ETHIO12.COM

በርካታ የትህነግ መኮንኖች ተማረኩ፤ አቶ ጌታቸው መሞታቸው ይፋ ሆነ፤ወደ አማራ ክልል የሸሸ የትህነግ ሃይል ተቀጨ

ጦርነቱ ያለጊዜው እንዲጀመር ጫና በመፍጠራቸው ከሚወቀሱት የትህነግ ባለስልጣናት መካከል አንዱ ናቸው የሚባሉት አቶ ጌታቸው አሰፋ በጠና መታመማቸውን ለትህነግ የውጭ አመራር ቤተሰብ ቅርብ የሆኑ የመረጃ ሰው ጠቅሰን ባለፈው ሳምንት ዘግበን ነበር። ዛሬ ኢሳት የመከላከያ ምንጮቹን ጠቅሶ የፈጣሪ ሞት መሞታቸውን ይፋ አድርጓል። አቶ ስብሃት ሲያዙ የትግል አጋራቸው በህይወት ይኖራል ብለው እንደማያስቡ ተናግረው ነበር።

ኢሳት እንዳለው አቶ አሰፋ ህመማቸው ጠንቶባቸው ህይወታቸው እንዳለፈና ሉኪያ በሚባል ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ፍትሃት ተደርጎላቸው የቀብር ስነ ስርዓታቸው ተፈጽሟል። በጠና ከታመሙ የቆዩት አቶ ጌታቸው እንደ ልባቸው መላወስ ስለማይችሉ ሃይላቸው በተንቀሳቀሰ ቁጥር በቃሬዛ በሰው ሃይልና በጋማ ከብት ይጓጓዙ እንደነበር ነው እማኞቹ የተናገሩት።

አቶ ጌታቸውን የሚያውቁ የሸራተን ምንጮች እንደሚሉት በመሞላቀቂያ ጊዚያቸው አቶ አሰፋ መድሃኒት ያዘወትሩ ነበር። የልብና የስኳር ህመምተኛ የነበሩት አቶ ጌታቸው ወደ መቀለ ከሸሹ በሁዋላም ቢሆን ይህ ነው የሚባል ጤና አልነበራቸውም።


የጫካ ትግሉን የሚመሩት ጌታቸው አሰፋ በጠና መታመማቸው ተሰማ

የቀድሞ የአገር ውስጥ ደህነትና ዋና ሃላፊ የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ በጠና መታመማቸው ተሰማ። በካናዳ የትህነግ አመራር የቅርብ ሰው ለኢትዮ 12 እንደነገሩት ከፍተኛ መዋቅሩ መታመማቸውን ከሰማ ሰንባብቷል።


መታመማቸውን ከሳምንት በፊት የጠቆሙን የመረጃ ሰው እንዳሉት መቀለን ለቀው እንደወጡ የተወሰኑ መኪኖች በአየር ሲመቱ ከመኪና የወረዱት አቶ ጌታቸው የጤናቸው ሁኔታ እየተባባሰ መሄዱ ተሰምቷል። ” ህወሃት ሚስጢር መያዝ የሚችል ድርጅት መሆኑ እንጂ ብዙዎቹ በህይወት ያሉ አይመስለኝም። የማውቃቸውም ሰዎች ይህንን ሲሉ ነው የሰማሁት” ሲልም አክሎ ገልጿል።

የመቀለ ከንቲባ የነበሩት ውንድማቸው አቶ ዳንኤል አሰፋ ቀድሞ የሞቱባቸው አቶ አሰፋ ህይወታቸው ሁሉ አነጋጋሪ እንደሆነ ያለፉ ሰው ሆነዋል። አቶ ጌታቸው ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎም ሆነ በጠና መታመማቸው ሲገለጽ ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑ ሚዲያዎችም ሆኑ ግለሰቦች አላስተባበሉም።

ቁልፍ ሰዎቹን ያጣው ትህነግ ዛሬ የቀሩት የሚባሉት ዶከተር ደብረ ጽዮን፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ፣ አቶ ዓለም ገብረዋህድ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ብ/ጄነራል ጻድቃን፣ ብ/ጄ ወረደ፣ አለቃ ጸጋዬ፣ ከሚጠቀሱት በቀር በአመራር ደረጃ የሚታወቁት ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አቶ ጌታቸውን ጨምሮ በሕይወት የሉም።

የመረጃ አቀባያችን እንደሚሉት በርካታ ጄነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች በተፈላጊ ሊስት ውስጥ ቢኖሩም መያዛቸው ይፋ አልሆነም። ይሁን እንጂ ዛሬ እንደተሰማው አስራ አንድ ጀነራሎችና ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ 34 ኮሎኔሎች ሰሞኑንን በተጀመረው የክፍል ሁለት ኦፕሬሽን እርምጃ ተውስዶባቸዋል። የተማረኩም።

