Site icon ETHIO12.COM

አዲስ አበባ ሲሚንቶ ከ377 ብር በታች እንዲሸጥ መወሰኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

50 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ አዲስ አበባ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች ከ377 ብር በታች እንዲሸጥ መወሰኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ


በሲሚንቶና ሌሎች ምርቶች ላይ የሚስተዋለው ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ሕገ ወጥ ደላሎች እና ሌሎች የፖለቲካ አሻጥረኞች በሚሠሩት ሴራ ምክንያት መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

መንግሥት የኅብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማሻሻል በርካታ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑንም የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል፡፡ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ሚናው ከፍተኛ ለሆነው የግንባታው ዘርፍ በዋና ግብዓትነት የሚያገለግለውን የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት ስርዓትና የዋጋ መጨመር ለማስተካከል እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች አማካኝነት የቀረበ 50 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ አዲስ አበባ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች ከ377 ብር በታች እንዲሸጥ ተወስኗል ብለዋል፡፡ ደርባ 343 ነጥብ 35፣ ሙገር 352 ነጥብ 63፣ ሐበሻ 364 ነጥብ 39 እና 376 ነጥብ 28 እንዲሸጥ መወሰኑን ነው ያስታወቁት፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም የስርጭት ፍትሐዊነቱን ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ለኅብረተሰቡ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተወስኗል ብለውል።

(ኢ.ፕ.ድ)

Exit mobile version