የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጣኛ የነበረው ዳዊት ከበደ በስም ካልተጠቀሰ ጓደኛው ጋር በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን የጀርመን ድምጽ ዘግቧል። ዘገባው ሙሉ መረጃ ባያቀርብም በመቀለ ባለ ዘጋቢው አማካይነት ማረጋገጫ ሰጥቷል። የትግራይ ተወላጅ የሆኑ አክቲቪስቶች በበኩላቸው ” የትግራይ ተወላጅ የብልጽግና አመራር ቀብራቹህ በቅርብ ገሃድ ይሆናል” የሚል ሃረግ ያለበት ወርቀት የሰዓት እላፊ በመጣስ በተሽከርካሪ ሆነው ሲበትኑ እንደነበር እየገለጹ ነው።
የጀርመን ድምጽ የመቀለ ዘጋቢ አክቲቪስቶቹ የጠቀሱትን ሃሳብ በዜናው አላካተተም። ይሁን እንጂ ” የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የሚያስተዳድረው ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ እና ጓደኛው ትናንት በመቐለ ከተማ በጥይት ተመተው ተገደሉ። ቤተሰቦቻቸው እና የሥራ ባልደረቦቻቸው እንደተናገሩት ዳዊት እና ጓደኛው የተገደሉት የሰዓት ዕላፊ በታወጀባት ከተማ በተሽከርካሪ ሲንቀሳቀሱ ከጸጥታ ኃይሎች በተከተኮሰ ጥይት ነው” ሲል ነው ዜናውን የጀመረው።
መለስ ብስራት የሚባለው አክቲቪስት የሚከተለውን በፌስ ቡክ ገጹ ያሰፈረ ሲሆን ዞባ ተምቤን Tembien Province በበኩሉ ሰፋ ያለ መረጃ አስፍሯል።
“የጀርመን ድምጽ እንዳለው በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ታስረዋል። በመቐለ ከተማ የሰዓት ዕላፊ ታውጇል። ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ያነጋገርኩት ሚሊዮን እንደነገረኝ ኩነቱ የተፈጸመው በከተማው መንቀሳቀስ በተከለከለበት ወቅት ነው። የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከጊዜያዊው አስተዳደር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሚሊዮን ያደረገው ጥረት እንዳልሰመረ በስልክ ነግሮኛል” የጀርመን ድምጽ ዘገባውን ያተቃልላል።
ዞባ ተምቤን Tembien Province ከጀርመን ድምጽ ጋር ተመሳሳይ መረጃ ያቀረበ ሲሆን ልዩነቱ ያለው ከሰዓት እላፊ ተላልፈዋል የተባሉት ሟቾች ምን ሲያደርጉ እንደነበር ማብራራቱ ላይ ነው። ዞባ ተምቤንም ሆነ ጀርመን ሬዲዮ እንዳሉት በመቀለ ሰዓት እላፊ ታውጇል። ከምሽቱ አንድ ሰዓት በሁዋላ የንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። ዳዊትና ጓደኞቹ በምግምት 2:30 አካባቢ በተሽከረካሪ ውስጥ ሆነው ጎዳና ላይ ይነዱ ነበር።
የጀርመን ድምጽ ቤተሰቦች አነጋግሮ በሰዓት እላፊ ምን ይሰሩ እንደነበር አላብራራም። ዞባ ተንቤን የሚከተለውን በከፊል ከፌስ ቡክ ገጹ ላይ ወስደናል።
ዞባ ተምቤን Tembien Province· የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ እና ሶስት ጓደኞቹ ትላንት በመቐለ ከተማ ከምሽቱ 2 30 አከባቢ የበተኑት ወረቀት ቃል በቃል የሚለውን ይዘን ቀርበናል።
“ህዝቢ ትግራይ ንክፀንት ብዝከኣለኩም ትረባረቡ ዘለኹም ኸደምቲ ስርዓት ኣብይን ብልፅግናን ዝኾንኩም ተወለድቲ ትግራይ ናይ ብልፅግና መራሕቲ ቀብርኹም ኣብ ቀረባ እዋን ክገሃድ ‘ዩ።
የአማርኛው ትርጉሙ – “የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ በምትችሉት እየተንቀሳቀሳቹህ ያላአቹህ የአብይ እና የብልፅግና አገልጋዮች የሆናቹህ የትግራይ ተወላጆች የብልፅግና አመራሮች ቀብራቹህ በቅርቡ ገሃድ ይሆናል።
በትግራይ ክልል ማታ ከአንድ ሰአት ቦሃላ ማንኛውም አካል መንቀሳቀስ እንደማይቻል ኮማንድ ፖስቱ ህግ አውጥቷል። ሲልም ዞባ መረጃ ይሰጣል። ኢትዮ 12 ዜናውን በራሱ መነግድ ለማጣራት አልቻለም። ይሁን እንጂ የሶስት ወገኖችን መረጃ ጨምቀን አቅርበናል። ከዚህ የዘለለ መረጃ ማግኘት ከቻልን እንመለስበታለን። አስገድዶ ማስቆም ያልተቻለበትን ምክንያት ለማወቅ ግን ጥረታችን ይቀጥላል።
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