አማራ ክልል ኮሚሽነር አበረን አገደ፤ ” ከሁለቱም ወገን አሉበት”

የጸጥታ መዋቅር የት ነበር

የአማራ ክልል የፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙን ማገዱ ተሰምቷል። የአማራ ልዩ ሃይልና የአካባቢውም ሆን የክልሉ አተቃላይ የጸጥታ መዋቅሩ እንደሚጠይቅ ፍንጭ ተሰጥቶ ነበር። ወ/ሮ ሉባባ መኮንን የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በደረሰው ጉዳት ከሁለቱም ወገን እጃቸው ያለበት መኖራቸውን ይፋ አደረጉ።

ኮሚሽነሩ መታገዳቸውን ለአዲስ አበባ ተባባሪያችን የገለጹ እንዳሉት ኮሚሽነር አበረ ከመታገዳቸው ውጪ ስለመታገዳቸው ዝርዝር አልቀረበላቸውም። የደብረ ማርቆስ አካባቢ ተወላጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ አበረ በሰሜን ሸዋ የደረሰውን አስከፊ አደጋ ተከትሎ መታገዳቸው ቀደም ሲልም ከአካባቢው የልዩ ሃይል እንዲወጣ ተድርጎ ከደረሰው ጥቃት ጋር ስለመያያዙ አልታወቀም።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ከቀናት በፊት ” ይህ ሁሉ እስኪሆን የክልሉ የልዩ ሃይል፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻና የጸጥታ መዋቅር የት ነበር” ሲሉ ጉዳዩ እንደሚጣራ መናገራቸው ይታወሳል። አቶ አገኘሁ በግልጽ የመንግስት አካላት እጅ እንዳለበትም አመላክተው ነበር። ይህን ሲሉ ግን በዋናነት ኦነግ ሸኔና ጽንፈኞች ሲሉ ነበር የከሰሱት። የተቃወሙት። እንደ መሪም አጥፊዎች ለህግ እንደሚቀርቡ የገለጹት።

ይህ እስከታተመ ድረስ አቶ አበረ በሃላፊነታቸው ስራቸውን ሲሰሩ አልታዩም። መታገዳቸውንም ክልሉ ገሃድ አውትቶ አልተናገረም።

በሌላ በኩል የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር በአማራ ክልል ማስ ሚዲያ ቀርበው እንዳሉት /ከስር ያለውን ቪዲዮ 7 ደቂቃ ከ06 ደቂቃ ጀምሮ ያድምጡ/ በሸዋ ሮቢትም ተመሳሳይ ጥቃት ለመፈጸም ወረራ ሲደረግ የተባበሩ አካላት እንደነበሩ ገልጸዋል። አያይዘውም ተባባሪዎቹ ከሁለቱም አካላት መሆናቸውን ገልጸዋል። አያይዘውም ” የችግሩ ባለቤት ማን ነው” የሚለውም ከአጎራባች የአስተዳደር እርከኖች ጋር በሚደረግ ውይይት እንደሚለይ ገልጸዋል።

ዜናው ላይ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን ተጠያቂ አድርገዋሎ። ቢቢሲ የአጣዬ ጥቃት ላይ ነዋሪዎችን ጠቅሶ ” ሌሎች ህወሃቶች አጠቁን” ማለታቸውን እንደዘገበው የሸዋ ሮቢት ነዋሪው ” የጁንታው ሃይልም ይኖርበታል የሚል ጥርጣሬ አለኝ” ሲሉ ተደምጠዋል። ሙሉ ሃሳባቸው አለተላለፈም።

መከለካያ እንዳለው የተሟላ ትጥቅ አድርጎ የገጠመ ሃይል እንደሌለ ገልጿል። አራት አባላቱ መሰዋታቸውን አመልክቷል። በሰሜን ሸዋ የደረሰው ጥፋት በመላው አገሪቱ የተወገዘ፣ በተለይም በመላው አማራ እጅግ ቁጣን የቀሰቀሰ ጉዳይ ሆኗል። በዛው መጠን ጉዳይን የፖለቲካ ድል መጨበጫ ለማድረግ የሚደረገው ዘመቻና የሚዲያ ግብግብ ክልሉን እንዳያናጋውና ለጠላት እንዳያጋልጠው ፍርሃት አለ።


Leave a Reply

%d bloggers like this: