Site icon ETHIO12.COM

የግብጽ ክስ «ቧልት ነው፤ ያለ ፈተና የፀና ሕልውና የለም» የውጭ ገዳይ ሚኒስቴር

ሰሞኑንን የኢትዮጵያ ጉዳይ እጅግ ሰፊ መወያያ ሆኗል። በግብጽ መሪነት፣ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ አስተባባሪነት ዘመቻ የተከፍተበት የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ” ያለፈውን ቁጭትና የወደፊቱን ተስፋ ያገናኘ” ሲሉ ነበር የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የውጭ ጉዳይ አማካሪ ለውጭ አገር ዲፕሎማቶች የገለጹት።

“ቁጭትና ተስፋ” የተጋመዱበት የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት፣ የመግባቢያ ሰነዱ ወደ ተግባር ከመቀየሩ በፊት ዘመቻቸውን እያጋጋሉ ያሉት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚችሉትን ድንጋይ ሳያማርጡ እየፈነቀሉ ነው።

ግብጽ ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪቃ አተራማሽ አድርጋ መግለጫ ማውጣቷን ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር «ቧልት ነው፤ ያለ ፈተና የፀና ሕልውና የለም» ሲል ምላሽ ሰጥቷል። የባህር በር ህልውና መሆኑን አስመረው በጉዳዩ እንደማይደራደሩ ያስታወቁት አምበሳደር መለስ ዓለም ናቸው። የዲደብልዩ ሙሉ ዘገባ ከስር ተቀምጧል።

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና «ያለመረጋጋት ሳይሆን የመረጋጋት መንስኤ ናት» ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ ዛሬ ምላሽ ሰጠ ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ፦ አምበሳደር መለስ ዓለም፦ ግብጽ ኢትዮጵያን የአካባቢው አለመረጋጋት መንስኤ አድርጋ መክሰሷን «ቧልት» ብለውታል።

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና «ያለመረጋጋት ሳይሆን የመረጋጋት መንስኤ ናት» ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ለግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  መግለጫ ዛሬ ምላሽ ሰጠ ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ፦ አምበሳደር መለስ ዓለም፦ ግብጽ ኢትዮጵያን የአካባቢው አለመረጋጋት መንስኤ አድርጋ መክሰሷን «ቧልት» ብለውታል። ኢትዮጵያ ራሷን የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ብላ ከምትጠራው እና ሶማሊያ የግዛቴ አካላ ናት ከምትላት ሶማሊላንድ ጋ የወደብ ጉዳይን በሚመለከት የተፈራረመችው የመግባቢያ ሰነድ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል ። የአረብ ሊግ በዚሁ ጉዳይ የሰጠውን መግለጫም አምባሳደር መለስ፦ «ለአፍሪቃውያን ንቀት» ብለውታል ።  በግብጽና በአረብ ሊግ መካከል ያለውን ግንኙነት «የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ» ሲሉ አክለዋል ። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት (IGAD) በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ አለመሳተፏንም አረጋግጠዋል።  

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ግንኙነት ላይ የተፈጠረ ለውጥ አለ?

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ታኅሣሥ 22 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ለኢትዮጵያ የባሕር በር ፣ ለሶማሊላንድ ከግዙፍ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ድርሻ እንዲሁም እንደ ሀገር ዕውቅና ማግኘት የሚያስችላት የተባለለትን ስምምነት ከተፈራረሙ ጀምሮ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የከረረ ውዝግብ  ተነስቷል።

ብዙ ሀገራት እና ድርጅቶች በጉዳዩ ላይ ባወጧቸው ተከታታይ መግለጫዎች የሶማሊያ ሉዓላዊነት እንዲከበር ሲያሳስቡ የአፍሪቃ ሕብረት የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተስተዋለውን ውጥረት እንዲያረግቡ ጠይቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ሰሞነኛውን ውዝግብ ተከትሎ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለውጥ ስለመኖር አለመኖሩ በጋዜጠኞች ተጠይቀው “የለም” ብለዋል። “የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የንግድ እንዲሁም የአቪየሽን ግንኙነትን በተመለከተ የተለወጠ ነገር የለም” ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ “የአለመረጋጋት መንስኤ አይደለችም ።”

