Site icon ETHIO12.COM

ቄሮ ኦሮሚያን በተቃውሞ እንዲያምስ የቀረበለትን ማባበያ ውድቅ አደረግ፤ ” አንፈልግም”

በኦሮሚያ በሚታወቁ የወጣቶች አደረጃጀት ውስጥ በመግባት ክልሉን በሰላማዊ ስለፍና በሁከት ለመናጥ የቀረበውን ማበበያ አመራሮቹ ” አንፈልግም” ሲል እንዳጣጣሉት የኢትዮ12 ታማኝ የዜና ሰዎች አስታወቁ። በክልላቸው ካሁን በሁዋላ መሰረት ልማት እያወደሙ መቃወም እንደማይታሰብም አመልክተዋል።

ለቀደመው የወጣቶች አደረጃጀት ጥሪ ያቀረቡት መንግስት ለመጣል በውስን ጽንፈኞች የሚመራ መዋቅር አስፈጻሚዎችና በውጭ አገር የሚኖሩ ከእነዚሁ አካላት ጋር ግንኙነት ያላቸው ክፍሎች እንደሆኑ ያመለከቱት ክፍሎች ” አስፈላጊ ገንዘብና ቁሳዊ ድጋፍ እንሰጣችኋለን” እንደተባሉ ተናግረዋል። ከአገር ቤትና ከውጭ አገር እነሱን በሚቀርቡ አካላት አማካይነት ጥሪው እንደደረሳቸውም አመልክተዋል።

ለኦሮሞ የወጣቶች አደረጃጀት አመራሮች ቅርብ የሆኑት እነዚህ ክፍሎች ” በክልላችን ችግሮች አሉ። ቸግሮቹን ግን ያለንን እያጠፋን መቅረፍ አንችልም። ያለፉት ተቃውሞዎች ብዙ አስተምረውናል” ሲሉ ጥያቄውን እንደገፉት አስታውቀዋል። ኦሮሞ ሆነው ከህወሃት ጋር አሁን ህብረት የፈጠሩ ክፍሎች ” ጊዜው አሁን ነው” በሚል ወጣቱን እንዲያነሳሱ ሃሳቡ ሲቀርብ መስማታቸውን የቀድሞው ኡኦነግ ደጋፊና የዋሽንግቶን ዲሲ ነዋሪ አቶ ገመቹ ምስክርነት ሰጥተዋል። ምላሹ ምን እንደሆነ በግልጽ ባይሰሙም ኦሮሚያ በግልጽ አመጹን እንደምትቀላቀል የህወሃት ሰዎች ሲናገሩ መስማታቸውን ገልጸዋል።

በአማራ የተካሄዱትን ሰፋፊ ሰላማዊ ሰልፎች ተከትሎ ኦሮሚያ እንዲበጠበጥ ከፍተኛ ቅስቀሳ መካሄዱ ይታወሳል። የዜናው ሰዎች እንዳሉት እንደውም በኦሮሚያ ሰፊ የህብረትና የአንድነት ንቅናቄ እንደሚጀመር አመልክተዋል። ለዚህም ምክንያቱ ሰሞኑንን ጥፋተኛውን ሳይለይ በደፈናው ” የኛ መሬት ይመለሳል” የሚለው ማስፈራሪያና ማስተንቀቂያ ከተሰማ በሁዋላ ነው።

Exit mobile version