መግቢያ በማጣት በሽሽት ወደ አገው ዞን ለመመሸግ ሲያመራ የነበረ የትህነግ ሰራዊት በአማራ ክልል ልዩ ሃይል ተመቶ የተረፈው ሲመለስ መከላከያ ሙሉ በሙሉ ደምሥሦታል።

አቶ ጌታቸው ረዳ “አንድ መቶ ሺህ ሰራዊት ደምስሰናል። ምርኮኛውን መቀለብ ስላልቻልን ለቀናል።” በሚል ለትግራይ ሚዲያ ሃውስ ከተናገሩና በቅርቡ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የአጻፋ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን፣ በቅርቡም ትግራይን ነጻ እንደሚያወጡ አስታውቀው እንደነበር ይታወሳል።

የአቶ ጌታቸውን ቃለ መተየቅ ተከትሎ የውጭ ሚዲያዎች በከፍተኛ ደረጃ ሽፋን እየሰጡ ትህነግ የመዋጋት አቅሙ ከፍተኛ እንደሆነ፣ ጦርነቱ ሊሰፋ እንደሚችል በማስፈራራት ድርድሩን እንደ አንድ አማራጭ እያደረጉ ሊፈጠር የሚችለውን ቀጠናዊ ቀውስ በማጉላት ተጽዕኖ ለመፍጠር ሲጥሩ ነበር።

” ጦርነቱን ቶሎ መዝጋት፣ አባይን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሌቱን ማካሄድ፣ለጊዜው  ከሱዳን ጋር ጥንቃቄ የተሞላበት ድርድር ማድረግ” የሚል አጀንዳ ይዞ የተነሳው መንግስት የትህነግን  ሃይል ወደ አንድ አካባቢ ሲገፋ መቆየቱ ታውቋል።

ባለፈው ሳምንት ሁለተኛውንና የመጨረሻውን ምዕራፍ ኦፕሬሽን የጀመረው የመከላከያ ሰራዊት ቁልፍ ናቸው በተባሉ አመራሮችና መሪዎች ደጃፍ መድረሱን መዘገባችን ያታወሳል። ዛሬ ኢሳት የመከላከያ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው በጦርነቱ ከተደመሰሱት ውስጥ የበርካቶችን አስከሬን መለየት አልተቻለም። የታወቀው የብ/ጄ አብረሃ ተስፋዬ /ዳንኩል አስከሬን ብቻ ነው።

ቀደም ሲል ሌሎች ግንባሮች እንደሆነው አንገታቸው የተቆረጠ አስከሬን በብዛት መገኘቱና ባንድ ጉድጓድ እስከ አርባ አስከሬን እያደረጉ የቀበሩባቸው መቃብሮች መታየታቸው ታውቋል። 2800 የሚሆኑ የሰራዊቱ አባላት ሲሞቱ 1800 የሚሆኑ ቁስለኛና ምርኮኛ እንደሆኑ ከግንባር የመከላከያ ምንጮች ለኢሳት ጠቁመዋል። ድርድር እንዲደረግ ገፊት ባለበት በአሁኑ ወቅት ትህነግ ሃይሉ መመናመኑ ተስፋ አስቆራጭ እንደሚሆን ጉዳዩን የሚከታተሉ ተናግረዋል።

አቶ ስብሃት ሲያዙ ” እሱ ታሟል እስካሁን የሚቆይ አይመስለኝም” ሲሉ አጠገባቸው ለነብሩ መኮንኖች ሲናገሩ የሰሙ ለኢትዮ 12 ጠቁመው ነበር። የፕሬዚዳንት ባይደን አመራር ወደ ስልጣን እንዲመጣ ከፍተኛ በጀት መድበው ዘመቻውን ሲደግፉ የነበሩ የትህነግ የውጭ ክንፍ አባላት ጦርነቱ ያለጊዜው እንዲጀመር ያደረጉት አቶ ጌታቸው አሰፋ ናቸው በሚል ጣታቸውን ሲቀስሩባቸው እንደነበር ይታወቃል። ዛሬም ድረስ እነዚህ ሃይሎች ቢያንስ የመደርራደሪያ አቅም እንዳይኖረን አድርጎናል ሲል አቶ ጌታቸውን ይወቅሳሉ። ይህ ልዩነት እያደር መካረሩ እንደማይቀር ግምት አለ።

Exit mobile version