Site icon ETHIO12.COM

መቀሌ ህገ-ወጥ የኢትዮጵያ ብርና የኤርትራ ናቅፋ ሲያትሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የህወሓት ቡድን ተላላኪዎች ሀሰተኛ ገንዘቦችን በማሰራጨት ህዝቡን ተጎጂ ለማድረግና ኢኮኖሚውን ለማናጋት እየሰሩ መሆኑን የሰሜን ዕዝ የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ተናገሩ። ህጋዊ ንግድ ፈቃድን ከላላ በማድረግ ሕገ-ወጥ የኢትዮጵያ ብር፤ የኤርትራ ናቅፋ እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦችን በማተም ህረተሰቡን የማሳሳትና የአገሪቱን ኢኮኖሚ የማናጋት ስራ ሲሰሩ እንደነበር አመልክተዋል።

ከሰሞኑ የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ጸጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል በመቀሌ ከተማ ህገ-ወጥ ገንዘብ ሲያትሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

የሰሜን ዕዝ የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ካሳ መላኩ እንዳሉት ሕገ-ወጦቹ ከ570 ሺህ ብር በላይ ተመሳስሎ የተሰራ ብር በማተም ወደ ህብረተሰቡ ለማሰራጨት ሲያዘጋጁ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።በዚሁ ወቅትም በርካታ ገንዝብ ወደ ሁመራ፣ የድንበር አካባቢና ሌሎች ቦታዎች ያሰራጩ በመሆኑ ህብረተሰቡ የገንዘብ ልውውጥ ሲያደርግ ወይም ሲገበያይ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ግለሰቦቹ ህጋዊ ንግድ ፈቃድን ከላላ በማድረግ ሕገ-ወጥ የኢትዮጵያ ብር፤ የኤርትራ ናቅፋ እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦችን በማተም ህረተሰቡን የማሳሳትና የአገሪቱን ኢኮኖሚ የማናጋት ስራ ሲሰሩ እንደነበር አመልክተዋል።በአሁኑ ወቅት የሕወሓት ቡድንና ተላላኪዎቹ በለመዱት ሕገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል ያሉት ሃላፊው ግለሰቦቹ ህገ- ወጥ ገንዘቦችን ከማተም በተጨማሪ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች ማሕተሞች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡የሁመራና የአካባቢው የቀበሌ መታወቂያና ተመሳስለው የተሰሩ ህገወጥ የመታወቂያ ወረቀቶችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሰዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ህገ-ወጥ ገንዘቦቹን በአማራና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎችና በሱዳንና ኤርትራ ድንበር አካባቢዎች ማሰራጨታቸውን ተናግረዋል።እንደ ኢዜአ ዘገባ ኮሎኔል ካሳ መላኩ ህገ-ወጥ ገንዘቦቹን ወደ ህብረተሰቡ ለማሰራጨትም ትብብር የሚያደርጉ የተወሰኑ የግል ባንኮች መኖራቸውን ጠቁመው በነዚህ አካላት ላይም የጸጥታ አካላት ክትትል እያደረጉ መሆኑን አስረድተዋል።

Via – FBC

Exit mobile version