Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ሱዳን ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ እንደምትገደድ አስታወቀች!!

የግብጽን ስም ቃ በቃል በይገልጹም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ የሌላ አገር አጀንዳ እያስፈጸመች ነው በሚል የሚከሷት ሱዳን ላይ ኢትዮጵያ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ እንደምትገደድ የትላንትናው አዲስ አድማስ ጋዜጣ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጠቅሶ ዘግቧል። መረጃው ምንም ይሁን ምን ጦርነት ዛሬ ላይ እንደማያዋጣ በርካቶች ያምናሉ። ከጊዜ አንጻር!!

የአገር መከላከያ ኤታማዦር ሹም ብርሃኑ ጁላ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከሱዳን ጋር ችግሩን በድርድር ለመፍታት አስፈላጊ የተባለውም ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ስለ ” ተመጣጣኝ እርምጃ” ያሉት ነገር ባለመኖሩ አዲስ አድማስ የዘገበው ዜና አዲስ ሆኗል። ዜናው አምብሳደሩን በግል ያናግር ወይም ከሌላ ሚዲያ ይጥቀሳቸው በግልጽ አልስቀመጠም።

ኢትዮጵያ የሱዳን ወረራ በተወሰኑ ቡድኖች የሚመራና የመላው ሱዳን አቋም እንዳልሆነ እንደምታምን በተደጋጋሚ ስትገልጽ ብትቆይም፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በኩል በቀርቡ ከቀናት በፊት ይፋ ያደረገቸው ጠንካራ አቋም ” ሱዳን በሃይል የተያዘችውን የኢትዮጵያን ድንበር ሳትለቅ ድርድር ብሎ ነገር የለም” የሚለው ነው። ሱዳንም በበኩሏ የይዛቸውን ቦታ እንደማትለቅ በጀነራሏ አማካይነት በይፋ አስታውቃለች።

” ከብዙ ትዕግስት ውስጥ የምትወጣ ሃይል ሳታደቅ አትመለስም”

አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር

በትግራይ የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ሰፊ ሃይሏን ያሰማራቸው ኢትዮጵያ በቤኒሻንጉል የተከፈተባትን የተቀናጀ ጥቃት ስታስተነፍስ ከሱዳን ጋር ምንም ዓይነት ግጭት ውስጥ እንደማትገባ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ይናገራሉ። በዚህ ሁለት ቀናት ይፋ እንደሆነው ቢኒሻንጉልን እንዲጠብቁ 10 ሺህ የሚሊሻ ሰራዊት ሰልጥኖ ለምረቃ እየተዘጋጀ ነው። ይህ ሃይል የየራሱን ቀበሌ መጠበቅ የሚችል ሲሆን ከሰላሳ ሺህ በላይ ጫካ የገቡ የጉሙዝ ብሄር አባላት ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰዋል። በሽፍቶቹ ሲተዳደሩ የነበሩ ቀበሌዎች 80 ከመቶ በአዲስ አደረጃጀት ተዋቅረዋል። እንደ ዜናው ከሆነ በቤኒሻንጉል የተጀመረው ሰላም የማስፈን ተግባር በቅርቡ ይጠናቀቃል።

ሌላው ፍርሃት በጋምቤላ በኩል ሲሆን መንግስት አስቀድሞ የተደራጀ የመከላከያ ተወርዋሪ ሜካናይዝድ ሃይል ያሰፈረ ቢሆንም በዛሬው እለት በርካታ የክልሉ ሚሊሻ በልዩ የኮማንዶ ሃይል ሰልጥኖ ተመርቋል። የክልሉ መሪ እንዳሉት ይህ ሃይል የክልሉን ድንበርም ሆነ አካባቢ የመጠበቅ አቅም አለው። በጋምቤላም ሆነ በቢኒሻንጉል የተሰራው ስራ መንግስት ትኩረቱን በሱዳን ድንበር ውጥረት ላይ ለማድረግ እንዲያስቸለው ታስቦ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

“የዓባይ ወንዝ መገደብ ያሰጋኝም፤ እንዲያውም በጎርፍ አደጋ ያትደገኛል” ስትል የነበረችው ሱዳን ዛሬ ላይ ” ሁለተኛው የውሃ ሙሌት ለህልውናዋ እንደሚያሰጋት ደጋግማ እያስታወቀችና ይህ ከሆነ ” ውርድ ከራስ” እያለች ነው። ግብጽም የሱዳንን የጦር መሪዎች እየቆሰቆሰችና እይገፋች ከአፍሪካ ህብረት አደራዳሪዎች ራሷን ለማግለል እየዛተች ነው።

ይህ በሚባልበት ሰዓት ላይ የውሃና መስኖ ሚኒስትሩ ከትናንት በስቲያ በይፋ ለዓለም ሁሉ መግለጫ በትነዋል። ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንዳሉት የግድቡ ሁለተኛ ደረጃ ሙሌት በተያዘለት እቅድ መሰረት ይቀጥላል። ኢትዮጵያ ማንንም ሳትጎዳ የምታካሄደውና እያንዳንዱ ዜጋ ከሚበላው ቆጥቦ እየገነባው ያለውን ግድብ አጠናቆ ለማስጨረስ መንግስት ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ለአልጃዚራ በቃለ ምልልሳቸው አስረግጠው ተናግረዋል። አያይዘውም ኢትዮጵያ በስምምነትና በንግግር ሁሉንም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ የማስኬድ የቆየ ጽኑ እምነት እንዳላት አመልክተዋል።

የድንበር ወረራው ዋና ዓላማና ጉዳይ የህዳሴው ግድብ ሁለተኛው ዙር ውሃ ሙሌት ለማስተጓጎል፣ ድርድሩ ላይ ጫና ለመፍጠርና ከግብጽ ጋር በስውር ( ነገር ግን በግልጽና በማስረጃ) ሲሰራ የነበረውን የትህንግ ሃይል ከተከበበት ይወጣ ዘንድ ለማመቻቸት ታስቦ እንደሆነ በጉዳዩ ዙሪያ በቂ መረጃ ያላቸው በተለያዩ ጊዜያት ሲገልጹ ነበር።

ይባስ ተብሎ ” አብዛኛው በድንበር አካባቢ ያለው የቤኒሻንጉል ክልል የሱዳን መሬት ነው፤ የህዳሴውም ግድብ ያለው በሱዳን መሬት ላይ ነው። ሱዳን እዛ ድረስ መሬቷን የመጠየቀ እቅድ አላት። ይህንንም በሃይል ተግባራዊ ታደርገዋለች” የሚል መረጃ በትህነግ ደጋፊዎች ዘንድ በሚሰማበት በአሁኑ ወቅት መንግስት ሁሉንም ጆሮ ዳባ ብሎ ” በቤኒሻንጉልም ሆነ በሱዳን ድንበር ያለው አለመረጋጋት የህዳሴው ግድብ ላይ ቅንጣት ታክል ጫና አያመጣም” በሚል ማስታወቁ መንግስት ልዩ ዝግጅት ላይ መሆኑንን የሚያሳይ እንደሆነ ምልክት አድረገው የወሰዱ አሉ።

አልፎ አልፎ መጠነኛ ግጭት ያለበት የኢትዮ ሱዳን ድንበር መቼና እንዴት ባለ እርምጃ እልባት ሊያገኝ እንደሚችል የበርካቶች ጥያቄ ቢሆንም ” ከብዙ ትዕግስት ውስጥ የምትወጣ ሃይል ሳታደቅ አትመለስም” ሲል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዳስገነዘቡት፣ ይህን የቆየና በሴራ ሲነከባበል የቆየው ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ለመስጠት ጊዜው የደረሰ ይመስላል። መቼ? ለሚለው ግን ፍንጭ የለም። ሁሉም ወገኖች የሚስማሙበት ጉዳይ ቢኖር ጫናው ከውስጥም ከውጭም ቀላል ያለመሆኑንን ነው።

