Site icon ETHIO12.COM

በአንድ ሳምንት ብቻ ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በአንድ ሳምንት ብቻ ተያዙከጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት አንድ ሳምንት ውሰጥ ብቻ 33 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ፣ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ 25 ተሽከርካሪዎች እና 7 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ይገኛል ብሏል።29 ሚሊዮን 66ሺህ 239 ብር እንደሚያወጡ ግምት ዋጋ የወጣላቸው ዕቃዎች የገቢ ኮንትሮባንድ ሲሆኑ፣ 4 ሚሊዮን 715 ሺህ 942 ብር የሚገመቱ ደግሞ የወጪ ኮንትሮባንድ መሆናቸው ተገልጿል።በአጠቃላይ 33 ሚሊዮን 782 ሺህ 181 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢ እና የወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በአንድ ሳምንት በተለያዩ የጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች የተያዙ ናቸው ተብሏል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተለያዩ ሀገራት የመገበያያ ገንዘብ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጥ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ መድኃኒት፣ መለዋወጫ፣ አትክልት፣ የተለያዩ የጦር መሣሪያ ጥይቶች፣ ጫት፣ ቡና፣ ሺሻ እና እሁ ማጣበቂያ እንደሆኑም ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል።

OBN

Exit mobile version