Site icon ETHIO12.COM

ከአዲስ አበባ የመሬት ዘረፋ ጋር በተያያዘ ” አንቱ” የተባሉ ሊጠየቁ ነው፤ አቃቤ ህግ ክስ እያደራጀ መሆኑ ተሰማ፤ ውክልና መሬት ተዘርፏል

በአዲስ አበባ ተፈጸመ የተባለውን ህገ ወጥ የመሬት ንግድ ያስጠናው የአዲስ አበባ አስተዳደር ጥናቱን ከመረጃ ጋር አያይዞ ለፌደራል አቃቤ ህግ እንደላከለት ማስታወቁ ይታወሳል። የኢትዮ12 መረጃ አቀባዮች እንዳሉት በማጣራቱ እጃቸው አለበት ተብሎ የሰነድ ማስረጃ ከተገኘባቸው መካከል ” አንቱ” የተባሉ ተገኝተዋል። የሞተ ኢንቨስተር ወኪል በመምሰል ሰነድ አዘጋጅተው መሬት የቸበቸቡ አሉ።

በተለያዩ ግንኙነቶች ከህግ ውጪ የተወሰዱና የግል ንብረት ሆነው ለሌሎች የተላለፈ መሬትና በስፋት የተቸበቸበ የኮንዶሚኒየም ቤት አስመልክቶ አቃቤ ህግ መረጃ በማጣራት ክስ እያደራጀ መሆኑ ታውቋል።

በመሬት ንግድ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ የሚታወቁ ሰዎች መኖራቸውን የገለጹት የዜናው ባለቤቶች የቀድሞ ከንቲባ ታከለ ኡማ ምርመራ ከሚደረግባቸው መካከል አንዱ ናቸው። ምርመራው ያስከስ እንደሆነ ለተጠየቁት ” አንቱ የተባሉ አሉበት” ከማለት ውጪ ዝርዝር ለመናገር ጊዜው እንዳልሆነ የዜናው ባለበኤቶች ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ እጅግ የተደራጀ የመሬት ዘረፋ የተከናወነ ሲሆን በቅርቡ በሞተ የውጭ አገር ባለሃብት ላይ ውክልና በማውጣት ተቧድነው መሬት የዘረፉ ከፈቀደላቸው ሃላፊ ጋር ወደ ህግ እንደሚቀርቡ ከምንጮቹ ለማረጋገጥ ተችሏል። መሰወር እንዳይኖር ክትትል እየተደረገ መሆኑም ታውቋል።

አቃቤ ህግ በርካታ ጉዳዮች ስላሉት የጊዜ ችግር አጋጥሞት እንጂ ጉዳዩ የሚጓተት እንዳልነበር ምንጮቹ ተናግረዋል። አንድ የአዲስ አበባ ብልጽግና አመራ ጉዳዩን እንደሚያውቁ፣ ነገር ግን ዝርዝር ነገር ለማለት እንደሚቸገሩ እግረመንገዳቸውን ስለሌላ ጉዳይ ሲናገሩ መጠቆማቸውን ሌላ ምንጭ ተናግረዋል።

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባን የተረከቡት ከአቶ ታከለ ኡማ ሲሆን፣የፌደራል አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት ደግሞ በአቶ ብረሃኑ ጸጋዬ ምትክ መሆኑ ይታወሳል። አቶ ታከለና አቶ ብረሃኑ ወይዘሮ አዳነች የባንክ አካውንት ውስጥ ከፍተኛ ገንዘብ መግባቱን ሰነድ ይዘው በድርጅት ጉባኤ አቅርበው ሲያሳጡ የነበሩ መሆናቸውን የኢትዮ12 ታማኝ የድርጅቱ ምንጮች ቀደም ብለው ጠቁመው ነበር።

አዳነች አቤቤ ሁሉንም አልፈውና አሸንፈው ዛሬ አዲስ አበባን እየመሩ መሆኑ የፍትህ ሂደቱ እንዲታደፍ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ስለ ውስጥ ፍትጊያው የሚያውቁ ይናገራሉ።

Exit mobile version