እየፈታን እናልቅስ ለኢትዮጵያ እንቁም

የወገን ሞት ያማል። ሕመሙም የአጥንት ሕመም ነው። በአንድ በኩል የተጎዱትን እየረዳን፣ በሌላ በኩል የሌሎችን ጉዳት ለማስቀረት አንድ ሆነን መሥራት አለብን። የዘመድ ቄስ እንሁን። እየፈታን እናልቅስ። ለኢትዮጵያ እንቁም።

ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን 3ኛ ዙር ልትሞላ ነው። ይሄንን ዙር ሞልታ ብትተወው እንኳን የሕዳሴው ግድብ ሥራውን ይቀጥላል። ያም ማለት ኢትዮጵያ የላይኛው ተፋሰስ ብቻ ሳትሆን የላይኛው ወሳኝ አካል ትሆናለች ማለት ነው።
ይሄንን ወሳኝ የሀገር ግብ ለማምከን ግብጽና ሱዳን ከአንዳንድ የምዕራብ ሀገሮች ጋር ሆነው የግመሉን ጀርባ የሚሰብረውን የመጨረሻውን ጭነት ኢትዮጵያ ላይ ለመጣል እየተረባረቡ ነው።

ብዙ ጊዜ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ከአፋቸው የማይጠፋው ምዕራባውያን፣ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው አረንጓዴ ዐሻራ የገንዘብ ድጋፍ ሲጠየቁ ” ግብጽ ተቃውሞ ስላላት እንቸገራለን” ነው ያሉት። ግብጾች አረንጓዴ ዐሻራን የኢትዮጵያን አፈር ለማስቀረት የተጀመረ ዘመቻ ነው ብለው ነው የሚወስዱት። ግድቡን ማስቀረት ባይችሉ እንኳን በደለል እድሜውን ወይም ዐቅሙን ማሳጠር አንዱ ዓላማቸው ነው። ትግሉ ብዙ መልክ ነው ያለው።

ግብጽና ሱዳን ከአንዳንድ የምዕራብ ሀገሮች የመረጃና የዲፕሎማሲ ድጋፍ በማግኘት ከ4 አካላት ጋር ይሠራሉ። አሠልጥነው በሳዑዲ ተመላሽ ስም ካስገቧቸው አካላት፤ ከአሸባሪ የውጭ ኃይሎች፣ ከአሸባሪ የሀገር ውስጥ ተቋማት እና ከሱዳን ታጣቂዎች ጋር።

በሳዑዲ በረሃ ያሠለጠኗቸውን የኢትዮጵያ ስደተኞች ለማስገባት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ፈጥረው ነበር። በማኅበራዊ ሚዲያ በታገዘ ዘመቻ የኢትዮጵያውያን ኅሊና እንዲጨነቅ አድርገው ተጽዕኖ ፈጥረዋል። እንደ አልሸባብ ያሉትን አሸባሪዎች በምሥራቅ ኢትዮጵያ ለማስገባት ሞክረዋል። የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ በኩል ጫና እንዲፈጥሩ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። የሕወሓት ሰዎች በጁባ በኩል ገብተው ረብጣ ብር እያከፋፈሉ ይሄንን ሲሠሩ ነው የከረሙት። የሸኔ፣ የጋምቤላና የጉሙዝ አሸባሪዎች ሥልጠና ወስደው በሳተላይት መረጃ እየተመሩ በግብጽ ድጋፍ የምዕራቡን ድንበር ፋታ እንዲነሡ ተልከዋል። በአማራ ክልል ያሉ፣ ታጣቂ ነን ባዮችም ከውስጥ ሆነው እንዲረብሹ ሥራ ተሰጥቷቸዋል።
የሱዳን ወታደሮች በኢትዮጵያ የሰሜን ምዕራብ ድንበር ጫና ለመፍጠር ትንኮሳ ጀምረዋል።

ብዙ ጊዜ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ከአፋቸው የማይጠፋው ምዕራባውያን፣ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው አረንጓዴ ዐሻራ የገንዘብ ድጋፍ ሲጠየቁ ” ግብጽ ተቃውሞ ስላላት እንቸገራለን” ነው ያሉት። ግብጾች አረንጓዴ ዐሻራን የኢትዮጵያን አፈር ለማስቀረት የተጀመረ ዘመቻ ነው ብለው ነው የሚወስዱት። ግድቡን ማስቀረት ባይችሉ እንኳን በደለል እድሜውን ወይም ዐቅሙን ማሳጠር አንዱ ዓላማቸው ነው። ትግሉ ብዙ መልክ ነው ያለው።

በኢትዮጵያውያን ስም እየተጻፉ ከግብጽ የሚመነጩ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች በውስጥ በሚገኙ አጋጋዮች እየታገዙ የፕሮፓጋንዳ ሥራውን አጧጡፈውታል። በየአካባቢው ዐመጽ ለመቀስቀስ የወጠኑት ሤራ አልይዝ ሲላቸው፣ የጊምቢውን ጭፍጨፋ ለማውገዝ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን “ዐመጽ” ብለው እስከመጥራት ደርሰዋል።

See also  ኦነግ መንገድ ሲጠግኑ ውለው ወደ ማረፊያቸው ሲጓዙ የነበሩ አስር ሰዎች ገደለ " መኪናቸውን ከበው ጨረሷቸው"

የዚህ ሁሉ ዓላማ ሁለት ነው። ኢትዮጵያውያንን በሐሳብ መከፋፈልና የመከላከያ ሠራዊቱን መወጠር። በፕሮፓጋንዳ ሥራው ኢትዮጵያውያንን በመከፋፈል፣ በጠላቶቻቸው ላይ አንድ ሆነው እንዳይቆሙ ለማድረግ ሁለት ዘዴዎች ታቅደዋል። በተገኘው አጋጣሚ ንጹሐንን በመግደል የሕዝቡን እፎይታ መንሣት የመጀመሪያው ነው። ከሰሞኑ የታየው የምዕራብ ወለጋ አሰቃቂ የአማራዎች ጭፍጨፋ የዚህ አካል ነው። የተፈለገው መግደል ብቻ ሳይሆን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ሕዝቡን ማሸበር ነው። መጀመሪያ በሱማሌ ክልል አልሸባብ ሞክሮ ከሸፈበት፤ በመቀጠል በጋምቤላና በደምቢዶሎ አካባቢ ተሞክሮ ከሸፈ። በመጨረሻ በቀቢጸ ተስፋ የጊምቢው ጭፍጨፋ ተፈጸመ። በሌሎች አካባቢዎች ሊፈጸሙ የነበሩ ክሥተቶችም በጸጥታ አካላት በየቀኑ እየከሸፉ ነው። የሚያመልጡ አይኖሩም ብሎ መገመት ግን አይቻልም።

የፕሮፓጋንዳው ሌላው አካል ከግብጽ በሚመነጩና በኢትዮጵያ ተላላኪዎች በሚታገዙ የማኅበራዊ ሚዲያ ባንዳዎች የሚሠራ ነው። እምነትንና ብሔርን መሠረት ያደርጋል። በብሔሮች መካከል ብጥብጥ ለመፍጠር እየተሠራ ነው። የኦርቶዶክስ እና የእስልምና እምነቶችን ወደ ግጭት ለመክተት የታቀዱ ሤራዎች አሉ። ዋና ዋና የእምነቱ አስተማሪዎችን በመጠቀም ብጥብጥ መፍጠር። እነዚህ ሁሉ አንጀት መጎተቻ ናቸው።

