Site icon ETHIO12.COM

ጎንደር ” የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማርሻ ቀያሪ” ለይቶ ተቃውሞ አሰማ፤ “ወንድም የኦሮሞ ሕዝብ” ሲል የነውጥ አራጋቢዎችን ሃሳብ ገለበጠ

የኦህዴድ ጽንፈኞችና “አክራሪ” የሚባለው አብን በአንድነት የጠመቁት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ሴራ ዛሬ ጎንደር ላይ ተገለበጠ። ጎንደር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማርሽ ቀያሪነቱን አሳየ። ሰልፉ ክልሉን ለማናወጥና ሕዝብ እንዲጋጭ ሌት ተቀን ለሚሰሩ ፖለቲካዊ ሞት እንደሆነ ተመልክቷል።

ሰሞኑንን በደረሰው ዝገናኝ እልቂትና የንብረት ወድመት ማግስት የሽግግር መንግስት የጠየቁ አሉ። አብን መንግስት እንደሌለ ሲያውጅና ክተት ሲጠራ “የሞሳድ ስራ አስፈሳሚ” የሚባሉት፣ ቀደም ብለው አገራቸውን ከድተው የሸሹትና በውድ የኢትዮጵያ ጀነራሎች የተመራውን መፈንቅለ መንግስት እንዳከሸፉ የሚታወቁት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ አበበ በለው በሚመራው የአዲስ ድምጽ ሬዲዮ በኩል የሽግግር መንግስት ለማቋቋም የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ይፋ አድረገዋል። አያይዘውም ተቃውሞው እስከ አራት ኪሎ ቤተመንግስት እንደቀጥል ጥሪ አቅረበዋል።

ይህንኑ ተከትሎ ስሙ እንዳይተቀስ የጠየቀ የኦፌኮ ወጣት ክንፍ አመራር ” ምንም እንኳን አመራሮቻችን ቢታሰሩና በምርጫው ባንሳተፍም በክልላችን ጉዳይ ማንም እንዲፈተፍት በር አንከፍትም። ተቀባይነት የለውም። የሚሰሙት አንዳንድ ሃሳቦች ወቅቱን ካለመገንዘብ የመጣ ነው” ሲል ተናግሮ መሪዎችም ቢጠየቁ የተለየ መልስ እንደማይኖራቸው አመልክቷል። ” ኦሮሙማ ይወደም” እያሉና እያስባሉ በህበረት መንግስት ስለመለወጥ ሲያስቡ መደነቁንና ሌሎች ክልሎች ምን ሊያስቡ እንደሚችሉ ለማውቅ አለመሞከራቸው እንደሚያሳስበው አክሎ ጠቁሟል።



በሰሜን ሸዋ በተለይ አጣዬ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ዘር የለየ ጭፍጨፋ በመቃወም አደባባይ የወጡት የጎንደር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ” የከዳን ኦህዴድ እንጂ ወንድም የኦሮሞ ሕዝብ አይደለም” የሚል መፈክር አጉልተው በማሳየት ያሳዩት ተቃውሞ ” ስልጡን” ተብሏል። ጽንፈኛ አመለካከት ላላቸው ደግሞ ታላቅ መልዕክት እንደሆነ ነው የተጠቆመው።

ከሌሎች አካባቢዎች ዘግየት ብሎ በስከከነ መንፈስ መካሄዱ፣ በተለይም ከራያ በተጨማሪ ላለፉት 30 ዓመታት መከራ ለተፈራረቀበት የጎንደርና፣ የወልቃይት ህዝብ ነጻ መሆን አመራር የሰጡና ኤርትራና ጎንደርን ድንበረተኛ እንዲሆኑ ሰፊ ስራ የሰሩ መሪዎችን በጎንደሩ የተቃውሞ ሰልፍ ስማቸው እየተነሳ ሲሰደቡ አልተሰማም።

አብን ” ከፊት እመራዋለሁ” ሲል ድርጅታዊ መግለጫ አውጥቶ፣ መግለጫው አስቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ” አሸባሪ ብሎና የክክሉን ነባርና አዲስ አመራሮች ” ለአማራ ሕዝብ የማይቆረቆሩና የማያዝኑ ተላላኪዎች” በሚል ፈርጆ በቀጣይ ባዘጋጀው የሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ” ኦሮሙማ ይወደም” የሚል መፈክር መስተጋባቱ ቅሬታ አስነስቶ ነበር። ከዚያም በላይ የአማራን ምትክ አልባ መሪዎች ህይወት ያባከነው ጀነራል አሳምነው ጽጌን እንደ ጀግና እንዲወደስ አምስደረጉ በክልሉም ውስጥ አሉታዊ አስተያየት እንዲነሳ ምክንያት ሆኖ ነበር።

