Site icon ETHIO12.COM

የኤርትራ ሰራዊት ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቷል ስለሚለው ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተናገሩት‼

👉 የኤርትራ ሰራዊት ትግራይ ውስጥ ገብቷል በሚልም በሰፊው ይነሳል፤

👉 በመጀመሪያ ወዳጅም ጠላትም ማወቅ ያለበት የኢትዮጵያ መንግስት፣ ሕዝብና የመከላከያ ሰራዊት ክህደት ተፈጽሞበት በገዛ ወገኖቹ ጥፋት ሲካሄድበት የኤርትራ ሕዝብና መንግስት ወደሱ የሄዱትን ወታደሮች የያዘበት ወደፈለጉት እንዲሄዱና እንዲደርሱ ድጋፍ ያደረገበት መንገድ የሁልጊዜም የኢትዮጵያ ባለውለታ ያደርገዋል፤

👉 ማንኛውም አክቲቪስት ነኝ ብሎ በሚናገረው ንግግር የሚበላሽ ጉዳይ አይደለም፤ በጭራሽ፤

👉 የተከበረው ምክር ቤት እንዲገነዘብ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፤ በችግር ቀን ሰው አብሮ አይቆምም፤ እንኳን ሰው ጨለማ ሲሆን የራስ ጥላ ይከዳል፤ ጥላ ሲከተል የሚታዬው ብርሃን ሲኖር ነው፤ ጨለማ ሲሆን ይሸሻል አይታይም፤

👉 ስለዚህ በችግር ጊዜ የእኛ ወታደሮች ከመከራ ወጥተው ሄደው የተደረገላቸውን እንክብካቤ የኢትዮጵያ ህዝብ በታሪክ አይረሳውም፤

👉 ይሄን እንድንክድ፣ እንድንረሳ፣ እንድንሳደብ የሚፈልጉ ሀይሎች ሞኞች ናቸው፤ በፍጹም አናደርገውም፤

👉 የኤርትራን ሕዝብና መንግስት ስላደረገው ነገር በጣም ነው የምናመሰግነው፤

👉 ከዚያ በኋላ የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሸግሮ በትግራይ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ በእኛ ሕዝብ ላይ በማንኛውም መንገድ በጥፋት በሚገለጽ የሚያደርጋቸውን ጥፋቶችን አንቀበልም፤

👉 ይሄን የማንቀበለው የኤርትራ ወታደር ስለሆነ አይደለም፤ የእኛ ወታደርም ይሄን ካደረገ በፍጹም አንቀበልም፤ ምክንያቱም ዘመቻው በግልጽ ከተለዩት ጠላቶቻችን ጋር እንጂ ከሕዝባችን ጋ አይደለምና፤

👉 ይሄን በሚመለከት ከኤርትራ መንግስት ጋር በተደጋጋሚ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ወደዚያም ወደዚህም ልከን ስንወያይ ቆይተናል፤

👉 የኤርትራ ወታደር የኢትዮጵያ ድንበሮችን አልፎ ያለባቸውን አካባቢዎች በሚመለከት የኤርትራ መንግስት የሚያነሳው መከራከሪያ ጉዳይ ላለፉት ሃያ አመታት የኢትዮጵያ መከላከያ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ምሽግ ለቃችሁ ሂዳችኋል፤ የጁንታው ሀይል ወደ ውጊያው እንድንገባ ሮኬት እየተኮሰ ጋብዞናል፤ አሁን ደግሞ እናንተ ይሄን ምሽግ ለቃችሁ ወደመካከለኛው ትግራይ ጠላት ፍለጋ እየሄዳችሁ ስለሆነ እዚያ ስታጠቁት ተገልብጦ ወደ እኛ ሊመጣ ይችላል፤ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ አለብን፤ ለዚህ ብለን ድንበር አካባቢ ያሉትን ቦታዎች ይዘናል፤ ነገር ግን የእናንተ ወታደር ምሽጎቹን የሚቆጣጠሩ ከሆነ በማግስቱ ለቀቅን እንወጣለን፤ በማግስቱ እኛ የለንም፤ መቆየት አንፈልግም ብለዋል፤

👉 በሁለተኛ ደረጃም የሚፈጸም በደል አለ፤ ዘረፋ ይታማል በሚል ለኤርትራ መንግስት አቅርበናል፤

👉 የኤርትራ መንግስት ድርጊቱን በከፍተኛ ሁኔታ ነው የኮነነው፤

👉 የኤርትራ ወታደር በዚህ የሚሳተፍ ካለ ርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፤
ዋናው ኦፕሬሽን ጨርሰን ድንበሮችን ማስከበር መቻል ነው፡፡

Exit mobile version