የዚህ ድምር ውጤት ሠራዊቱ ስትራቴጂካዊ ቦታ ይዞ ለከፋው የሉዓላዊነት ግድጅ እንዳይሠማራ ለማድረግ ነው። እዚህም እዚያም በመተንኮስ ሠራዊቱን ከድንበር ወደ መንደር ለማውረድ። ይሄንን ለማሳካት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀምሯል። በተለይም ወሳኝ ከሚባሉ አካባቢዎች ሠራዊቱ ወደ ግጭት ቦታዎች እንዲሳብ ለማድረግ እየተሠራ ነው። የሠራዊታችንን ዐቅምና የዝግጁነት ልክ ጠላቶቻችን ጠንቅቀው ያውቁታል። ካለፈው ጦርነት በኋላ የኢትዮጵያ ሠራዊት የት ደረጃ ላይ እንዳለ ከወዳጆቻችን በላይ ጠላቶቻችን እየመረራቸውም ቢሆን ያውቁታል። ያላቸው አማራጭ ለተጨማሪ ዝግጁነት ፋታ እንዳያገኝ መወጠር ነው ብለው አምነዋል። በዚህ በዚያ ሞከሩ። እምቢ አላቸው። አሁን የንዴት ሥራቸውን ሊሠሩ ተነሥተዋል።

በፕሮፓጋንዳ ሥራው ኢትዮጵያውያንን በመከፋፈል፣ በጠላቶቻቸው ላይ አንድ ሆነው እንዳይቆሙ ለማድረግ ሁለት ዘዴዎች ታቅደዋል። በተገኘው አጋጣሚ ንጹሐንን በመግደል የሕዝቡን እፎይታ መንሣት የመጀመሪያው ነው። ከሰሞኑ የታየው የምዕራብ ወለጋ አሰቃቂ የአማራዎች ጭፍጨፋ የዚህ አካል ነው። የተፈለገው መግደል ብቻ ሳይሆን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ሕዝቡን ማሸበር ነው። መጀመሪያ በሱማሌ ክልል አልሸባብ ሞክሮ ከሸፈበት፤ በመቀጠል በጋምቤላና በደምቢዶሎ አካባቢ ተሞክሮ ከሸፈ። በመጨረሻ በቀቢጸ ተስፋ የጊምቢው ጭፍጨፋ ተፈጸመ። በሌሎች አካባቢዎች ሊፈጸሙ የነበሩ ክሥተቶችም በጸጥታ አካላት በየቀኑ እየከሸፉ ነው። የሚያመልጡ አይኖሩም ብሎ መገመት ግን አይቻልም።

ይህ ሁሉ የኢትዮጵያን እግር ሰብሮ ሽባ የማድረግ ዕቅድ የሚከሽፈው የጠላትን ዕቅድ ተረድቶ፣ አንድ ሆኖ በመቆም ነው። አመራሩ እጁንና ልቡን ንጹሕ አድርጎ፣ በጎጥና በጥቅም ከመጓተት ወጥቶ ግዳጁን ይወጣ። አካባቢውን ይጠብቅ፤ ያስጠብቅ፤ ከከፋፋይ ሐሳቦች ይታቀብ። ሕዝቡም ወገቡን አሥሮ፣ ሐሞቱን አኮሳትሮ ለየአካባቢው ዘብ ይቁም። የወገን ሞት ያማል። ሕመሙም የአጥንት ሕመም ነው። በአንድ በኩል የተጎዱትን እየረዳን፣ በሌላ በኩል የሌሎችን ጉዳት ለማስቀረት አንድ ሆነን መሥራት አለብን። የዘመድ ቄስ እንሁን። እየፈታን እናልቅስ። ለኢትዮጵያ እንቁም።

See also  አማራን ለይቶ የተካሄደው ጭፍጨፋ - ክልሉ የጀመረውን የህግ ማስከበር ስራ መስመር ለማሳት መሆኑ ተሰማ

በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን ለመታደግ፣ ከጸጥታ አካላት ጋር አንድ ሆነን ከመቆም የተሻለ ምንም አማራጭ የለም። ጥርሳችንን ነክሰን ወሳኝ ምዕራፎቻችንን የግድ እንሻገር።

ዳንኤል ክብረት

Leave a Reply