Category: SOCIETY

የማህበር ቤት ምዝገባ ለተጨማሪ አስር ቀናት መራዘሙን ቢሮው አስታወቀ

ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት ሲካሄድ የቆየ የማህበር ቤት ምዝገባ ለተጨማሪ አስር ቀናት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ በተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎች ያስተላለፈና ተጨማሪ ቤቶችንም በመገንባት ላይ […]

ሙስሊሙ ህብረተሰብ የረመዳን ፆምን በፍቅርና በመተጋገዝ እንዲያሳልፍ ተጠየቀ

ሙስሊሙ ህብረተሰብ የ1442 ኛው የረመዳን ፆም ለፈጣሪው በመገዛት፣ በፍቅር፣ በመረዳዳትና በመተጋገዝ ሊያሳልፈው ይገባል ሲል የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለጸ:: በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለአዲስ አበባ ከተማና ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ህዝበ ሙስሊሞች ዛሬ የተጀመረውን የ1442 ኛው የረመዳን ፆም በማስመልከት የእንኳን […]

“ፊቤላ ኢንዱስትሪ 12 ነጥብ 2 ሚሊየን ሊትር የሚጠጋ ዘይት ለገበያ አቅርቧል”

አቶ በላይነህ ክንዴየፊቤላ ኢንዱስትሪ ባለቤትና የቢኬጂ የቦርድ ሰብሳቢ ፊቤላ ኢንዱስትሪ በመጀመሪያው ዙር የውጭ ምንዛሪ ተመድቦለት ባስገባው ጥሬ እቃ ተጠቅሞ 12 ነጥብ 2 ሚሊየን ሊትር የሚጠጋ ዘይት እና 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ተጓዳኝ ምርቶችን አምርቶ ለገበያ ማቅረቡን የፊቤላ ኢንዱስትሪ ባለቤትና የቢኬጂ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይነህ ክንዴ አስታወቁ። ስምንት ሚሊየን […]

ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ አካባቢዎች ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገለጸ

ከዚህ በፊት በነበረው መረጃ አብዛኛው ሥርጭት የሚከሰተው አዲስ አበባ ውስጥ እንደነበር የገለጹት ዶክተር ደረጀ፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ግን በክልሎች የቫይረሱ ወረርሽኝ እየተስፋፋ መምጣቱን አመልክተዋል። በአንዳንድ የክልል ከተሞች ከሚመረመሩ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ከ30 በመቶ በላይ ሆኗል ብለዋል።

ጭው ባለ በርሀ፤ እንደ እሳት በሚፋጅ ሙቀት ውስጥ ፤ አንዲት ትንሽ መንደር….

መጋቢት 25 ቀን 2013 “ድንበር ተሻጋሪው ህዝባዊነት” ጭው ባለ በርሀ፤ እንደ እሳት በሚፋጅ ሙቀት ውስጥ ፤ አንዲት ትንሽ መንደር…. የሁለቱ ሱዳኖች የግጭት ቦታ በነበረችው ፣ በአብዬ ደቡባዊ ሴክተር በ24ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የግዳጅ ቀጠና ውስጥ የምትገኝ ‘አንቶኒ መንደር ‘…. በመንደሯ ውስጥ ትንንሽ የሳር ጎጆዎች አለፍ አለፍ ብለው […]

የዶሮ እርባታ ማዕከላት በገጠማቸው የመኖ እጥረትሊዘጉ መቃረባቸው ተጠቆመ

በሀገሪቱ የሚገኙ ጥቂት የዶሮ እርባታ ማዕከላት በገጠማቸው የመኖ እጥረት ሊዘጉ ጫፍ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች ማህበር ፕሬዚዳንትና የሀዋሳ ዶሮ እርባታ ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገነነ ተስፋዬ አስታወቁ። ፕሬዚዳንቱ በተለይም ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ በሀገሪቱ አሁን እየታየ ያለው የዶሮ በተለይም የእንቁላል እጥረት የተከሰተው ማባዣ ማዕከላቱ በገጠማቸው የመኖ እጥረት መሆኑን […]

ክፉው ቀን ሳይመጣ ጆሮ ያለው ይስማ – ባለፉት ሰባት ቀናት 14 ሺህ 437 ግለሰቦች በኮቪድ19 ተይዘዋል 149 ሞተዋል

ባለፉት ሰባት ቀናት ከመጋቢት 17 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 14 ሺህ 437 ግለሰቦች በኮቪድ19 መያዛቸው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፡፡ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 100 ግለሰቦች ውስጥ 25ቱ ቫይረሱ እንደተገኘባቸውም ኢንስቲቲዩቱ ገልጿል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥም 149 ግለሰቦች ህይወታቸውን አጥተዋልም ነው ያለው፡፡ በትናንትናው እለት ለ8 ሺህ 294 […]

