Site icon ETHIO12.COM

አሜሪካ ድምጽ ጃል መሮን ሳይሞግት ለሁለተኛ ጊዜ አስተባበለለት፤ ተጎጂዎቹ ኦነግ ሸኔ እንዳረዳቸው መረጃና ማስረጃ አላቸው

በወለጋ ዞን ሆሮ ጉድሩ የተለያዩ ወረዳዎች ከ42 በላይ ንጹሃን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ከጭፍጨፋው ያመለጡ ምስክሮች አስታውቀዋል። ድርጊቱንም ኦነግ ሸኔ እንደፈጸመባቸው፣ ከመፈጸሙም በፊት ማስፈራሪያ እንደነበር አስታውቀዋል። የሰለባዎቹ ቤተሰቦችና የዓይን ምስክሮች በገሃድ ይህንን ቢሉም ቪኦኤ ጃል መሮን ጠቅሶ የዜናው አቅጣጫውን ወደ መንግስት አዙሮታል።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የአማራ ተወላጅ የሆኑትን እየለዩ እንዳረዷቸውና እንደገደሉው ገልጸዋል። የተረፉም ቆስለው ሃኪም ቤት ናቸው። ከጥቃት የተረፉትም የመንግስት ሃይል ባለበት ቦታ ራሳቸውን ለማትረፍ እየፈለሱ ነው። ፖሊስንና እማኞቹን ያናገረችው ሪፖርተር ጽዮን ግርማ ስትሆን በዘገባው የተካተተውን ጃልመሮን አናግሯል ተብሎ ስሙ የተጠቀሰው ተቀማጭነቱን አምቦ ያደረገው የቪኦኤው ሌላ ሪፖርተር ናኮር መልካ ነው።

ናኮር እጅግ ሰፊ ቁጥር አላቸው የተባሉትን የአማራ ብሄር አባላት ቁስለኞችን ከሆስፒታል ሲያናግር በዘገባው አልተሰማም። ናኮር ጃል መሮን ሲጠይቅም ድምጹ የለም። ምን ብሎ እንደጠየቀውም አልተሰማም። ይሁን እንጂ ጃል መሮ የተባለውና በኦነግ ሸኔ መሪነት የሚታወቀው ይህ ግለሰብ እሱ የሚመራው ሰራዊት በብሄር ነጥሎና ለይቶ ጥቃት እንደማያደርስ፣ ይልቁኑም ጥቃቱን ያደረሱት የኦሮሚያና የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች እንደሆኑ አስታውቋል። የአማራ ልዩ ሃይል ሆሮ ጉድሩ ድረስ ሄዶ የአማራ ብሄር አባላትን ለምን እንደሚገድል፣ ከግድያው ምን እንደሚያተርፍ፣ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ለዚህ ግድያ ተባባሪ ሲሆን ምን እንደሚጠቀም ጃል መሮ እንዲያብራራ በመስቀለኛ ጥያቄዎች ባይሞገትም ” ለምን” እንኳን ተብሎ አልተጠየቀም።

ጥቃቱን ፈጸመ የተባለውና ምስክሮቹ በስም የጠቀሱት የኦነግ ሸኔ ሆኖ ሳለ ቪኦኤ በድረ ገጹ ” የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ” ሲል የጠራው የምዕራብ ኦሮሚያ አዛዥ ኩምሳ ድሪባ ወይም ጃል መሮ እንዴትና ለምን ከኦነግ ሸኔ ወደ ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እንደተቀየረ ማብራሪያ አልጠየቀም። ሸኔ በወንጀል ተከሶ ሳለ በሌላ ስም ውንጀላውን ለምን ማስተባበል እንደተፈለገም ግልጽ አልሆነም።

ከሃጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞ በግልጽ የስልክ መልዕት የኦነግ ሸኔ ግድያውን እንዳቀነባበረ፣ ሊገለው ይዝትበት እነደነበር ራሱ ሃጫሉ መናገሩና ቤተሰቦቹ ምስክር መሆናቸውን ተከትሎ ህዝብ በጥቅሉ ኦነግ ሸኔ ፖለቲካዊ ሞት መሞቱን በሚያወራበት ወቅት የቪኦኤዋ ጽዮን ግርማ ” አንተ ማን ነህ? እንዴት እንመንህ?” እንኳን ሳትለው ቃለ ምልልስ አድርጋበት እንደነበር ያስታወሱ፣ የአሁኑም ቃለ ምልልስ የዚያው አካል እንደሆነ ያስባሉ።

ቪኦኤና ጀርመን ድምጽ – የክልሎችን ኅልውና እንደ ህወሓት እየጣሱ ነው

ይህ በውቅቱ ሃጫሉ ሲገደልና ጃል መሮ በቪኦኤ ማስተባበያ ካደረገ በሁዋላ በትቅሉ የተጻፈ አስተያየት ሲሆን የተወሰደው ከጎልጉል ነው

“በቅርቡ ጃልመሮ የተባለው የኦነግ ሸኔ በንጹሃን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጭፍጨፋ መንግሥትና ሰለባዎች ካጋለጡና የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳይን አስገዳይ ኦነግ ሸኔ መሆኑ ሲገለጽ፣ ቪኦኤ ማስተባበያ መሥራቱ ዕድሜ ልኬን የማልረሳው ስህተት ነው” ሲሉ ለጎልጉል አስተያየት ሰጥቶ ነበር።

አሁን የተፈጸመው ግድያ በመላው የኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ሳይቀር ከፍተኛ ቅሬታ በማስነሳቱ ጃልመሮ ለማስተባበል እንደወጣ አመለካች መሆኑንን ያመለክቱ እንዳሉት ቪኦኤ ኦነግ ሸኔ በከፍተኛ ደረጃ አሰቃቂ ወንጀል ሲፈጽም ማስተባበያ ሲሰራ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑንን አውስተዋል።

ከጥቃቱ የተረፉና ቤተሰቦቻቸው በጥቃቱ እንዳጡ የሚናገሩ ቤተሰቦች ግን የጦር መሳሪያ በሚገባ የታጠቁና የኦነግ ሸኔ መለያ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች እንዳጠቋቸው ገልፀዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ “ኦነግ ሸኔ ጥቃቱን ከፈፀመ በኋላ ሁሌም የሚያሳብብበት አካል ይፈጥራል” ማለታቸው በዜናው ተመልክቷል።

የቪኦኤን ዘገባ እዚህ ላይ ያድምጡ

ከሆሮ ጉድሩ የወጣው የቪዲዮና የምስል መረጃ እጅግ የሚያም፣ ለማየትም የሚጨንቅ፣ ፍጹም አረመኔነት የተሞላበት ጄኒሳይድ ሲፈጸም የሚያሳይ ነው። ናኮር መልካ አንድ ሰው ሲታሰር የዋስ መበቱ ተለከለ ብሎ ለድግግሞሽ መልስ ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ፣ የወረዳ፣ የዞን፣ የክልል አስተዳርና የጸጥታ መዋቅር አደራርቦ ሲጠይቅ የሚታወቅ ሪፖርተር ነው። ጃል መሮን ለዚህ ጉዳይ ጎትቶ ሲያመጣ ቢያንስ በጥያቄ ደረጃ መነሳት ያለባቸው ሰፊ ጉዳዮች እንዳሉ የሚዘነጋው አይመስለንም። ናኮር ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የራሳቸው እምነትና ውግንና ሊኖራቸው ይችላል። ግን ወደ ስራው ሲመጣ ታዛቢ ስላለና ከዛም በላይ በግፍ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሕጻናት ስላሉ ለህሊና መታመን አግባብ መሆኑንን ዝግጅት ክፍላችን መግለጽ ይወዳል።

Exit mobile version