የአማራ ክልል በሰልፈኞቹ ቅሬታ ሙሉ ስምምነት እንዳለው፣ ሰልፉ በጨዋነት መደረጉን ዋጋ እንደሚሰጠው፣ የተነሳው የፍትህ ጥያቄ የመጨረሻ እልባት እስኪያገኝ ድርሰ እረፍት እንደማይኖረው ጠቅሶ አንድነት በጠየቀበት መግለጫው አብንን ጠርቶ ጠንካራ ምላሽ ሰጥቷል።

ክልሉ ከህዝብ ነጥሎ “አደገኛ” ሲል አብን እያካሄደ ያለውን የፖለቲካ ገበያ አውግዟል። የአማራ ክልል ዛሬ ላይ ከየአቅጣጣው ችግር እንደገጠምውና በስከነ መንገድ ሕዝባዊነቱን ጠብቆ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባው ያመለከተው መግለጫው ” በድርጅቱ ፕሬዚዳንት፣ በባልስልጣናትና አመራሮች ላይ ስም እየተጠራ የተካሄደው ማጠልሸት ትናንትን የዘነጋ ጸያፍ ተግባር ነው” ሲል መንግስትን በህግ እንዲጠይቅ አሳስቧል። የምርጫ መቀሰቀሻ ፖስተር ሳይቀር እየተመረጠ እንዲወድም መደረጉን ጠቅሶ ምርጫ ቦርድ በድነቡ መሰረት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።

ከለውጡ በፊት የነበረውን ኦሮሙማ እንቅስቃሴ ” የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው” በሚል ገልብጦ ለውጡን አገር አቀፍ ይዘት እንዲኖረው ማርሻ የቀየረው ጎንደር፣ የፖለቲካውን ትግል እንዲነድና የትህነግ መጥፊያ እንዲቃረብ በማድረጉ ሲጠቀስ እንደሚኖር ያወሱ፣ የአዳም ዩኒዘርስቲ ተማሪዎች ” የአማራ ደም የኔም ደም ነው” ሲሉ የትግሉን አቅጣጫ በመቀበልና በማስተጋባት ታሪክ መሰራቱን ገልጸዋል።

ዛሬም ከደረሰው ከፍተኛ ቀውስና ዘግናኝ ጭፍጨፋ ስሜት መውጣት ሳይቻል። ከግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በተበተነበት ሁኔታ የሽግግር መንግስት ለማዋቀር ለሚደክሙ ክፍሎች የጎንደር ሰልፍ እንዳልተመቻቸው አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ቀደም ሲል አዲስ አበባ ገብተው አንድ ወር የተቀመጡት ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ስልጣን ጠይቀው በኢትዮጵያ ጉዳይ መጥፎ ሪኮርድ ስላላቸው፣ አገር ከድተው የነበሩና ለሌሎች እንደሚሰሩ መረጃ በመኖሩ ” ዞር በሉ” ሲባሉ አኩርፈው እንደወጡ በወቅቱ ተገልጾ ነበር። በዚህ ጉዳይ በስፋት በትሩ ሞጋች ያልተፈተኑት ዳዊት ያደራጇቸው ክፍሎች አማራ ክልል ላይ ዘመቻ ከጀመሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው አስተያየት የሰጡ ጥቂት አይደሉም። ዛሬ ጊዜ ቆጥረው በሰጡት ዲስኩር ህዝብ መንግስትን እንዲያስወግድ ጠይቀዋል። ሕዝብ ሲሉ ግን ኦሮሞውን፣ ሶማሌውን፣ ቢኒሻንጉሉን፣ አፋሩን፣ ደቡቡን፣ ሲዳማውን፣ ሶማሌውን ስለመሆኑ አላብራሩም። ጠያቄው አብሯቸው ሲያወራ የነበረውም አበበ በለውም አላነሳባቸውም።

ይህ በንዲህ እንዳለ ትናንት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የነበሩት የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ከተማቸው በድንጋይና በአጠና ተዘጋግቶባቸው ነበር። በማህበራዊ ሚዲያዎች የታዩት ምስሎች እንዳመለከቱት ባህር ዳር ቆሻሻ ነበር። ጉዳዩን ከአብን ጋር የተያያዘ መሆኑ ደግሞ አብን ወዴት? የሚለውን እያጎላው መጥቷል።


Exit mobile version