Site icon ETHIO12.COM

“ዕቅዱ ሃይላችንን በግጭቶች በታትነው መቆም የሚገባን ቦታ ሆነን አገር እንዳንጠብቅ ለማድረግ ነው” ጠ/ሚ አብይ

የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በአነስተኛና በድንገተኛ ግጭት በመበታተን መቆም የሚገባው ላይ ሆኖ አገሩን እንዳይከላከል ለማድረግ የተከፈተውን ዘመቻ ተረድቶ መዘጋጀት የወቅቱ ጥያቄ መሆኑንን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስታወቁ። በደረሰው ክፉ ድርጊት ስሜታቸውንም ገልጸዋል።

ምርጫን አስመልክቶ ዛሬ ከክልል መሪዎችና ሃፊዎች ጋር ውይይት ሲያደርጉና የስራ መመሪያ ሲሰጡ እንዳሉት በየአቅጣጫው ሽፍቶች ጥቃት የሚሰነዝሩት ሃይል ለማዳከም ነው። ኢትዮጵያን የሚወዱ ሁሉ በአንድ ላይ ህብረት አለመፍተራቸው ጉዳት እንዳለው ጠቅሰው ወቃሳም ሰንዝረዋል።

መከላከያን ፖሊስ ለማተናከር ሃይል ሲጠየቅ መልስ እንደሌለ፣ ሁሉም ቤቱ ተቀምጦ ሰላም ጠያቂ መሆኑ እርስ በርስ የሚጋጭ ተግባር እንደሆነ አመልክተው፣ ይህ ትክክል እንዳልሆነ ጠቁመዋል። አያይዘውም ” ሃሳብ ሲደርቅ ስድብ ይከተላል” በማለት የክልል አመራሮች ይህን ስድብ ወደ ጎን በመተው ምርጫ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አበረታተዋል።

ምንም ይሁን ምን ከምርጫ ውጪ ሌላው መንገድ የመንግስትን እርምጃ አቋም ያስቀይር እንደሆን እንጂ ሌላ አማራጭ ስለማያስገኝ ሁከትን አቋራጭ ማድረግ እንደማይጠቅም ገልጸዋል። እሳቸውም ሆኑ ፓርቲያቸው ቃለ በገቡት መሰረት ፍትሃዊ ምርጫ የማድረግ ፍላጎታቸው እንደማይታጠፍ በመግለጽ ጥብቅ ማስተንቀቂያ አክለዋል።

መስከን፣ ሃላፊነት በተሞላው መንገድ ማሰብ፣ ከስሜት መውጣት እንደሚያስፈልግ በማውሳት፣ ጠላት ባስቀመጠው ቦይ መፍሰስ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠቁመዋል።

ማንም እንዳየው የጨረቃ ምርጫ አካሂደው አገር ለማተራመስ የሞከሩ ምን እንደደረሰባቸው በመግለጸ፣ አገር ለማተራመስና ለማፍረስ የቤት ስራ የውሰዱ በተመሳሳይ እንደሚፈርሱ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን የተሸከመ መሪና ድርጅት በረባውም ባልረባውም የአደባባይ ስድብ ሊያኮርፍ እንደመይገባ ለክልል አመራሮች አጽንዖት ሰጥተው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ሃሳብ አዘጋጅተው መሸጥ ያልቻሉ ስድብን ማምረታቸው እንደማይገርም አመልክተዋል። አያይዘውም በዚህ መልኩ እንደማይቀጥልና ህጋዊ አካሄድ መከተልም አግባብ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።

” መስዋዕት እየተከፈለ እውቅና የሚነፈግ ከሆነ ድካም ያመጣል” ሲሉ አንዳንዶች መከላከያን ሊወርፉ መሞከራቸውን በመቃወም የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ድርጊቱ ነውር መሆኑንንም አስታውቀዋል። ሙሉውን ከቪዲዮው ያድመጡ


Exit mobile version