የሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለቤትና ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ አዲስ በሰጡት ሹመት የሚድሮክን ዋና ስራ አስፈፃሚነ የሆኑት አቶ አብነት ገብረመስቀልን ከኮቪድ በጠና ታመው የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ማገገማቸው ተገለጸ።
ከሚስዶክ በተጨማሪ በኮንስክትራክሽን፣ በሆቴሎች እና በሪል ስቴት ዘርፍ ያሉትን ኩባንያዎች በሙሉ እንዲመሩና ፋርማኪዩርን እየመሩ እንዲቀጥሉ ስልጣን የተሰጣቸው አቶ አብነት የታመሙት በኮቪድ 19 ቫይረስ ተያዘው ነበር። የሸራተን ዜና አቀባያችን እንዳሉን አቶ አብነት በጸና ታመው ነበር። መተንፈስ ተስኗቸው የከፋ ደረጃ በመድረሳቸው ቤተሰቦቻቸውና የሚወዷቸው እጅግ ተደናግጠው ሰንብተው ነበር።
በሸራተን ሆቴል አንድ ክፍል ውስጥ በመተንፈሻ መሳሪያ እገዛና እጅግ ጥብቅ ክትትል እየተደረገላቸው ያገገሙት አቶ አብነት አሁን እዛው ሸራተን ታለው ቢሯቸው ስራቸውን መስራት መጀመራቸውን የዜናው ምንጭ አስታውቀዋል።
” ደንግጠን ነበር” ያሉት ወዳጃቸው እንደነገሩን ሁሉም አልፎ ዛሬ እጅግ በመልካም ሁኔታ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። አቶ አብነት ሸራተን ውስጥ በልዩ ክብካቤ ሲታከሙ መቆየታቸው በድብቅ የተያዘ ቢሆንም ሰራተኞች መረጃ ደርሷቸው እንደነበር ኢትዮ12 አረጋግጣለች። ወዳጃቸው አክለው አቶ አብነት በጠና መታመማቸውን የሰሙና ስጋት ገብቷቸው የነበሩ ወገኖችና በጸሎት ሲተጉ ለነበሩ ክፍሎች ትልቅ ዜና እንደሆነ ገልጸዋል።
አቶ አብነት ደምሰው ለማ ወይም በተለምዶ አራዊት ጤናው በመታወኩ ወገን ወዳዶች ወደ አገር ቤት እንዲመለስ ለማድረግ የሳቸውን ፈቃድ ለመጠየቅ መዘጋጀታቸውን ጠቅሰን ዜና መስራታችን የሚታወስ ነው።
ፎቶ ካፒታል ጋዜጣ የሸገር ዳቦ ፕሮጀክት ምርቃት ወቅት የተነሳ
Latest stories
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው