በምዕራብ ውለጋ ነጹሃን ተገደሉ፤ ግድያው ብሄርን መሰረት ያደረገ ነው፤ “ጃልመሮ በቪኦኤ ያስተባብላል”

አስቀድሞ ነዋሪዎቹን አንድ ቦታ ሰብሰቦ እንደጨፈጨፋቸው ነው የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያስታወቀው። ቦታው በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ፣ ቦኔ ቀበሌ ሲሎን በርካታ ዜጎች በብሄር ተለይተው ነው የተገደሉት። የተለያዩ የዩቲዩብ አውታሮች የሟቾችን ቁጥር ወደ መቶ ከፍ አድረገውታል። አንዳንዶች በፌስ ቡክ በተመሳሳይ ቁጥሩን ከሰባ በላይ እንደሆነ አመልክተዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ግን 28 ሰዎች መሞታቸውን በይፋ አመልክቷል። በድንገት በሚከፈት ጥቃት በርካታ ንጹሃን አርሶ አደሮችን የገድላል በሚል የሚወነጀለው ጃልመሮ ይህንኑ ጥቃት አስመልክቶ በቪኦኤ ማስተባበያ ይሰጣል ብለው እንደሚጠብቁ የገለጹ አሉ።

ግድያውን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል ባወጣው መግለጫ በዞኑ ውስጥ በሚገኘው ባቦ ገንቤል ወረዳ በቦኔ ቀበሌ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ “አሰቃቂና ዘግናኝ” ያለውን ጥቃት የፈጸመው ኦነግ-ሸኔ መሆኑንን አመልክቷል። ወዲያው የክልል የጸጥታ ሃይል የአጸፋ እርምጃ መውሰዱን በቀጣይነትም በቡድኑ ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለሕዝብ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል። ክልሉ ይህንን ባለ ሰዓታት ውስጥ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ ሶስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወዲያውኑ መገደላቸውን አመልክተዋል።

ክልሉ እንዳለው ኦነግ ሸኔ የህወሓት ተላላኪ በመሆን በአካባቢው የመንግሥት መዋቅርን በማፍረስ በገጠርና በከተማ በመንግሥት አመራሮችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከዚህ በፊት “ዘግናኝ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል” ብሏል አያይዞም የቀበሌ ጨምሮ በተለያዩ ደረጃ ያሉ አመራሮችንና፣ እንዲሁም ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የክልሉ መንግሥት መግለጫ አውስቷል። ቡድኑ በግልና በመንግሥት ንብረቶች ጥቃት ሰንዝሯል።

በተደጋጋሚ መንግስት በወስደበት እርምጃ በመዳከምና ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ያለው ኦነግ ሸኔ “በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ የጥፋት ሴራውንና እርምጃውን ቀጥሏል” ሲል ክልሉ በመግለጫው የቡድኑን የማይቀየር ባህሪ አመላክቷል።

የኦሮሚያ ፖሊስ እንዳለው የተገደሉ ንፁሀን ዜጎች 28 ናቸው። 16 ወንዶች እና 12 ሴቶች ህይወት ተቀጥፏል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ እንዳሉት ከሟቾች በተጨማሪም 12 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የክልሉ ፖሊስ በአካባቢው ደርሶ አካባቢውን ለማረጋጋት ባደረገ ስራም ሶስት የኦነግ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ ተናግረዋል።ከምሽቱ ሶሰት ሰአት ላይ ከ50 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ሰብስቦ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ጭፍጨፋ ፈፅሟል ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። ባለፈው አንድ አመት በኦነግ ሸኔ ላይ በተወሰደም እርምጃ 1 ሺህ 947 አባላቱ የተገደሉ ሲሆን 489 አባለቱ ደግሞ መማረካቸውን ኮሚሽነር ጀነራሉ ተናግረዋል።

” ስሜ ኦነግ ሸኔ አይደለም” ሲል ባለፈው በሆሮ ጉድሩ የተፈጸመውን እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በቪኦኤ እንዲያስተባብል እድል የተመቻቸለትና ከስሙ በቀር በውል ማንነቱ የማይታወቀው ጃልመሮ በቅርቡ እንዳለው በአዲሱ ስሙ ” ወንጀሉን እኛ አልፈጸምንም። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በብሄርና በሃይማኖት ለይቶ አይገድልም፤ ግድያውን የፈጸሙት የአማራና የኦሮሚያ ብልጽግና ናቸው” በማለት እንደሚያስተባብል ጭፍጨፋው ስር አስተያየት የሰጡ ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ብልጽግና ወለጋ ድረስ ሄዶ የራሱን ወገኖች ለምን መግደል እንዳስፍለገው ማብራሪያ እንዲሰጥ ያልተጠየቀው ጃል መሮ ዛሬም ተመሳሳይ መግለጫ እንደሚሰጥ በአስተያየት ሳጥን ስር የጻፉ ” አትገረሙ ቢቢሲና ቪኦኤ የጃልመሮ ናቸው” እያሉም ብስጭታቸውን በስላቅ ለማሳየት ሲሞክሩ ታይተዋል።


Related posts:

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

Leave a Reply