Site icon ETHIO12.COM

“ምቀኝነትን እናቁም፤ ውድድር እወዳለሁ አገሬን የሚጎዷትን ግን አልወዳቸውም” በላይነህ ክንዴ

ኢትዮ 12 ዜና – ” አንዱ ሲሰራ መመቅኘት ጥሩ አይደለም” የሚሉት ባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ ቅናት የአገራችን ትልቁ ችግር መሆኑንን ያሰምሩበታል። በራስ መቆምን ሲናገሩ ደግሞ ” ክህወሃት ውርደት እንማር” በማለት ነው። ተስፋቸውን ደግሞ ” ጊዜው ከሰራንበትና አንዱ ለሌላው አስፈላጊ መሆኑንን በማመን ከተጠቅምንበት” በሚል ጉጉት ነው።

በቅርቡ ስድስት አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ ገደማ ተፈናቃዮችን ለአንድ ወር የሚሆን ቀለብ በማቅረብ አጋርነታቸውን የገለጹት አቶ በላይንህ ክንዴ አገራችን በኢኮኖሚ ማደግ እንዳለበት በእጅጉ ያምናሉ። ዩክሬን ስድስት ወር ክረምት መሆኗን ጠቁመው ባላቸው አጭር በጋ ሰርተው ራሳቸውን እንደቻሉ ጠቁመው፣ ” እኛ እጃችን አጣጥፈን ተረት እያወራን” ሲሉ የተበላሸ የስራ ባህልና አመለካከት እንዳለን ያመላክታሉ።

በአገሪቱ ትልቁን የሚባል የዘይት ማምረቻ አስገንብተው ወደ ስራ የገቡት ባለሃብቱ ” ምድራችን ወርቅ አላት” አሉ። ግን ደሃ ህዝብ ይዘን ሰርተን እንዳንጠቀምበት ከውስጥም ከውጭም ጠላቶቻችን፣ በተለይም የስጥ ሴረኞች እንቅፋት መሆናቸው አሳዛኝ ጉዳይ ነው። እሳቸው እንዳሉት እንዲህ ያሉት በትግል ወድቀዋል። በቀጣይም መታገል አስፈላጊ ነው።

ተወዳዳሪዎች ጠላት እንዳልሆኑ ያመለከቱት በላይነህ ክንዴ፣ “ይሄ የኔ ነው ” የሚለው አስተሳሰብ አገሪቱን ስለሚጎዳ ሁሉም ወገን አንዱ ያለው ለሌላው አስፈላጊ መሆኑን፣ ይህም ተፈጥሯዊ መሆኑንን ተረድቶ በህብረት ወደ እድገት የሚወስደውን መንገድ ሊከተል እንደሚገባ አመላክተዋል።

ሁለትና ሶስት እንጀራ እንደሚበላ ሰው መንገብገብና ለባቻ ስለመበልጸግ ማሰብ እንደማይጠቅም ባለሃብቱ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ይፋ ያደረገው አጭር ቃለ ምልልስ እንደሚያስረዳው አቶ በላይነህ አገሪቱን ጠፍንገው ይዘዋት የነበሩ የተወሰኑ ቫንጋርዶች እነደነበሩ ገልጸዋል። ይሄ የኔ ነው በሚል ላለፉት ዓመታት ሁሉ ይሄ የእኔ ነው በሚል እሳቤ ተጉዘን ሊሳካልንና እንዳልቻለ፣ ከድህነት እንዳንወጣ እንድደረገን አስታውቀዋል።

” ሁሉንም ይቅር ብለን እንኑር ሲባሉ እምቢ አሉ፤ አሁን ተዋረዱ” ሲሉ ለትምህርት ይሆን ዘንድ የትህነግን መጨረሻ ያጣቀሱት ባለሃብት፣ የትህነግ መጨረሻና እድል ፈንታ ለፖለቲከኞች፣ ለባለሃብቶችና ለአጠቃላይ አገራችን ታላቅ ትምህርት እንደሆነ አመልክተዋል። ከነሱ ጋር ንክኪ የነበራቸው ባለሃብቶች መጎዳታቸውንም አውስተዋል።

” ውድድር እወዳለሁ ነገር ግን አገሬን የሚጎዱትን አልወዳቸውም” በሚል ነገሮችን በትልቋ ስዕላቸው ኢትዮጵያ እንደሚመዝኑ ሳይሸሽጉ የገለጹት አቶ በላይነህ ” አብይ አሕመድን እደግፋቸዋለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል። ሲያብራሩም ” 50 ዓመታት ኢትዮጵያን ሊያጠፉ ሲሰሩ ከነበሩ የኢትዮጵያ ልጆች ስልጣን ነጥቀው አገሪቱ አንድ እንድትሆንና እንድትቀጥል የሚያደርጉትን አግዛለሁ” ሲሉ ነው ድጋፋቸውን የገለጹት።

ኢትዮ 12 ዜናን ይርዱ፣ ሰብስክራይብ ያድርጉ፣

ቪዲዮውን ይመልከቱ

Exit mobile version