Site icon ETHIO12.COM

“በሌሊት ሰርጎ የገባ የጁንታው ርዝራዥ” የተባለ ሃይል በዋግኽምራ ጦርነት ከፍቶ መመታቱ ተሰማ

የጁንታው ርዝራዥ አበርገሌ ወረዳ ሰርጎ ለመግባት ያደረጋው ትንኩሳ በአማራ ልዩ ሀይል እና በአካባቢው የጸጥታ ሀይል አይቀጡት ቅጣት ተቀጥቶ ወደ ነበረበት ዋሻና ጫካ ትርፍራፊው መመለሱ ተገለጸ።

በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ ሚያዝያ 17 ቀን ለ18 /2013 ንጋት 11: 00 ሰዓት አካባቢ የጁንታው ርዝራዥ አበርገሌ ወረዳ ሰርጎ ለመግባት ያደረጋው ትንኩሳ በአማራ ልዩ ሀይል እና በአካባቢ የጸጥታ ሀይል አይቀጡት ቅጣት ተቀጥቶ ወደ ነበረበት ዋሻና ጫካ ትርፍራፊው መመለሱን የብሄረሰብ አስተዳደሩ ሰላም እና ህዝብ ደህንነት ም/መምሪያ ሃላፊ አምሳ አለቃ አዘዘው አዳነ ገለጹ።

ም/መምሪያ ሃላፊው እንደገለጹት የጁንታው ርዝራዥ የአማራ ልዩ እና የአካባቢው የጸጥታ አካላት ባልሸፈነው ቦታ ጨለማን ተገን በማድረግ ተመሳስሎ አበርገሌ ወረዳ ኒሯቕ ከተማ ላይ ገብቶ ከላይ በተገለጸው ሰዓት ጥቃት ለመፈጸም የሞከረ ቢሆንም በጀግናው እና አይበገሬው የአማራ ልዩ ሀይል እና በአካባቢው የጸጥታ ሀይል አይቀጡት ቅጣት ተቀጥቶ ወደ ነበረበት ዋሻና ጫካ ትርፍራፊው ተመልሷል ብለዋል።

በጀግናው እና በአይበገሬው በአማራ ልዩ ሀይል እና በአካባቢው የጸጥታ ሀይል አይቀጡት ቅጣት መቀጣቱን ያረጋገጠው የጁንታው ርዝራዥ የመሰሪነት ባህሪውን እና ተግባሩን ባልታጠቁ ንጹሀን ዜጎች እና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሶ ፈርጥጧል ብለዋል።በአበርገሌ ወረዳ ኒሯቕ ከተማ በጁንታው ትንኮሳ የደረሰ አካላዊም ይሁን ቁሳዊ ጉዳት ቀጣይ በተደራጀ ለህዝባችን የምናሳውቅ ይሆናል ያሉት ም/ሃላፊው አሁን አበርገሌ ወረዳ ኒራቕ ከተማ አንጻራዊ ሰላም የሰፈነ መሆኑን እና ጀግናው የአማራ ልዩ ሀይላችን እና የአካባቢ የጸጥታ ሀይላችን ብሎም የአካባቢው መላ ማህበረሰብ በመቀናጀት አካባቢው የጸጥታ ስጋት እንዳይኖር በንቃት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አምሳ አለቃ አዘዘው የአካባቢው ማህበረሰብ እንደተለመደው የጀግንነት ተግባሩን አጠናክሮ የጁንታው ርዝራዥ ትንኮሳን እጅግ ጀግንነት በተላበሰ ወኔ አካባቢውን ከሰርጎ ገቦችና ጸጉረ ልውጦች ነጻ በማድረግ የተለመደውን ሰላማዊ የእለት ተእለት ኑሮውን ተረጋግቶ እንዲያስቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል። ዘገባው የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው፡፡


Exit mobile version