Site icon ETHIO12.COM

አራዊት ጤንነቱ ታውኳል፤ ወደ አገር ቤት ለመመለስ አብነት ገብረመስቀል ምላሹ እየተጠበቀ ነው

“በሥዕል የተደገፈውን ግለሰብ ለመለየት ACPD ን መርዳት ይችላሉ?” ሲል The Arlington County Police Department  በፌስ ቡክ ገጹ ማስታወቂያ የበተነው ለአቶ ደምሴ ለማ ወልደየስ ወይም / አራዊት / በሚል ስያሜ ለሚታወቀው ተፈላጊ ነው።

ፖሊስ ደምሰው የተሰወረበትን ሰዓትና ጊዜ ጠቅሶ ” እሱ በአእምሮ በሽታ ወይም በሌላ የእውቀት እክል እየተሰቃየ ሊሆን ይችላል” በማለት የጤና እክል ላይ እንደሚገኝ ጠቁሞ “ዕድሜው ከ55-65 የሚመስል፣ ኢትዮጵያዊ  ፣ አማርኛ የሚናገር ፣ ግራጫማ ሹራብ ፣ ቀይ ጃኬት እና ጥቁር ካፖርት ለብሷል ፣ ሰማያዊ የአትሌቲክስ ሱሪ ወዘተ  ለብሷል፣ ቀይ ባርኔጣ አድርጓል” የሚል የአፋልጉኝ ምልክት ይሰጣል። ከዛም የድንገተኛ ስልክ በማስቀመጠ ያዩት ሰዎች መረጃ እንዲሰጡ ይጠይቃል።

ይህ ከሆነ በሁዋላ ደምሰው መገኘቱን  FINAL: The gentleman has been identified and his family has been located. Thank you to all who shared to assist with this case! ሲል አፋልጉኝ ያለው ክፍል በተመሳሳይ ገጹ አስታውቋል።

ደምሰው / አራዊት ወደ አሜሪካ የሄደው በድንገት ነበር። የሄደውም የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት አቶ አማረ አረጋዊ ላይ የግድያ ሙከራ ከተደረገ በሁዋላ ግድያ ሞካሪዎቹ ሲያዙ አራዊት በዛው ምሽት ወደ አሜሪካ እንዲያቀና ተደርጓል።

2020 አሜሪካ በሄድኩበት ጊዜ በጥቆማ ሜሪላንድ ቴራሚዞ ካፌ አካባቢ አግኝቸው ነበር። በወቅቱ መልካም ጤንነት ላይ ይገኝ ነበር። ረስቶኝ ስለነበር ማንነቴን ነግሬው አሜሪካ ስለሚኖርበት ምክንያት ጠይቄው ነበር። ቁጭት አለበት። እዛ እንደተጣለ አድርጎ ያስባል። በራሱ ፍላጎት አገር ቤት መግባት እንደማይችል፣ ብዙም አዲም ባይሆን አንዳንድ ጉዳዮች አጫወተኝ።

የአሜሪካ አካሄዴ እሱንም ለማግኘት ጭምር በመሆኑ፣ ካገነሁት በሁዋላ አዘንኩ። ምንም የማያውቅ መሆኑንን ስረዳ እንዴት እንደተጫወቱበት ተረዳሁ። አገር ቤት እንደሚፈለግ ከማወቁ በቀር እሱ መራው በተባለው ወንጀል ዙሪያ ሁሌም መመሪያ ተቀባይ ነው።

እሱ ዘሪሁን የሚባል ወጠምሻ መልምሎ አቶ አማረ ላይ ግድያ ሲሞከር  ደምሰው እዛው አካባቢ ዲኤች ገዳ ህንጻ ሼቭሮሌት ውስጥ ቁጭ ብሎ ይመለከት ነበር። ገዳዮቹ የተባሉትን አድርገው ሲሸሹ አንደኛው በህዝብ ትብብር ተያዘ። የመጡባት ታክሲ እንከን ገጥሟት አልሄድም በማለቷ ሁለቱ ሲያመልጡ  አንዱ የመሮጥ ችግር ያለበት ስለነበር ተያዘ። በሱ ጥቆማ ሌሎቹ በ24 ሰዓት ተያዙ።

ምርመራውን የሚመሩት የወቅቱ የፖሊስ ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁ ስለነበሩ በየእለቱ አገኛቸው ነበር። ምርመራው የተጠናቀቀው አራዊት ላይ ነው። አራዊት ተይዞ ከመጣ ማን ገቢ እንደሚሆን ይታወቃል። ስለዚህ ጉዳዩ ተድበሰበሰ። በኢንተር ፖል አማካይነት አራዊትን ከአሜሪካ ማስመጣት እየተቻለ ዝም ተባለ። አደጋው ሲደርስ አያት ሆስፒታል ሲፎክሩ የነነብሩት የህወሃት ታላላቅ ሰዎች ምን እንደነካቸው በግልጽ ባይታወቅም ዛቻቸው ረገበ። ብዙ ታሪክ አለው።