የተቀነባበረ ዓለም ዓቀፍ የሚዲያ ዘመቻ የተከፈተባት ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ጫና ሲበዛ፣ ጠላት ሲያጋሳ ” ክፉ ጊዜን በህብረት” የሚለውን የአያቶች ብሂል በዘነጉ ልጆቿ ጭምር እየተለበለበች ነው። ትሀንግ በስልጣን ላይ እያለ በኢትዮጵያ ስምና በጀት ሲደራጅና ሲዘረጋ የነበረው መረብ ዛሬ አንድበቱ ኢትዮጵያን ለመብላት በሃሰት ዘመቻ በተነሳበት ወቅት ” ኢትዮጵያዊ ነን ” የሃይማኖት ሰዎች መሆናቸውን የሚገልጹ ምን እንደተከፈላቸው ባይታወቅም ኢትዮጵያ ላይ መዝመታቸው በርካቶችን ያሳዘነ ሆኗል። ” ደግነቱ” ያላሉ አቶ ሰለሞን የተባሉ የቴክሳስ ነዋሪ ” ደግነቱ በሚጮኸው ልክ ሰሚ የለም፤ ሕዝብ እየገባው ነው፤ ሁሉም መርዙን የሚተፋበት ቀን ደርሷል” እኚህ ሰው ብዙ ብለዋል። ሱዳን በውስጥ ቀውስና ዳቦ ጥያቄ አደገኛ ውጥረት ውስጥ እንዳለች ልብ ይሏል። ይህንኑ መሰረት ያድርጉ አያድርጉ ባይታወቅም ” ለውጥ በጠብመንጃ ብቻ አይመጣም” ሲሉ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት መናገራቸውም አይዘነጋም። እንደሚባለው ከሆነ የሱዳን የውስጥ ቀውስ የሚባባስ ነው።

እንግዲህ እንዲህ መሰሎቹ ሃሳቦችና አካሄዶች ባሉበት ሰብሰብ ሲደረጉ ኢትዮጵያ ጦርነት የምትገባበት ወቅት ዛሬ አይሆንም የሚሉ ይበረክታሉ። ነገር ግን ዘግጅቱ አለ። አዲስ አድማስ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደርን ጠቅሶ ከዚህ በታች ያለውን ነው የዘገበው።

ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር ላይ በፈጸመችው ወረራ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድረሱንና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር አልፎ በፈጸመው ወረራ በርካታ ገበሬዎች መፈናቀላቸውን ፣ሃብት ንብረታቸው መዘረፉንና የሞት ጉዳት ማጋጠሙን የተናገሩት አምባሳደሩ ሃገሪቱ ጦሯን በአፋጣኝ በወረራ ከያዘችው ግዛት የማታስወጣ  ከሆነ ኢትዮጵያ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ትገደዳለች ብለዋል፡፡

ሱዳን ኢትዮጵያ ላይ የፈፀመችው ወረራ ከህግም ሆነ  ሁለቱ ሃገራት ካላቸው የቆየ ጉርብትና አንጻር ታሪካዊ ስህተት መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ፤ በሁለቱ ሃገራት መካከል በ1972 የተፈረመውን የድንበር መርህ ስምምነት የጣሰ ድርጊት ነው ብለዋል።

ሱዳን  ድርጊቱን የፈጸመችው  መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ህግ የማስከበር ተግባር ላይ መሆኑን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እንደሆነ ያስታወሱት አምባሳደሩ፤ ይህም ወዳጅን ከጀርባ የመውጋት ድርጊት ነው ሲሉ ነቅፈዋል፡፡
የሃገሪቱ ሰራዊት በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች በአፋጣኝ ለቆ እንዲወጣና ድርድር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ እየጠየቀ ሲሆን የሱዳን መንግስት በበኩሉ፤ የያዝኩትን አለቅም በሚል አቋሙ ፀንቷል፡

Exit mobile version