Site icon ETHIO12.COM

“ርዝራዥ ጁንታ”የተባለው ሃይል ወደ ሱዳን ሲሸሽ ተደመሰሰ፤ ለይለፍ የኦሮሞ ማንነት መታወቂያ አዘጋጅተው ነበር

የአገር መከላከያ ሰራዊት ” ርዝራዥ” ሲል የሚጠራውን ሃይል መደምሰሱን አስታወቀ። ሃይሉ የተደመሰሰው ድንበር አቋርጦ ወደ ሱዳን ለመሸሽ በሞከረበት ወቅት እንደሆነ ታውቋል። ከተገደሉት በፍተሻ ” የኦሮሞ ማንነት መታወቂያ ተሰርቶላቸው ነበር” ተብሏል።

የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት የጁንታው አባላት በከፍተኛ ዝግጅት ነበር ከአገር ለመውጣት ሙከራ ያደረጉት። ቀደም ባለው መግለጫቸው በዚሁ ሃይል ላይ በስምንት አቅጣጫዎች በተወሰደ እርምጃ የተርፈው ሃይል ተበታትኖ ከአገር እንዳይወጣ ስራ መሰራቱን አስታወቀው እንደነበር ይታወሳል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ፣ ርዝራዡ የጁንታው አባላት ወደ ሱዳን ሲሄዱ በቀላሉ ማለፍ እንዲችሉ ያዘጋጁት የኦሮሞ ማንነት እንዳላቸው የሚያስመስል መታወቂያ ነው። ከዚህም በተጨማሪ አለባበሳቸውን ቀይረው ነበር። ይሁን እንጂ አስቀድሞ በተዘረጋ ስልትና እቅድ መሰረት ሃሳቡ ሳያሳካ ቀርቷል። መከላከያ በክትትል ደርሶ እርምጃ ወስዷል። አብዛኞቹ ሲደመሰሱ የተቀሩት ወደ ጉድጓድ መጋታቸው ተገልጿል።

ወደ ሱዳን ለመግባት የተፈለገበት ዋና ምክንያት ሱዳን ተቀምጠው አገር ውስጥ ያሉትን ታጣቂ ሀይሎች በሽምቅ ውጊያ በማሰማራት ሀገር ለመበጥበጥ ባለው ዕቅድ መነሻ እንደነበር ሌ/ጄነራል ባጫ በመግለጫቸው አስረድተዋል። እርምጃ በተወሰደባቸው ሁሉም የጁንታው አባላት እጅ ላይ የሀሰተኛ መታወቂያ እንድተገኘባቸው አመልክተዋል።


Exit mobile version