Site icon ETHIO12.COM

“ነጭ ቀለም ያላቸው የአረብ ወታደሮች በኢትዮ ሱዳን ድንበር እየሰፈሩ፣ አዳዲስ ከምፕ እየገነቡ ነው”

ወታደሮቹ ለጋ እድሜ ያላቸው ወጣቶች፣ አረብኛ የሚናገሩ፣ ሱዳኖቹ የማያውቋቸው፣

ድግሱ ብዙ ነው። እቅዱ ብዙ ነው። የታሰበው እጅግ የከፋ ነው። ሃሳብና እቅዳቸውን ለማስፈጸም ከፋፍለው፣ ለያይተውና እርስ በርስ በማጫረስ ነበር ሊፈጽሙት ያሰቡት። ሁሉም አልተሳካም። ዛሬ የመጨረሻዋ ወቅት ላይ ነን። ይህን ጊዜ ለማለፍ አንድ መሆን ግድ ነው። አንድ ካልሆን እንዋረዳለን። ሊያዋርዱን እየተንቀሳቀሱ ያሉ በባንዲራና በአገር የሚምሉ አሉ። ሕዝብ ያስብ። በዚህ ወቅት ቅድሚያ ዜጎች ልመን ትኩረት ሊሰጡ ይገባል? የአማራ ክልል ስላም መሆን ራሳቸውን የሚያሳምማቸው ወገኖች ሃሳባቸው ምን ይሆን? ከዚህ ሌላ የምለው የለም…. አስተያየት የሰጡ ብራስል ነዋሪ

ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቃ ወረራ ከፈጸመች በሁውላ አዳዲስና ቀደም ሲል ታይቶ የማያውቅ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑ ይሰማል። ከሁሉም በላይ ግን ዛሬ የተሰማው መረጃ ወረራው የሶሰተኛ ወገን አጀንዳን ለማስፈጸም የተካሄደ ለመሆኑ ማረጋገጫ ተደርጎ ተውስዷል።

በመተማ ወረዳ የመርትርናር ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ አለሙ አወቀ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ እንዳሉት ቀለማቸው የተለመደው የሱዳኖችን የማይመስል ወታደሮች እንደሚታዩ ገልጸዋል። እንዲያብራሩ ተጠይቀው። ቀያይ መሆናቸውን፣ አረብኛ እንደሚናገሩ አስረድተዋል።

Related stories   የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ዳዊትና ጓደኛው ተገደሉ፤ “የትግራይ ተወላጆች የብልፅግና አመራር ቀብራቹህ በቅርቡ ገሃድ ይሆናል”Powered by Inline Related Posts

የድንበር ቀበሌ ሊቀመንበር እንደመሆናቸው በየእለቱ መረጃ እንዳላቸው ያስታወቁት አቶ አለሙ፣ ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ሱዳን እነዚህን ነጭ አረብ ወታደሮች እያሰፈረች እንደሆን አመልክተው ” የምንቀርባቸው ሱዳኖች እነሱም እንደማያውቋቸው ነግረውናል” ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ወራ ከያዘች በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እያዘለቁ የወታደራዊ ከምፕ እንደሚገነቡ ያመለከቱት አቶ አለሙ ከትናንት በስቲያ ለሊት ላይ የሱዳን ወታደሮች ተኩስ ከፍተው በረት በመስበር 250 ከብቶችን መንዳታቸውንም አመልክተዋል።

የአገር መከለከያ ኤታማዦርሹም ብርሃኑ ጁላ በቅርቡ ሱዳን ለሶስተኛ ወገን ስትል የገባችበትን የውክልና ወርራ እንድታቆምና ወደ ነበረችበት ቦታ እንድትመለስ በተደጋጋሚ እየተነገራት እንደሆነ መናገራቸው የሚታወስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድም “ የትዕግስት ክንድ ከተሰነዘረች ሳታደቅ አትመለስም” ሲሉ ዓመት በዓልን አስታከው ባስተላለፉት መልዕክት መናገራቸው አይዘነጋም።

The Egyptian Armed Forces Chief of Staff Lieutenant General Mohamed Farid met with Sudanese officials in Khartoum to talk ways of enhancing military and security cooperation between the two countries.

መንግስት የህግ ማስከበር የሚለው ዘመቻ በአብዛኛው መጠናቀቁን ተከትሎ ሱዳን ወራራ ያካሄደችው በሁመራ በኩል ለትህነግ አመራሮች የመውጪያ በር ለማዘጋጀት እንደሆነ ይነገራል። ከዚያም አልፎ በቤኒሻንጉል የተጀመረው የጅምላ ጭፍጨፋ ጦርነቱን ለመለጠጥና መንግስት ሰራዊቱን ሲበታተን በትግራይ የተበተነውን ሃይል ለማሰባሰብ ታቅዶ በመሆኑ የተነሳ መንግስት ሱዳን ላይ ለመለሳለሱ እንደምክንያት ይቀርባል።

Related stories   ኢትዮጵያ በወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ ከአፍሪካ 6ኛ ከዓለም 60ኛ ሆነችPowered by Inline Related Posts

ተደጋግሞ መንግስት ሲናገር እንደሚሰማው ከሱዳን ጋር ሳይቋጭ ለቆየው የድንበር ውዝግብ መፍትሄ ለመፈለግ ሱዳን አስቀድማ የወረረችውን መሬት መልቀቅ አለባት። ከሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት ዘንድ የሚሰማው ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት አይፈልጉም ፤ ስንዝር መሬትም መልቀቅ አይችሉም።

Exit mobile version