Site icon ETHIO12.COM

አዳነች አቤቤ የጥናት ግኝቱ ለአቃቤ ህግ መመራቱ አስታወቁ

የኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በተጠናው ጥናት መሰረት ህግ ፍርዱን እንዲሰጥ የጥናት ግኝቱ ለፌደራል አቃቤ ህግ መላኩን አዳነች አቤቤ አስታወቁ። ጥናቱ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ የኮተቤ ሜትሮ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ መስፈርቱን ያሟላ ብሎታል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተጠቀሱትና በጥናቱ የተካተቱት ጉዳዮች በህዝብ ዘነዳ ከፍተኛ ቅሬታ ሲስተናገድባቸው የቆዩ ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን አመልክተዋል። ከንቲባዋ በማህበራዊ ገጻቸው እንዳሉት በጥናቱ ግኝት መሰረት ማስተካከያ ተወስዶ ፍትሃዊ አገልግሎት ይሰጣል።

አገልግሎቱን ፍትሃዊ ከማድረግ በተጨማሪ በጉዳዩ የተሳተዱ ወገኖች ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ይሆኑ ዘንድ ሰነዱ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ መላኩን ትፋ አድርገዋል። በተደጋጋሚ ሲነገር እንደነበረው ቀደም ሲል ከሌብነት ጋር በተያያዘ ስማቸው የሚነሳና ከፍተኛ ሃብት የሰበሰቡ የህግ ተጠያቂነትን ፍርሃቻ ስላለባቸው ለውጡን ጠልፈው ከሚጥሉ ጋር በሴራ ፖለቲካው ውስጥ ተሳታፊ ሆነው እንደቆዩ ሲዘገብ ነበር።

ለውጡ ከተረጋጋና መልክ ከያዘ ተጠያቂነት ሊነሳ ያችላል በሚል ስጋት አንድ እግራቸው ለውጡ አራማጆች ዘንድ፣ ሌላኛውን ከአደናቃፊዎቹ ጋር በማድረግ የሚነቀሳቀሱ መኖራቸውን መንግስት፣ ህዝብ፣ የሴራው ሰላባዎች፣ እንዲሁም የፍትህ አካላት በተደጋጋሚ ሲያስታወቁ ነበር።

አጋጣሚውን ጠብቀው በዝርፊያ የተሰማሩ ወፍ በረር ህገወጦች መኖራቸው በተደጋጋሚ ሲገለጽ እንደነበር፣ በቡድን መጥተው አንድን አካባቢ በመውረር በትሥሥር ህጋዊ የማድርገና ተግባር በፋት አዲስ አበባ ውስጥ መከናወኑ ቀደም ሲል ጀመሮ የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርብባቸው ሲሆን፤ መንግስት ህግ ሲያስከበር ማህበራዊ ቀውሱን በማጉላት መንግስትን የሚያወግዙ፣ አውሬ አድረገው የሚያሳዩ፣ እንዲሁም ህግ ማስከበሩን ከብሄርና ከቡድን ፍላጎት ጋር በማያያዝ ፖለቲካዊ ይዘት እንዲሰጣቸው መደረጉ ለህገወጦች ከፍተኛ ድጋፍ እንደሆነ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ገጻቸው ይህንን ብለዋል።

Exit mobile version