Site icon ETHIO12.COM

ጄኔራል ዮሐንስ ገብረ መስቀል – በትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ግብረሃይል መሪ ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት ለትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ ግብረሃይል መሪነት ጄነራል ዮሐንስ ገብረ መስቀል መሾማቸውን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ዛሬ ከክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ግበረሃይልና አስተዳደር ጋር ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ላይ ስለተነሱት ጉዳዮች ዝርዝር ባይጠቅሱም በክልሉ ስለተሰሩ ስራዎችና ቀጣይ ተጋባራት ውይይት መደረጉን በማህበራዊ ገጻቸው አመላክተዋል። ይህን በጠቀሱበት ወቅት ነው ጀነራሉ መሾማቸውን ያመለከቱት።

“… ከዛሬ የካቲት 24፣ 2013 ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይሉ በጄኔራል ዮሐንስ ገብረ መስቀል ተስፋ ማርያም አመራር በመታገዝ የማረጋጋት እና መልሶ የመገንባት ሥራውን ይቀጥላል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ማስታወቃቸውን ተከትሎ ” የተደረገው ውይይት ጠንካራና በርካታ ጉዳዮችን በደካማ አፈጻጸም ገምግሟል” የሚል መረጃ አግኝተናል።

የአገር መከላከያ ኤታምዦር ሹም ብርሃኑ ጁላንና ምክትላቸው ሌ/ጀኔራል አበበው ታደሰ፣ ዶክተር አብረሃ በላይና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ዶክተር ሙሉ በሚታዩበት ፎቶ ታግዞ የቀረበው ዜና ውስንማ ቁልፍ ሰዎች የተገኙበት ከመሆኑም በላይ፣ ለነራል ዮሐንስ ወደ ሃላፊነት እንደመጡ መገለጹ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካሄድ ደካማ መሆኑንን አመላካች ሆኗል።


Exit mobile version