Site icon ETHIO12.COM

በርካታ የጦር መኮንኖች በአሰሳና ፍተሻ ተያዙ፤ አሰሳው ቀጥሏል

የመከላከያ ሚኒስቴር ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት አስራ ስምንት ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ውለዋል። እነዚህ ከፍተኛ መኮንኖች የተያዙት በፍተሻና በመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ጸጥታ ሃይሎች የጋራ አሰሳና ፍተሻ ነው።

ከጁንታው የጥፋት ቡድን ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሰለፉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለመንግስት እንዲሰጡም በድጋሚ ጥሪ ቀርቧል። የመከላከያ ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ለኢዜአ አንደገለጹት 18ቱ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉት የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ጸጥታ ተቋማት በቅንጅት ባካሄዱት አሰሳና ፍተሻ ነው።

በቀጥጥር ስር ከዋሉት መኮንኖች መካከል ዘጠኙ የሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ፤ ሰባቱ የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ ያላቸውና ሁለቱ ደግሞ የፖሊስ ኮማንደሮች መሆናቸውን ገልጸዋል። ሜጀር ጄኔራል መሃመድ፤ ወንጀለኞችን የማደኑ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

ከጁንታው የጥፋት ቡድን ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሰለፉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለመንግስት እንዲሰጡም ሜጀር ጄኔራሉ በድጋሜ ጥሪ አቅርበዋል። ህዝቡም ለፀጥታ ሃይሉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል።

በቅርቡ ከጁንታው የጥፋት ቡድን ጋር ተሰልፈው ከነበሩት ከፍተኛ መኮንኖች መካከል ሜጀር ጄኔራል መሀመድ እሻን ጨምሮ ሌሎች የጁንታው ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እጃቸውን መስጠታቸው ይታወሳል።


Exit mobile version