቁም ነገር ሲያበቃ ቆይቷልም ብለዋል።

ህዝቡ ከሠራዊቱ ጋር ተዛምዶ ተዋልዶና ቤተሰብ ሆኖ በኖረበት ክልል በፀንፈኛ ፖለቲከሀኞች ምክንያት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በሠራዊታችን ላይ መፈፀሙን ጠቁመው ቀኑ ዛሬም ነገም ሁሌም ይዘከራል መላው ኢትዮጵያዊም ይህ ድርጊት እንዳይደገም መዘከር ሠላም እንዲመጣ ማስታወስ ይገባዋል ብለዋል ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ።

መከላከያ ጦርነቱ እንዳይካሄድ ያደረገው ጥረት ዋጋ ከማስከፈሉም በላይ የትግራይ ህዝብ ወገናችን ስለሆነ ሠራዊቱ ግዳጅ እንዳይወጣ አግደንም ነበር ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ሴራ ሀገሪቱ እና መላው ህዝብ ለችግር ተዳርገዋል ይህን ለመቀልበስ መከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ መሆኑንም ተናግረዋል።

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጦርነቱ በሁሉም ወገኖቻችን ላይ ያደረሰው ጉዳት የኢትዮጵያ ጉዳትና መከራ በመሆኑ ከዚህ ታሪክ መላው ኢትዮጵያዊ ተምሮ እንዳይደገም መዘከር ይገባዋል ካሉ በኋላ ሁሉም ህዝብ ለሠላም መሥራት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዕለቱን በተመለከተ በጀኔራል መኮንኖች የፓናል ዉይይት የተካሄደ ሲሆን የፓናል ዉይይት መድረክን የመሩት በኬንያ ባለሙሉ ስልጣን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ በበኩላቸው ጥቅምት 24 ቀንን መዘከር ትልቅ ትርጉም አለው የተፈጠረው ነገር ከልባችን ተፀፅተን ለሠላም በህብረት ልንተጋገዝ ይገባል ብለዋል።

የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት አባላት በወገናቸው ጭካኔና ግፍ በተሞላበት ሁኔታ የተካዱበት 3ኛ ዓመት መታሰቢያ መርሃ ግብር በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጄኔራል መኮንኖች ከፍተኛ መኮንኖች የሠራዊት አባላትና ከሲቪል መህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ ውሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም


Exit mobile version