ETHIO12.COM

በሱዳን እንቅፋትነት የኪንሻሳው ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ

ተቋርጦ የነበረው የህዳሴው ግድብ ድርድር በሱዳን እንቅፋትነት ያለ ስምምነት መበተኑ ተሰማ። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ስማቸውን ያልገለጻቸውን የኮንጎ ባለስልታን ጠቅሶ እንዳለው በድርድሩ ማብቂያ በይፋ ሊበተን የነበረውን መግለጫ የተቃወመችው ሱዳን ናት። ሱዳን ኢትዮጵያን ወቅሳለች።

ኢትዮጵያ በህልውናዋና ዜጎቿን ከጨለማ ለማላቀቅ የያዘችውን እቅድ ማንንም ሳትጎዳ ከመተግበር ወደሁዋላ እንደማትል ማስታውቋ ይታወሳል። በዚሁ ቁመናዋ ወደ ኪንሻሳ ያመራቸው ኢትዮጵያ ከየሱዳንና የግብፅ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ጋር ተደራድራ ነበር።

ኪንሻ-ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተከናወነው ድርድር ዝርዝሩ በይፋ ባይቀርብም አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳለው ያበቃው ያለ ውጤት ነው። በወቅቱን የአፍሪቃ ሕብረት መሪ አገር በሆነችው ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ አደራዳሪነት የተከናወነው ይህ ድርድር ለወራት ተቋርጦ የተጀመረ በመሆኑ አዳዲስ ውሳኔዎች ይገኙበታል የሚል ግምት አሳድሮ ነበር።

ኤኤፍፒ ዘገባ ከሆነ ሶስቱ ተሸማጋዮች ድርድራቸውን ከጠናቀቁ በሁዋላ የተዘጋጀውን የመግለጫ ይዘት ግብፅና ኢትዮጵያ ሲቀበሉት ሱዳን አልተስማማችም። በዚሁ የሱዳን አቋም ሳቢያ ድርድሩ ውጤት አልተመዘገበበትም።

የሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ማሪያም አል ሳዲግ አል መሕዲ እንዳሉት ለድርድሩ መቋረጥም ኢትዮጵያን ተጠያቂ አድርገዋል። ከኪንሻሳ መግለጫ የሰጡት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ በተናጠል ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጥስእርምጃ መውሰዷን አመልክተዋል።

የግብፅ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ድርድሩ ያለ ውጤት መቋጨቱን ከመናገራቸው ውጭ ምንም እንዳላሉ፣ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድንም በይፋ የሰጠው አስተያየት ስለመኖሩ ኤኤፍፒ ያለው ነገር የለም።


Exit mobile version