ቻይና ለኢትዮጵያ ያበረከተችው 300 ሺህ ዶዝ ሲኖፋርም የኮቪድ-19 ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ ገባ

ክትባቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ዣዎ ዢውሃንና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል። ከዚህ ቀደም ከኮቫክስ ጥምረት 2.2 ሚሊየን ዶዝ ክትባት ወደ ሀገር መግባቱና ለጤና ባለሙያዎች መሰጠቱ የሚታወስ ነው። አሁን ከቻይና መንግስት የተገኘው የክትባት […]

ኢትዮጵያ በተራራ የተከበበች መሆኗ ዳመና አዝናቢ ኬሚካልን ወደ አየር ለመልቀቅ ምቹ መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በተራራ የተከበበች አገር መሆኗ ዳመና አዝናቢ ኬሚካልን ወደ አየር ለመልቀቅ የተሻለ ዕድል እና ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አመለከቱ። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ክንፈ ኃይለማርያም በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ ኢትዮጵያ የመልክአ ምድሯ መለያየት የሚታይባት፤ ተራራማ አካባቢዎች የሚበዙባት መሆኗ ዝናብ አምጪ ኬሚካሎችን ወደ ደመና […]

“ … ግብርና ወደ ሜካናይዜሽን ማስገባት በግብርና ምርቶች ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመከላከል ወሳኝ ሚና ይኖረዋል”

“ … ግብርና ወደ ሜካናይዜሽን ማስገባት በግብርና ምርቶች ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመከላከል ወሳኝ ሚና ይኖረዋል” የአማራ ክልል ምክር ቤት በ5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር ከሰሞኑ ጠንከር ያለ የውሳኔ ሃሳብ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ አብመድ የአስፈፃሚ አካላት ውሳኔ አተገባበር […]

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተወሰኑ የሠራዊቱ አባሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ

ትግራይ ክልል፤ በአክሱም ከተማ የተፈጸመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በአጠቃላይ በክልሉ የተሟላ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነትን ያመለክታልበአክሱም ከተማ፣ ትግራይ ክልል የደረሰውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርቱን ይፋ አደረገ። ከበርካታ ሳምንታት ጥረት በኋላ የምርመራ ባለሞያዎቹን […]

ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምቀው ዘውትር ቢጠጡ እነዚህን 10 የጤና ጥቅሞች ያገኛሉ

ጉበቶን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳሉ፡፡ለብ ባለ ውሃ ውስጥ የሎሚውን ጭማቂ (ፈሳሽ) ብቻ ሳይሆን የሎሚው ልጣጭ ጭምር ከተን የምንጠጣ ከሆነ ደረጃ 2 የጉበት ፀረ- መርዝ ማስወገድ ተግባራን ያከናውናል፡፡ ጉበቶ ሐሞት እንዲያመነጭ በማበረታታት ቅባታማ ምግቦችን ሰውነቶ እንዲፈጭ ይረዳል፡፡ ሎሚ ከፍተኛ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ ስላለው ሕዋሳታችን(cells) እንዳይወድሙ ይጠብቃቸዋል፡፡ በሎሚ ውስጥ ያለው አንቲ- […]

ዕድሜዋ 4 ዓመት የማይሞላትን ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ተከሳሽ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 4 ዓመት የማይሞላትን ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ተከሳሽ በህፃኗ ላይ የክብረ ንፅህና መገርሰስ ባያደርስም በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል። የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው አሸናፊ ከድር ሰኢድ የተባለው ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627/1 ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ሰኔ 20/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ በአዲስ […]

በስምሪት መስመራቸው አገልግሎት በማይሰጡ ታክሲዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

በተሰጣቸው የስምሪት መስመር የትራንስፖርት አገልግሎት በማይሰጡ ታክሲዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ። ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች የታክሲ አገለግሎት ችግር ተስተውሏል። የትራንስፖርት እጥረቱ የተከሰተው አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች በመደበኛ የስምሪት መስመራቸው ተገኝተው ሥራቸውን ባለማከናወናቸው መሆኑን ከከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት […]

ሲስተር አሠጋሽ ጎሳ ሰማኒያ ጊዜ ደም በመለገስ የሴቶችን ክብረወሰን ያዙ

ዛሬ ደም ውድ በሆነበት ጊዜ ላይ ሲስተር አሠጋሽ ጎሳ ደም በመለገስ የሴቶችን ክብረወሰን መያዛቸው ተሰማ። ሲስተር አሠጋሽ ጎሳ ለ80ኛ ጊዜ ደም በመለገስ በኢትዮጵያ የሴቶችን ክብረወሰን መያዛቸውን ያስታወቁት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ናቸው። ዶክተር ሊያ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ “ሲስተር አሠጋሽ ጎሳ ነርስም፣ እናትም ቀዳሚ ደም ለጋሽም በመሆን ዛሬ […]