ETHIO12.COM

የኢትዮጵያአየር ሃይል ዘመናዊ የsu-30 ተዋጊ ጀቶችንና የስትራቴጂክ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ታጠቀ

ባለፉት አምስት ዓመታት በልዩ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶት ዳግም ከባዶ እየተገነባ ያለው አየር ሃይል የኢትዮጵያአየር ሃይል ዘመናዊ የsu-30 ተዋጊ ጀቶችንና የስትራቴጂክ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖችን መታጠቁን አስታወቀ። ”የኢትዮጵያን አየር ክልል ከማንኛውም ጥቃት የሚከላከሉ ዘመናዊ የውጊያ ትጥቆችን መታጠቃችን ይቀጥላል” ሲሉ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናገረዋል።

የመከላከያ ሃይሏን በስፋትና በጥልቀት እየገነባች ያለችው ኢትዮጵያ የፈረሰውን የባህር ሃይል ዳግም ገንብታ የባህር በር ለማግኘት ከሶማሊ ላንድ ጋር ስምምነት ላይ መድረሷን ተከትሎ ይፋ የሆነው የአየር ሃይል ዘመናዊ ትጥቅ ለኢትዮጵያ መከላከያ እመርታ ነው።

የኢትዮጵያን የአየር ክልል ከማንኛውም ጥቃት ሊከላከሉ የሚችሉ ዘመናዊ የውጊያ ትጥቆችን የመታጠቅ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዘመናዊ የሆነውን የመጀመሪያ ዙር የsu-30 ተዋጊ ጀቶችንና የስትራቴጂክ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ታጥቋል።

በዚሁ ርክክብ ላይ የተገኙት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፤ በዓለማችን ላይ ተመራጭ የሆኑትን የsu-30 እና የስትራቴጂክ ሰው አልባ አውሮፕላን ባለቤት መሆናችን በሀገራችን ላይ ሊቃጡ የሚሞከሩ ጥቃቶችን ለማክሸፍ ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የ5ኛ ትውልድ አካል የሆኑት ዘመናዊ ተዋጊ አውሮፕላኖችና የስትራቴጂክ ሰው አልባ አውሮፕላኖች አየር ሀይሉን የማዘመን አንዱ አካል መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ አየር ሀይል በአፍሪካ በውጊያ አቅሙ፣ በጀግንነቱና በትጥቁ የነበረውን ዝና ዘመኑ በሚጠይቀው መልኩ ለማዘመን እየተሰሩት ያሉት ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ዘመን ተሻጋሪ የአየር ሀይል የመገንባት እንቅስቃሴው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው፤ አየር ሀይሉ በሰለጠነ የሰው ሀይል፣ በትጥቅና በውጊያ መሰረተ ልማት መጠናከሩን ጠቁመዋል።

ተቋሙ የተረከባቸው ዘመናዊ የጦር ጀቶች በተመሳሳይ ጊዜ በአየርና በምድር ላይ ያለ የጠላት ኢላማን ማውደም የሚችል መሆኑን በመግለጽ ዘመናዊ የሰው አልባ አውሮፕላኖችም የጠላትን ዒላማ የማይስቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጥቂት ስለ አዳዲሶቹ ጨራሽ ወታደራዊ አኪንሲ

ኢትዮጵያ ይፋ ስላደረገቻቸው እጅግ ዘመናዊ ስለሆኑት ግዙፎቹና አዳዲሶቹ ጨራሽ ወታደራዊ አኪንሲ የቱርክ ድሮኖች ጥቂት መረጃ

ይህ የአለማችን ቁጥር አንድ የሚሊትሪ ድሮን ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የቱርኩ ባይራክታር ካምባፓኒ ውጤት የሆነው በብዙ ቴክኖሎጂ የታጨቀ ድሮን እስካሁን ከኢትዮጵያ ጋር የታጠቀችው ሌላኛዋ የቱርክ ወዳጅ ፓኪስታን ነች።

ድሮኑ 20 ሜትር የክንፍ ርዝመት ፣ 4.1ሜትር ቁመት ፣ 5,500ኪ.ግ ቴክኦፍ ክብደት፣ 8000 ኪሎ ሜትር ያለማቋረጥ መጓዝ የሚችል(ግ*ፅ 3ዙር ደርሶመልስ) ፣ 26 ሰዓት አየር ላይ መቆየት ሚችል ፣ 14 ሺ .ሜትር 45ሺ ጫማ ከፍታ ላይ ሆኖ የፈለገውን ኢላማ ሚመታ፣ የአየር በአየር ውጊያ ማድረግ ፣ ከአየር ወደ ምድር ፣ ኤሌክትሮኒክ ዋርፌር ፣ የረጅም ርቀት የቅኝት ራዳር ፣ የሁለት ሳተላይት ግንኙነት ፣ ወዘተ ዘመኑን የዋጀ የመጨረሻው የወታደራዊ ድሮን ቴክኖሎጂ ነው።

አዲሱ አኪንሲ ድሮኖች ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ከታጠቀችው የአለም ጦርነት ታሪክ ቀያሪ ከሚባሉት ባይራክታር ቲቢ 2ም ጭምር እጅግ የላቁና የበለጠ ቴክኖሎጂ የታጠቁ ሲሆን ሲሆን ፤ ለምሳሌ፦ ቲቢ2 የምትሸከመው የተተኳሽ ሚሳኤልና ቦንቦች አቅም 340 ኪ. ግራም ሲሆን ፤ አዲሱ አኪንሲ ድሮን ግን 1,500 ኪ.ግራም የተለያዩ አይነት ሚሳኤልና ቦምቦችን ተሸክሞ ኢላማዎቹን ጥርግ አርጎ ማውደም ይችላል።

ይህና ሌሎችም በይፋ ለእይታ ያልቀረቡ ነገር ግን የኢፌዴሪ መከላከያ አዳዲስ የታጠቃቸው ትጥቆች ኢትዮጵያን በትክክልም ክብሯን የሚመጥን ሩቅ ተጉዘው ሉዓላዊነቷን የሚያስከብሩ ሆነው ተገኝተዋል።

Exit mobile version