Site icon ETHIO12.COM

የትግራይ ልዩ ሃይል በመቀለ እንሳሳት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሴት የመከላከያ አባላት ላይ የሰራው ያልተወራ “አኩሪ ገድል”

” እኛ ለስብአዊ መብት የሚበቃ ህይወት የለንም። እኛ ስማችን የጦር ሰራዊት ስለሆነ እናት እይደለንም። እኛ በግዳጅ ላይ ስለነበርን ከሰው እኩል አይደለንም። እኛ በግዳጅ ላይ ሆነን በታማኝነት ስላገለገልን ከትግራይ ልዩ ሃይል ያነሰ የሰውነት ደረጃ ነው ያለን። እኛ ማንኛውም ጥቃት ቢፈጸምብን ህጋዊና የሚደገፍ ነው። መሳሪያ ጥለን ከተለያየ አካባቢ አንድ ላይ አሰብስበው ካገቱን በሁዋላ የትግራይ ልዩ ሃይል የፈጸመው ግፍ ተዳፍኖ አይቀርም” በቁጭት የወጣ ሲቃ ያለበት የአንድ ጀግና ቃለ ነው።

መቀሌ የንሣት ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ ከ800 በላይ ሴት የሰራዊት አባላት ታግተው ነበር። ከተለያዩ አካባቢ እየተጋዙ እዚያ የታገቱት ሴት ወታደሮች ተዋጊ ብቻ ሳይሆኑ በአየር ሃይል ቅጥር ገቢ ስልጠና እየወሰዱ የነበሩም ይገኙበታል። በድንገት ባሉበት መሳሪያቸውን እንዲፈቱ የተደረጉ፣ ከትንቅንቁ የቅጽበት ጦርነት የተረፉና ስልጠና ላይ የነበሩት ሴት ወታደሮች ወደ ኮሌጁ ከተጓጓዙ በሁዋላ መጀመሪያ የሆኑት በመንገድ ላይ ሳይቀር መዘረፍ ነው።

እጃቸው ላይ ቁሳዊ ነገር፣ ልብስና ጌጥ ተቀሙ። ቅያሪ ልብስ እንኳን ሳያስቀሩ እርቃናቸውን አስቀሩዋቸው። ለኢትዮ12 መረጃውን ከሰጡ መካከል አንዷ ” ዘረፋው ችግር አልነበረውም፤ ሞራል የሚነካ ተግባር ፈጸሙ። ዛሬ እንደተበዳይ ይጮሃሉ … ” ዝም አለች። ” ከምኑ ልጀምርልህ?” ጠየቀች ለምን ይሸፋፈናል? መንግስት ለምን ገሃድ አያወጣውም” ስትል አሁን ዝም አለች።

” በትንቅንቁ የሞት ሽረት የድነገት ውጊያ ሴት ወታደሮች መሳሪያ ከፈቱና ከታገቱ በሁዋላ እዛው ጡታቸው ተቆርጧል። መሳሪያ የፈቱ እህቶቻችንን አረዷቸው” ራስዋን መቆጣጠር እየተሳናት ” የዚህ ሁሉ ግፍ ፍርድ ምን ይሆን” ስትል ጠየቀች። አያይዛም ” ማረድና መግደል ሳያንስ የአስከሬን ጡት ቆረጡ። ከዛ ስቃይ የወጣነውን አግተው መቀለ ኮሌጅ ካመጡን በሁዋላ በቡድን ሆነው ደፈሩን” ስትል አነባች።

ያነባችው ከሃጂነታቸውን ስታስብ ከሚፈጠርባት የቁጭት ስሜት እንጂ በመንፈሰ ልፍስፍስነት እንዳልሆነ ገልጻ ” አጉረውን የምንቀይረው ልብስ እንኳን የለንም ነበር። አስበው ሴት ልጅ ያለ ቅያሬ ልብስ” ስትል ምን ያህል የከፋ በደል እንደፈጸሙባቸው ዘርዝራ አስረዳች። ሌላዋ ዛሬ ወደ ሌላ ቦታ ተዛውራ ስልተናዋን እየተከታተለች ያለችው የሰራዊቱ አባል ” እነሱ የሰሩት ግፍ በተጋነነ የሃሰት ጋጋታ ተሸፍኖ እኛ ጥፋተኛ መሆናችን ሌላ ህመም ነው” በማለት ሌላ ነገር ለመናገር ሃይል እንደሌላት አወሳች።

ያነጋገርናቸው እንዳሉት መሳሪያ ያስረከቡ፤ ታግተው በአንድ አጥር ስር እንዲኖሩ የተደረጉ ተድፍረው፣ ተዘርፈውና በሴትነታቸው የተፈጠሮ ሂደት ሳይቀር ግፍ ተፈጽሞባቸው ሳለ ስለምን የሰብአዊ መብት ተቋማት እነሱ ዘንድ አይሄዱም? ጥያቄያቸው ይህ ብቻ አይደለም መንግስት የዓለም ዓቀፍ ሚዲያ ሰዎችም ይሁኑ ተቋማት እነሱን እንዲያናገሩ ለምን አያደርግም? የሚል ጥያቄ አላቸው።

ሴት የአገር መከላከያ አባላት ላይ የተፈጸመው የጅምላ ጥቃት አሳዛኝ ነው። ይህንን ስንሰማ አብሮ የነበረ እንዳስረዳን በእንስት ወታደሮቹ ላይ የተፈጸመው ግፍና ወንጀል ራሱን ችሎ በገለልተኛ ሃይል ሊጣራ የሚገባው ጉዳይ ነው። እንደ እሱ አባባል ሚዲያዎችና አገር ወዳዶች በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩና ጫና ሊያደርጉ ይገባል። በሃፍረት የደረሰባቸውን መናገር ለማይፈልጉ ልዩ ዘዴ ተመቻችቶ መረጃ የሚሰጡበት መንገድ ሊፈጠር እንደሚገባ አመልክተዋል። የሃሰት መረጃ የሚሰጡትና ሰልጥነው እነደሚናገሩ ያስታወሰው የመከላከያ አባል ” የእኛ ሙሉ በሙሉ እውነት የሆነና ግነት የሌለበት መሆኑ እህቶቻችንን ፍርሃት ላይ ጥሏቸዋል ” ይላል። እሱ እንደሚለው የዝግጅት ከፍላችን ካናገራቸው መካከል ለመናገር ፈቃደኛ ያልሆኑ አሉ። ከዚህ አንሳር የሕክምና ባለሙያዎች የምክር አገልግሎት በመስጠት የህንን የሃፍረት መጋረጃ መገርሰስ እንደሚገባቸውም ተተቋሟል።

Exit mobile version