የምስራቅ አፍሪካ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላም፣ ደኅንነት እና መረጋጋት ያገባናል ባዮች በርካቶች ናቸው። በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪዎች ሶማሊያ ውስጥ ለሀገሪቱ መረጋጋት እየሠሩ ይገኛሉ። ሰሞነኛውና ቀጣናውን የበለጠ ዓለም አቀፍ መነጋገሪያ ያደረገው ገዳይ ሀገራቸውን ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ጦርነት ሊያስገባት እንደሚችል የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር መናገራቸው ሥጋቱን አባብሶታል።

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን የአካባቢው አለመረጋጋት መንስኤ አድርገው መፈረጃቸውን ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም አጣጥለውታል። “ኢትዮጵያ ያለመረጋጋት ሳይሆን የመረጋጋት መንስኤ ናት ለዚህ አካባቢ” የአረብ ሊግ በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ካደረገ በኋላየኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድን ስምምነትበዓለም አቀፍ ደረጃ የተቃጣ ጥቃት አድርጎ ወስዶታል። ለዚህ ቀጥተኛ ምላሽ የሰጡት አምባሳደር መለስ አለም “ለአፍሪካዊያን ንቀት ነው” ብለውታል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘትን ጉዳይ አንገብጋቢ የፍትሕ እና የፀጥታ አጀንዳዋ አድርጋ የያዘችው መሆኑንም ቃል ዐቀባዩ አብራርተዋል። “ጉዳዩ የፍትሕም፣ የርትዕም ፣ የልማትም የሰላምም ጉዳይ ስለሆነ ኢትዮጵያ የባሕር በር መዳረሻ ያስፈልጋታል።”

አወዛጋቢው የበርበራ ወደብ፤ ሶማሊላንድ ። ፎቶ ከማኅደርምስል Brian Inganga/AP/picture alliance

ኢትዮጵያ በኢጋድ አስቸኳይ ስብሰባ አልተሳተፈችም

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (IGAD) ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በገቡበት ልዩነት ዙሪያ ዛሬ ለመምከር አባል ሀገራቱን ለአስቸካይ ስብሰባ የጠራ ቢሆንም ኢትዮጵያ አለመሳተፏ ተገልጿል።

ሆኖም ኢጋድ ለኢትዮጵያ በጣም አስፈላጊ ድርጅት በመሆኑ እንዲጠናከር እንደሚሰሩ ፣ የድርጅቱ ጥንካሬ ለኢትዮጵያ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። የኬንያ መንግሥት ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ኢትዮጵያዊያን አዲስ የመግቢያ ፈቃድ እንዲተገበር ከሰሞኑ ወስኗል። የሁለቱ ሀገራት ዜጎች አንዱ ወደሌላው ሲጓዝ የቪዛ ሂደት ቅድመ ሁኔታ አልነበረም። ቃል ዐቀባዩ የዚህ የኬንያ አዲስ ሕግ መነሻ ምክንያት ምን እንደሆነ ባይገልፁም ተነጋግረን መፍትሔ የምንሰጥበት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት መሠረታዊ “የፀጥታ እና የስትራቴጂ ጉዳይ” መሆኑን የጠቀሱት ቃል ዐቀባዩ “ያለ ፈተና የፀና ሕልውና የለም” ሲሉ ኢትዮጵያ ስምምነቱን ተከትሎ የደረሰባትን ጫና ገልፀዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠመው ችግር መነሻ የተፈጠረው ውዝግብ እንዲፈታ ባንኩ ከመንግሥት ጋር ሰፊ ውይይት እያደረገ መሆኑንም በመግልጫቸው አንስተዋል።

Exit mobile version