Site icon ETHIO12.COM

“የዓለም አቀፍ ተቋማትና የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት እየለዘበ ነው ” – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

መንግስት፤ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እያደረጉ በሚገኘው ጥረት ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አንዳንድ ሀገራት በኢትዮጵያ ጉዳይ ያላቸው ጣልቃ ገብነት ለዘብ ማለቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የፌዴራል መንግስት፤ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በያሉበት እውነታውን ለማሳወቅ ባደረጉት ጥረት ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ አሜሪካ እና ምዕራባውያኑ ለዘብ ያለ መግለጫ እንዲያወጡ አግዟል።

ከትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ መጀመሪያ አካባቢ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፤ አንዱን የኢትዮጵያ ክፍል ከሌላው ጋር የማፋለስ አቅጣጫዎች እንደነበሩ ያመለከቱት አምባሳደር ዲና ፣ መንግስት ዓለም አቀፍ ተቋማት ለሚጠይቋቸው ጉዳዮች ምላሽ በመስጠቱ ፣ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ሀገር የሰብአዊ እርዳታውን በተመለከተ እውነታውን እያሳወቁ በመሆናቸው አሉታዊ ሃሳቦችን እና የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነቶች እየተቀየሩ መምጣታቸውን አስታውቀዋል ።

በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በዓለም አቀፍ ተቋማት እና በምዕራባውያን ዘንድ ውዥንብሮች ነበሩ።

በዚህም ምክንያት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆነ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኩል አሜሪካ እና ምዕራባውያን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት አሳይተዋል ብለዋል።

ኢ ፕ ድ

Exit mobile version