Site icon ETHIO12.COM

ጌታቸው ረዳ ትህነግ ለስልሳ አራት ቀናት አካሂዶ ያላጠናቀቀውን [ግምገማ] ረብ የለሽ አሉት

በትግራይ ከጦርነት ማግስት የሚወጡ መረጃዎች ህዝብ በከፋ ችግር ላይ እንደሚገኝ የሚያሳዩ ቢሆንም ትህነግ ስልሳ አራት ቀናት አካሂዶ ያላተናቀቀው ግምገማ / ስብሰባ ለህዝብ ጠብ የሚል ነገር የሌለው ረብ የለሽ እንደሆነ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። ድርጅቱ ዘንድሮም “ሂስና ግለሂስ” በሚል ለወራት መሰበሰቡን ገፍቶበታል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ይህን ያሉት ባላፉት ሳምንታት በሽረ እንዳስላሴና በማይጨው ከተሞች በመገኘት ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። ቲክቫህ የትግራይ ዘጋቢዎቹን ጠቅሶ ሲዘግብ ” ላለፉት ሰላሳ ዘተኝ” ቀናት ያካሄድኩትን ሰብሰባ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት አጠናቅቃለሁ ” ሲል የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ አውጥቶ እንደነበር አስታውሷል።

በተጠቀሰው ሰላሳ አራት ቀናት ሳይሆን ስብሰባው ስልሳ አራት ቀን እንደፈጀ በመጥቀስ “ለ64 ቀናት ስብሰባ ተቀምጠን ህዝብን የሚረባ ጠብ ያለ ቁምነገር የለም ” -ሲሉ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ መናገራቸው የውስጥ ልዩነቱ ምን ያህል የከረረ መሆኑንን የሚያሳይ ሆኗል።

ትህነግ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ላለፉት 39 ቀናት ከፀጥታ ሃይሎች ፣ ከተተኩ ነባር አመራርሮች በጥምር ያካሄደውን “ገምገም”፤ ግለሂስና ሂስ በዚህ ሳምንት እንደሚያጠቃልል አስታውቋል።

” የግምገማ ፣ የግለሂስና ሂስ መድረኩ ከሁለት ቀናት በማይበልጥ ጊዜ ይጠናቀቃል ” ያለው መግለጫው ” ቀጥሎ የድርጅቱ ካድሬዎችና አባላት የሚሳተፉትበት ጉባኤ ይካሄዳል ” እንደሚካሄድ አመልክቷል። ስብሰባው ስንት ወር ወይም ሳምንታት እንደሚፈጅ ግን አላስታወቀም።

” የቀጠለው መድረክ ከተጠናቀቀ በኃላ በድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴና ቁጥጥር ኮሚሽን መካከል በተደረሰ ስምምነት መሰረት መላ አመራር ፣ አባላትና ህዝብ የሚሳተፉበት ጉባኤ ይካሄዳል ” ሲልም አሳውቋል። እንደ መግለጫው በትግራይ ገና በርካታ የስብሰባ ዓይነቶች ይደረጋሉ። ሁሉም ሆኖ ግን አሁን ህወሓት ጉባኤው የሚያካሂድበት የተቆረጠ ቀን አልታወቀም።

በግመገማው ወቅት በመረጃ የተደገፈ ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ስለመኖሩ ቀርቦ ከፍተኛ ንትርክ ማስነሳቱን ትህነግ ባወጣው መግለጫ ይፋ አላደረገም። አብዛኞች ስልታዊ የመፈንቀለ ስልጣን አካሄድ ይዘት እንዳለው የሚናገሩለት ይህ ግምገማ መጨረሻውም ይህ እንደሚሆን ግምት ቢኖራቸውም እንደማይሳካ የሚገልጹም አሉ።

ህወሓት ለ39 ቀናት ስብሰባ እንደተቀመጠ ቢገልፅም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ባላፉት ሳምንት በሽረ እንዳስላሴና በማይጨው ከተሞች በመገኘት ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ስብሰባው ለ64 ቀናት መካሄደውንና ለህዝብ የሚረባ ጠብ የሚል ቁምነገር እንዳልተገኘ በማመልከት የትህነግን መግለጫ ስህተት ይፋ አድርገዋል።

የትግራይ ህዝብ ከጦርነቱ ማግስት በከባድ ድርቅና ረሃብ እንዲሁም ጦርነት ወለድ ችግሮች ተተብትቦ እያለ ይህን ያህል ቀናት አመራሮች ሰብሰባ መቀመጣቸውን የሚነቅፉት እጅግ በርካቶች ናቸው ሲል የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ምስክርነቱን ሰጥቷል።

በተረጂዎች ቁጥር ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ምላሽ ሲሰጥ ” ስብሰባ ከማብዛት ወደ ስራ መግባቱ ከወሬና አሉባልታ ይቆጥባል” ሲል መውቀሱ አይዘነጋም።

በግምገማው ከሙስና ጋር በተያያዘ መረጃ የቀረበባቸው በህግ እንዲጠየቁ አቅጣጫ መቀመጡን ከትግራይ ውስጥ አዋቂ መሆናቸውን የሚያውቁ በተለያዩ አውዶች እየገለጹ ነው።


                           

Exit mobile version