የተለያዩ የስራ ድርሻ፣አድራሻ፣ ስምና ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀምና በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ግለሰቡ ስንታየሁ ቢርጉ ካየና፣ ስንታየሁ ተመስጌን አበራና ስንታየሁ ደምሴ የተባሉ ስሞችን በመጠቀም የማጭበርበር ተግባር ሲፈፅም መቆየቱን በፋይናንስና ንግድ ነክ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት የህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ምርመራ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጥበቡ ገልፀዋል፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት፣ማታለልና በባለስልጣን ስም መነገድ ግለሰቡ ከተጠረጠረባቸው ወንጀሎች መካከል ጥቂቶቹ መሆናቸውን አቶ ሽመልስ ተናግረዋል፡፡
በሀሰተኛ መታወቂያው ላይ የፕሮቪዥን ኃላፊ እንደሆነ የሚገልጽ ሰነድ በማዘጋጀት ሲገለገልበት መቆየቱንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የስራ ድርሻው መርማሪ መሆኑን የሚገልጽ ሐሰተኛ መታወቂያ አስወጥቶ ሲገለገል መቆየቱን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ እንደደረሰበት ተገልጿል፡፡
በወንጀል ተጠርጣሪ ግለሰቦች ላይ ብርበራ ሲደረግ እንደ ጠቋሚና ተባባሪ ሆኖ በመቅረብ የከፍተኛ መንግስት ባለስልጣናትን ስም እየጠራ ጉቦ የሚጠይቅ መሆኑ መገለፁን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ተክለብርሐን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅት በሚያዝያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በመሄድ ድርጅታቹ ሊዘጋ ነው ወይም ሊታገድ ነው ብሎ በማስፈራራት 500 ሺህ ብር ጉቦ መቀበሉንና በህገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብም ለማሸሽ ሲል ወደ የባለቤቱ የሂሳብ ደብተር ሲያስተላልፍ እንደነበር ፖሊስ በማስረጃ ማረጋገጥ መቻሉን አቶ ሽመልስ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ከቴሌ ኮሙዩኒኬሽን የእሱ ባልሆነና ስንታየሁ ደምሴ በሚል ስም የሐሰተኛ መታወቂያ ሲም ካርድ እያወጣ ሲጠቀም መቆየቱን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ያረጋገጠ ሲሆን ግለሰቡ ሲጠቀምባቸው የነበረው መታወቂያዎች ሁሉ ሐሰተኛ መሆናቸውን ፖሊስ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡም ተገልጿል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ በግለሰቡ ላይ ባደረገው ክትትል ግለሰቡን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሲሆን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮም የክስ መዝገቡን ለሚመለከተው አቃቤ ህግ እንደላከ አስታውቋል፡፡
fbc
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው