Site icon ETHIO12.COM

Breaking news – የሞኝ ብልጠት ይሆን?ልዩ ሀይላችን ድሉን ሱዳን ላይ ደገመው!

በቅርቡ የሱዳን ጦር ይዞት የነበረውን የአል-ፋሻቃ ድንበር መሬት የአማራ ሚሊሻ እና ፋኖ ከመከላከያ ጋር በመሆን እንደገና ተቆጣጥረውታል:: አማራ ተራራ ነው:: ተራራን ካልገፋኸው አይገፋህም ለመግፋት ብትሞክርም ትርፉ ድካም እና ውድቀት ነው።

የሱዳን መከላከያ ሰራዊት በማን አለብኝነት የአማራን መሬት ወረረ፣ ቀጥሎም የአማራን ንብረት አወደመ። ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል ሚሊሻ እና ፋኖ ከሃገር መከታው መከላከያ ጋር በመሆን ከህወሓት ያልተማረውን የሱዳን መከላከያ በሚገባው ቋንቋ አናግሮ በርካታ መኪኖችን ነጥቋል፣ ብዙዎችንም ማርኳል፣ ከፊሎቹም ህይዎታቸው ሲያልፍ የተወሰኑት እግሬ አውጭኝ ብለው በመኪና መጥተው በእግራቸው ፈርጥጠዋል።

የአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ በየትኛውም ግዳጅ የላቀ ውጤት ያስመዘግባል፣ አሁንም ይህ ድል ብርቁ ያልሆነው ልዩ ሃይል ሚሊሻ እና ፋኖ ለቀጣይ ግዳጅ ዝግጅቱን ጨርሶ የመጨረሻዎ ፊሽካ እስክትነፋለት በመጠባበቅ ለይ ይገኛል!

በመጨረሻ የሰይጣን አመለካከት ያላችሁ ከዚህ አረመኔያዊ ተግባር ካልተቆጠባችሁ የመልስ ምቱ ከባድ ነው። በአለም ታሪክ የተጨቆነ ህዝብ ተሸንፎ አያውቅም!

እየሞተ የሚፈራ ጀግና ህዝብ ሲኖረህ የትኛውም ትግል ሊያስፈራህ አይችልም!!


Exit mobile version