አብነት ገብረመስቀል ” አፈርጠዋለሁ” ማለታቸው ተሰማ

ላለፉት ሰላሳ አምስት ዓመታት ከሼኽ ሁሴን መሐመድ አላሙዲ ጋር አብረው የዘለቁት አቶ አብነት ገብረመስቀል ” ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን” ማለታቸው ተሰማ። የእሳቸውን ስም የማንጠልጠሉ ጉዳይ የማይቆም ከሆነ በርካታ ጉዶችን ሊያፈርጡ ይችላሉ።

በሸራተን ውስጥ ሲፈተፈት ለነበረው ማናቸውም ጉዳዮች ሙሉ እውቅናና መረጃ ያላቸው፣ በበርካታዎቹ ጉዳዮች ላይ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ተሳታፊ እንደነበሩ ለመካድ አይቻልም። ለዚህም ይመስላል አቶ አብነት ነገሮች መስመራቸውን የሚያልፉ ከሆነ በርካታ ጉዳዮችን አደባባይ እንደሚያወጡ ለሚቃረኑዋቸው ወገኖች ወዳጅ ለሆኑ ነግረዋል።

ዝግጅት ክፍላችን አቶ አብነት ምን ምን ጉዳዮችን ይፋ እንደሚያደረጉ የገለጹ ቢሆንም ለጊዜው ከማተም ተቆጥበናል። አቶ አብነት በሰላሳ አምስት ዓመት ቆይታቸው በርካቶችን ሲያርቁም ጥቂት የማይባሉትን ማቅረባቸው የሚታወቅ ነው። ያራቁዋቸው የሚጠሏቸውን ያህል ያቀረቧቸው ይወዱዋቸዋል። አብነት የሼኽ መሀመድ ወዳጅና ወኪል ሆነ ረዥም ዓመት የዘለቁ ብቸኛ ሰው ናቸው። በዚህ ረዥም ቆይታቸው ሰፊ ሃብት በሼር ስም አፍርተዋል።

ከሚቃረኗቸው እንደሚሰማው የአገልግሎት 3 ቢሊዮን ገደማ ጠይቀዋል። ከዚህም በላይ መለያየቱ በዚሁ ከጸና ሰፊ ሃብት በሽርክናና በከፍተኛ አክሲዮን ወደ እሳቸው ስለሚዞር ምን አልባትም ሽምግላናው ነብስ ሊዘራ እንደሚችል ግምት ያላቸው እየተናገሩ ነው።

ወደ መንግስት የመሬት ባንክ የገባን የባለሃብቱን መሬት በድርድር ለግል ወስደው በመሸጣቸውና የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ከሚደሮክ ወስደው በልጃቸው ስም ለማቋቋም ጫፍ መድረሳቸው ተዳምሮ ” በዕምነት ማጉደል” ከነበሩበት ሃላፊነት እንዲነሱ፣ እንዲሁም የነበራቸው ሙሉ ውክልና እንዲነሳ መደረጉ ይታወሳል።

አቶ አብነት በነብስ ማጥፋት የነበረባቸውን ክስ ክፍት ቢሆንም፣ አቶ ደምሰው / አራዊት/ አዲስ አበባ ገብቶ ሳለ ጉዳዩን ተበዳዮ በዝምታ ማለፋቸው ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል። ዝግጅት ክፍላችን በዚህ ዙሪያ ሰፊ ሪፖርት የሚያቀርብ ይሆናል። ጋዜጠኛ አርአያ አሜሪካ ሆኖ እንዳጣራውና እንዳረጋገጠው አራዊት አዲስ አበባ ነው። አራዊት መታመሙ በተሰማና ጥፍቶ መገኘቱን ፖሊስ ይፋ ሲያደረግ አቶ አማረ አረጋዊ ” ወደ አገር ቤት ቢመጣ እረዳዋለሁ” ማለታቸው በማህበራዊ ሚዲያ ተዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።

አቶ አማራ ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት አውጥተው ለወላጆች ስብሰባ ተመልሰው ወደ ትምህርት ቤቱ ሂደው ሲወጡ ቀኑንን ሙሉ ሲከታተሏቸው በነበሩ ሰዎች ድንገት አናታቸውን በብረት ተመተው ራሳቸውን ስተው ነበር። ወዲያውም ሃያት ሆስፒታል ሲገቡ፣ እንዳይተርፉ ሆስፒታሉ ድረስ በመግባት ሌላ የግድያ ሙከራና የሆስፒታሉን ሰራተኞች በስልክ እርዳታ እንዳይሰጡ ማስፈራራት ሲደረግ የዚህ ዜና ዘጋቢ በአካል እዛው ነበር።

የግድያ ሙከራውን ያደረጉ በመጡበት የኮንትራት ታክሲ ለማምለጥ ሲሞክሩ መኪናዋ ሞተሯ አልነሳም በማለቱ አንዱን በስፍራው የነበረ ህዝብ ይዞ ለፖሊስ ካስረከበው በሁዋላ፣ የተቀሩት ሁለቱ ወንጀለኞች በሰዓታት ውስጥ ሊያዙ ችለዋል። በበቂ ደረጃ ቃላቸውን ለፖሊስና ለፍርድ ቤት ሰጥተዋል። ሰባት ሰባት ዓመት ተፈርዶባቸው ዝዋይ ማረሚያ ቤት ነበሩ።

Leave a Reply