Site icon ETHIO12.COM

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ወይዘሮ ሕርቲ ምህረተአብ እና የክልሉ መንግስት አማካሪ የነበሩት ወልደጊዮርጊስ ደስታ፣ እንዲሁም በእነ አባይ ወልዱ የክስ መዝገብ ላይ ከሚገኙ ተከሳሾች ውስጥ አምደማርያም ተፈራ በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ወሰነ፡፡

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ቀዳሚ ምርመራ እስከሚሰማ ድረስ በሰርቪስ ማረፊያ እንዲቆዩ ተወስኗል፡፡

በእነ አባይ ወልዱ መዝገብ 9 ሰዎች ቀዳሚ ምርመራ ቀርቦባቸዋል፤ ቀዳሚ ምርመራ እስከሚሰማ ድረስ ማረሚያ ይቆዩ ብሎ ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ መፍቀዱን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወይዘሮ ሙሉ ገብረእዝግአብሔር በወንጀል ስለሚፈለጉ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

Exit mobile version