Site icon ETHIO12.COM

የሰሜን ሸዋ የጸጥታ መዋቅር እየተመረመረ ነው፤ አማራ ክልል ዳግም መሪዎቹ እስኪሞቱ ጽንፈኞችን እንደማይታገስ ይፋ አደረገ፤

በአማራ ክልል ይህን መሰለኡ የተደራጀና ያታቀደ ጥቃት ሲፈጸም የጸጥታ መዋቅሩ አስቀድሞ ሊያውቅና ሊከላከል ሲገባው ይህንን ማድረግ ያልቻለበት ምክንያት በጥብቅ ምርመራ ስር መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል። ሃይል ከግንባር በማስመጣት ችግሩን መቆጣጠር እንደተቻለ ይፋ አደርገዋል።

አቶ አገኘሁ ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንዳሉት በተካሄደው አስከፊ ወነጀል ዙርያ መረጃ እየተሰበሰብ ሲሆን በጥፋቱ አመራሮች መሳተፋቸው ጥቆማ ደርሷል። በጥቆማው መሰረት ምርመራው እየተካሄደ ነው። በጥልቀት ይከናወናል። የጉዳቱ መጠንም በቀጣይ ይፋ እንደሚሆን አመልክተዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ከጥቂት ጉድለቶቻቸው በቀር የአማራን ህዝብ ክብር የመጠኑና ጨዋነትን የተላበስሱ እንደነበሩ ርዕሰ መስተዳደርሩ በመግለጫቸው ከምስጋና ጋር አስረድተዋል። በሌላ በኩል ግን የአማራን ህዝብ የማይወክል ተግባር መፈጸሙን ” ሊታወቅልን ይገባል” ሲሉ ገልጸዋል። ሲያብራሩም የሌሎችን ብሄርሰቦች ስም በመጥራት የተስተጋባ፣ ከጀርባው ገፋፊና ቆስቋሽ ያለበት፣ በሌሎች ክልሎች በሰላም የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን ለአደጋ አሳልፎ የሚሰጥ መግለጫ አውግዘዋል።



በቅርቡ ከኦሮሚያ ጋር በአጎራባች ዞኖች በህብረት የጸጥታ ስራ ለመስራት የተከናወነውን አበረታች መርጃ ከሰጡ በሁዋላ በሁሉም የኦሮሚያ ዞን የአማራ ተወላጆች አገሬ፣ መኖሪያዬ ብለው እንደሚኖሩ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል። ሌሎች ብሄሮች የኦማራ ወንድሞቻቸውን አቅፈውና አክብረው እየኖሩ ጥቂት አማራን የማይወክሉ ክፍሎች ሌላውን የሚያስቀይም መፈክር ማሰማታቸው ከቶውንም ተቀባይነት እንደሌለው በድጋሚ ” ይታወቅልን ” ሲሉ አመልክተዋል።

በክልሉ ላሉ ባለሃብቶች፣ ነጋዴዎች፣ ፖለቲከኞችና በማይታውቅ አደረጃጀት ላሉ ” እጃችሁን አንሱ” ሲሉ የተማጽኖ ማስጠንቀቂያ የሰጡት አቶ አገኘሁ፣ ካሁን በሁዋላ እንደቀድሞው አመራሮችን እስከምናጣ ድረስ አንታገስም” ሲሉ ገልጸዋል። በባህር ዳር የተሞከረውን ዝርፊያና ሁከት ዓይነት ተግባር እንደማይደገምም ተናግረዋል። ድርጊቱን በመቃወምና መልሶ በማጽዳት ለተከናወነው ተግባር ወጣቶችን አመስግነዋል። ረብሻውን የጀመሩት ክፍሎች ከባህር ዳር ውጪ ከሌላ ስራ መምጣታቸውን ገልጸው እንደሚጣራ አስታውቀዋል።

በጎነደር የተካሄደውን ስለፍ ” ስልጡን” ያሉት አቶ አገኘሁ፣ ትናንት በሰላም ስለፍ ተካሂዶ ዛሬ በባህርዳር ዝርፊያ እና የንግድ አገልግሎት የመዝጋት ሙከራዎች መደረጋቸውን አመልክተዋል። ምስኪን እህት ሻይና ዳቦ ሸጣ እለት ጉርሷን እንዳትሸፍን በዛሬ የኑሮ ውድነት መከልከሏ እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ ገልጸው እንዲህ ያለውን ድርጊት ተቃውመው ለውዳሴ፣ በተቃራኒ ለሽብር የተነሱትን ወደ ህግ መውሰድ ግድ መሆኑንንም ገልጸዋል።

የባህርዳር ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በትብብር በመስራቱ የከተማዋ እንቅስቃሴ ወደነበረበት መመለሱን በበጎ ያጎሉት አቶ አገኘሁ፣ የክልሉ ምሁራን፣ ወታቶች፣ ነጋዴዎች፣ ተቀናቃኞች፣ ሽማግሌዎች በማለት ዘርዝረው እርዳታ እንደሚሹ ተናግረዋል። ያለ ምንም ድብብቆሽ በአይከል ሱዳን ሰልጥኖ የገባ የቅማንት ጽንፈኛ ቡደን ከሁዋላ መተኮስ መጀመሩን ሲገልጹ ” አሁን ይህንን በምናገርበት ወቅት የቅማንት ጽንፈኛ ቡድን ሱዳን ሰልጥኖ ከጀርባችን እየወጋን ነው።

በመላው የክልላችን ድንበር የተበተነውን ጁንታ እያጸዳን ነው። በብዙ ጉዳይ ተውጥረናል” ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድርሩ “የመከለክያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ የኦሮሚያ ልዩ ሃይልና ፖሊስ መስዋዕትነት እየከፈሉ ነው ለዚህ ሙሉ እውቅና መስጠት ያስፈልጋል” ብለዋል። ኦነግ ሸኔ የሁሉም ህዝብ ጠላት መሆኑንም አመልክተዋል።

ሙሉውን ከቪዲዮው ያድምጡ ዛጎል ቲዩብን ሰብስካራይብ ያድርጉ


Exit mobile version