ደምሰው/ አራዊት የመለመለው ዘሪሁን ወደ ሱዳን ተላከ። ከሱዳን ወደ ዱባይ ማቅናቱ ይነገራል። ሶስቱን ግን ዝዋይ ማረሚያ ቤት በተደጋጋሚ አግኝቻቸዋለሁ። የመርካቶ ጭድ ተራ ልጆች ናቸው። ሞገስ የሚባለው ጎረምሳ ሶስት ጊዜ አስቤው ሳይሆን በተዓምር እንዳመለጥኩዋቸው ነገረኝ። ሶስቱንም ቀናት አስታወሰኝ። አንዴ ፖስታ ቤት ውስጥ፣ አንዴ ሰንጋተራ ኤደን ፐብ አተገብና፣ ፒያሳ ኖቪስ ከወዳጄ ናምሩድ ጋር ለሰርጌ ሽቶ ለገዛ ስል ነበር ለያስወግዱኝ የመጡት።

ለፖሊስ በሰጡት ማስረጃ ይህንኑ አረጋግጠዋል። አቶ ውርቅነህ ገበየሁ ክሱን ባያስቀጥሉም ከዚያ በሁዋላ ጥበቃ መድበውልኝ ነበር። በሄድኩበት ሁሉ የሚጠብቀኝ ነበር። እድሜ ለኦሮሚያ የማከብራቸው ሃላፊዎችና ዝና የማይፈልጉ ሃብታሞች እስካሁን ሳልሞት ልጄን ማሳደግ ችያለሁ።

እንደ ሰው አራዊት አንጀቴን በልቶታል። ቀደም ሲል ሲከፈለው የነበረው ገንዘብ ተቀንሶበት ይነጫነጭ ነበር። አንድ ወቅት ላይ ወደ አገር ቤት በመምጣት አሳስራቸዋለሁ ይል እንደነበር አውቃለሁ። ዛሬ ከሚኖርበት አካባቢ እንደነገሩኝ ሰሞኑንን ” ሰዎቹን ይዘሃቸው ና ብለውኛል” እያለ ካፊቴሪያ ያሉ ወግኖችን ያናግር ነበር። ” ወዴት ሄዱ” እያለም ይጠይቃል።

ይህንን ያዩ ወገኖች ብር አዋጥተው ወደ አገር ቤት ሊልኩት አስበው አቶ አብነት መፍቀድ አለባቸው ተብሏል። ይህንን ያሉት ወገኖች መልሱን እንዳገኙ የዜግነት ስራ ለመስራት ፈቃደኞች ናቸው። ይህግ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ!! አቶ አብነት ፈቃድ መስጠት ያለባቸው አቶ ወርቅነህ በተኙበት ያልተዘጋ ፋይል ስማቸው ከአራዊት ቀጥሎ ስለሚገኝ ነው።

አሁን አራዊት ጤናው ተዛንፏል። እና ወንጀሉ ሊዳፈን ነው? ይህ ያስጨንቀኛል። የኦሮሚያ ብልጽግና ሰዎች ከላይ እስከታች፣ እኔም ከአገር እንድወጣ የረዱኝ በሙሉ ጉዳዩን ያውቁታል። የዚህ ሁሉ ወንጀል መነሻ ምክንያትም ከነሱ የተሰወረ አይደለም። እናም ይህንን ከጻፍኩ በሁዋላ ዝርዝር ማስረጃውን አስቀድሜ ለላኩላቸው ወገኖች ሌላ ማስታወሻ እልካለሁ። ፍትህ የናፈቃቸው የህግ ባለሙያዎች ቢናገሩኝ ለመተባበር ዝግጁ ነኝ። ካልሆነም ህዝብ እንዲፈርድ የማወቀውን ይፋ አድረጋለሁ። አቶ አብነትም ሆነ ማንም እውነት በመናገሬ ቅር እንዳይሰኙ ከወዲሁ እየይቃለሁ።

ደምሰው አቶ አበነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስልኩን እንደማያነሱለት፣ ላግኛቸው ቢልም እንዳልቻለ፤ ሼክ መሐመድ ያሉበት ሁኔታ ለማግኘት እንዳላስቻለው ያማርር እንደነበር ባር አካባቢ ብዙ ብር ሲመነዝር የሚያውቁት ምስክርነት ሰጥተዋል።

የተለያዩ ሚዲያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ በቂ መረጃ ሳትይዙ የተዛባ መረጃ እንዳትሰጡ እማጸናለሁ። የምትፈልጉት መረጃ ካለ ለማካፈል ዝግጁ ነኝ። ከዚህ ውጭ ግን ሃብታምና የህባታም አለቅላቂዎችን በመስማት ተሳስታችሁ እንዳትሳሳቱ አደራ እላለሁ። ሰዎቹ እጃቸው እጅግ ረጅም በመሆኑ ጥንቃቆእ ግድ ነው። ዮፍታዬ ሞቷል። ኤፍሬም ስለ ጊዮርጊስ መጥፎ አስተያየት ሰጠ ተብሎ ተቀጥቅጧል። ወንጀል ካሰሩዋቸው በሁዋላ በየስፋራው የተጣሉ አሉ። የሴቶች ጉዳይ አለ። የቡና ስፖርት ክለብ አመራሮችን ” ቅንጅት ናቸው” በሚል ማስበላት ነበር። ብዙ ጉድ አለና ሚዲያው ይጠንቀቅ፤ የምርመራ ስራ ይስራና ጉዳዩን ከስር ያድማው።

Exit mobile version