Site icon ETHIO12.COM

በኢትዮጵያ የኢሳያስ አፉወርቂ ዲፕሎማት በባህር ዳር “ቅርንጫፍ ቢሮ ” ነበራቸው?

ከሰላሳ ዓመት በላይ ኤርትራን በብቸኝነት የመሩት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ፣ በአዲስ አበባ የመደቧቸው ዲፕሎማት ከኤምባሲያቸው በተጨማሪ በባህር ዳር ቅርንጫፍ ቢሮ አንደነበራቸውና ይህም በኢትዮጵያ ልዩ እንደሚያደርጋቸው በሌላ ሃላፊነት አብሮ ሲሰራ የነበረ የመዋቅር ሰው አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ቢያውቅም በጥድፊያ እርምጃ መውሰድ የማይችልበት ደረጃ ላይ እንደነበርም አመልክቷል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ በተኙበት በድንገት የተፈጸመውን የክህደት ጥቃት ተከትሎ ኢትዮጵያ ላይ እንዳሻው የተመላለሰውና ከፍተኛ ዝርፊያ የፈጸመው ሻዕቢያ አዲስ አበባ ድረስ የስለላና የውትድርና ባለሙያዎችን በይፋ አስገብቶ እንደነበር በስፋት ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል።

በዚሁ አግባብ አዲስ አበባ ቆይቶ አሁን በስደት ወደ ሌላ አገር የተሻገረ የመዋቅር አባል እንዳለው ከሆነ የኤርትራው ዲፕሎማት ለጉዳያቸው ከሚያመቿቸው ጋር በመሆን ባህር ዳር በተደጋጋሚ ይመላለሱ እንደነበር አስረድቷል። ” ቅርንጫፍ ቢሮ አላቸው ?” የሚል ጥያቄ በሚያስነሳ ደረጃ ባህር ዳርን የውሃ መንገድ አድርገውት እንደነበር ያስታወቀው የመረጃው ሰው፣ መንግስት ራሱን ካደራጀ በሁዋላ ከድህነትና ከቁልፍ የጸጥታ ተቋማት የኤርትራን ሃይሎች ማጽዳቱና እንዲመለሱ ማድረጉ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል።

“ከሚመለሱት መካከል አንዱ ነበርኩ። ግን እድሜ ለቤተሰቦቼ የሚችሉትን አድርገው አስወጡኝ” ሲል ዛሬ በስደት ሌላ አገር ነደሆነ ያስረዳው ጥቆማ ሰጪ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ላይ ለማቄምና በዚህ ደረጃ ለመጉዳት የተነሳሱበት ምክንያት እንደማይገባው አመልክቷል።

በግምት ከስድስት ወር በፊት የኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች አዲስ አበባ ለንግግር መጥተው እንደነበር አስታውሶ፣ ያ የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ከጦርነቱ ጎን ለጎን ሰፊ ሃይል ማደራጀቱ፣ ስለላውንና ጥቅል የጸጥታ ተቋማቱን በዝመናዊ ደረጃ በማደራጀቱ እንደቀድሞው ነገሮችን በዝምታ ባለማለፉ እንደሆነ ጠቁሟል።

በትክክል ንግግሩ ምን እንደሆነ መናገር ባይችልም ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ወገን አዲስ አበባ የነበሩ የኤርትራ የመዋቅር ሰዎችና መኮንኖች “በቃችሁ ሂዱ” መባሉ ቅሬታ በመፍተሩ እንደሆነ መረጃ እንዳለው ገልጿል። አሁን ላይ ምን አልባት ለኤትዮጵያ መንግስት ለመስራት ተስማምተው በሙሉ ለሙሉ ቅጥር የቀሩ ካልሆኑ በቀር በኢትዮጵያ የጸጥታ ተቋማት ውስጥ የኢሳያስ አፉወርቂ መዋቅር ሰዎች ሙሉ በሙሉ መጽዳታቸውን አመልክቷል። ለመመልስ ፈቃደኛ ያልሆኑ በስደት የተመዘገቡ እንዳሉም ጠቁሟል።

ከአዲስ አበባ ሊወጣ ሳምንት ሲቀረው መንግስት የኤርትራን አምባሳደር እጃቸውንማ እግራቸውንም እንዲሰበስቡ እንዳስጠነቀቃቸው እንደሚያውቅ አመልክቷል። በአዲስ አበባና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች አንድ ሚሊዮን የሚልቁ የኤርትራ ተወላጆች እንደሚኖሩ ግምቱን ተቅሶ የገለጸው የዜናው ምንጭ ” በአገሩ በሰላም መኖር ያልቻለውን ህዝብ ከአገሩ ውጪም በሰላም እንዳይኖር ጦስ እንዳይሆኑበት እፈራለሁ” ሲል ስጋቱን ገልጿል።

ባህር ዳር ሲመላለሱ የነበሩት ዲፕሎማትና ሌሎች የመዋቅር ሰዎች ማንን ያገኙ እንደነበር ለተጠየቀው ” እለፈኝ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ኤርትራ በይፋ የአማራ ሃይሎችን እንደምትደግፍ በማስታወቂያ ሚኒስትር ሃላፊዋ አማካይነት ማስታወቋ አይዘነጋም። ወቅቱ ትህነግ አማራ ክልልን ወሮ ጥቃት የሚፈጽመበት ስለነበር ጉዳዩን መንዝሮ ያያው አካል አለነበረም።

በ1983 ከትህነግ ጋር ሆኖ አዲስ አበባ የገባው ሻዕቢያ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ጠብመንጃ ካወረደ በሁዋል በኤርትራ በረሃ በጅምላ መረሸኑ በስፍራው የነበሩ መናገራቸው አይዘነጋም። አዲስ አበባ ከገባም በሁዋላ ከትህነግ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን የመከላከያ ሃይል “የደርግ ሰራዊት” በሚል እንዲበተኑ ሚና ተጫውቷል። የመከላከያ ተቋሞቿም እንዲዘጉና እንዲከስሙ ድርሻውን እንደተወጣ በገሃድ የታየ ሃቅ ነው።

ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ግዙፍ ሃይል መገንባቷ፣ የባህርና የአየር ሃይሏን ዳግም አደራጅታ ማብቃቷ፣ በተለይም አዲሱ የአገር መከላከያና የድህነት ተቋማቱ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፉ መሆናቸው ስጋት የገባው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አስተዳደር ኢትዮጵያ ከጦርነት ሳታገገም ወደ ዳግም ጦርነት እንድትሸጋገር የሚችላእውን ሁሉ እያደረገ እንደሆነ መረጃዎች ያመልክታሉ። ማስረጃዎችም አሉ።

ሻዕቢያ እንዴትና በምን መልኩ በገንዘብ አጠባ ተግባር እንደተዘፈቀ ያወጋው የዜናው ሰው በዚሁ ጉዳይ ላይ ሰፊ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ቃል ግብቷል። ሲያልቅ ይዘን እንቀርባለን።

ሻዕቢያ ትህነግን፣ ኤርትራ ተቀሞ አምስት ቦታ የተከፋፈለውን ኦነግን፣ አርበኞች ግንባርን፣ ግንቦት ሰባትን፣ የትግራይ ተቃዋሚ ድርጅት ደህሚትን አሁን ደግሞ እየታየ ያለውን ንቅናቄ በስንቅና ትጥቅ አሰባሳቢነትና በአስለጣኝነት ዝመኑንን ሁሉ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የማይታክት በመሆኑ መላ ሊባል ይገባዋል የሚሉ እየበዙ ነው።

Exit mobile version