Site icon ETHIO12.COM

የቀድሞው የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ኮ/ል ኢብራሂም ሸምሰዲን?

#FakeNewsAlert

ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት እንደወረደ (Endewerede) የተባለ ይህ የፌስቡክ ገጽ የቀድሞው የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ኮ/ል ኢብራሂም ሸምሰዲንን ያሳያሉ ያላቸውን ምስሎች ዛሬ አጋርቷል።

ከፎቶዎቹ ጋር ተያይዞ የቀረበው ጹሁፍ እ.አ.አ በ2001 በአውሮፕላን አደጋ እንደሞቱ የሚነገርላቸው ኮ/ል ኢብራሂም በቀድሞው የሱዳን ፕሬዝደንት ኡመር አልበሽር ትዕዛዝ ከመሬት በታች በሆነ ድብቅ እስር ቤት ሲማቅቁ እንደነበሩ ያትታል።

ኢትዮጵያ ቼክ በሪቨርስ ኤሜጅ ባደረገው ማጣራት ፎቶዎቹ የኮ/ል ኢብራሂም አለመሆናቸውን አረጋግጧል። በፎቶዎቹ ላይ የሚታየው በርሀብ የተጎዳው ግለሰብ ኬኒያዊ ሲሆን ፎቶዎቹ የተነሱት አምና በሰሜን ኬኒያ እና በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች በድርቅ ምክንያት ርሃብ በተከሰተበት ወቅት ነበር።

ፎቶዎቹን ለመጀመሪያ ጊዜ በመጋቢት ወር 2019 ዓ.ም በትዊተር ገጹ ያጋራው የቢቢሲ ጋዜጠኛ የሆነው ሮንክሊፍ ኦዲት ነበር።

Exit mobile version