Site icon ETHIO12.COM

“የአሜሪካ መንግስት ለምርጫ ጉዳይ አልላከኝም” ጄ ፍሪ ፌልትማን – አፍሪቃ ህብረትና አራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ምርጫ ይታዘባሉ

የኢትዮጵያን ምርጫ በተመለከተ የአሜሪካ የተወሰኑ ሴናተሮች ምርጫው እንዲራዘም ለልዩ ልዑክ ፊልትማን ደብዳቤ እንደተጻፈላቸው ተጠቅሶ ለቀረበው ጥያቄ “የእኔ ሚና ይህ አይደለም፣ የአሜሪካ መንግሥትም ለዚህ አልላከኝም” ሲሉ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጄ ፍሪ ፌልትማን የሚል ምላሻ እንደሰጡ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ።

ዲና ሙፍቲ የአውሮፓ ህብረት ስድስት አባል ያለው የቴክኒክ ቡድን እንደሚልክ ሲያስታውቁ ” ህብረቱ ለምን አቋሙን ቀየረ፟?” በሚል ለተጠይቁት ” ይህን ጥያቄ እነሱን ብትጠይቁ ይሻላል” ካሉ በሁዋላ ” የአሜሪካኖቹ መምጣት ገፋፍቷቸው ከሆነ አላውቅም ” የሚል የምጸት ምላሽ ሰጥተዋል። አውሮፓ ህብረት የአገሪቱን የምርጫ ቦርድ ህግ በሚጥስና የአገሪቱን ሉዓላዊነት በሚጻረር መልኩ የቪሳት ሳተላይት በማስገባት ታዛቢና ፈራጅ የመሆን ጥያቄ አንስቶ ” ወግድ ” ተብሎ ነበር።

ዲና ሙፍቲ እንዳሉት ህብረቱ አቋሙን የቀየረበትን ምክንያት እንዲያስረዳ በኢሜል ጥያቄ ብንልክም ይህ እስከታተመ ድረስ ምላሽ አልሰጠም። ይሁን እንጂ ህብረቱ የአገሮችን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህጎችን አክብሮ ምርጫ የመታዘብ ጥያቄ እንደሚያቀርብና ተግባሩን እንደሚወጣ ያዘጋጀውን የራሱን ህግ ለመጣስ ያነሳሳውን ምክንያት ” ሴራና በደቦ ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ዘመቻ አካል ነው” ሲሉ ለጉዳዩና ለህጉ ቅርብ የሆኑ ገልጸዋል። ከስር ኢትዮ ኢንሳይደር የዘገበውን ያንብቡ።

የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ አራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ለመጪው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢዎችን ለመላክ መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ ገለጹ። ቃል አቃባዩ ዛሬ ማክሰኞ በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ምርጫውን በዋናነት ይታዘባል ተብሎ ከሚጠበቀው የአፍሪካ ህብረት በተጨማሪ ሁለት የአሜሪካ እና አንድ የሩሲያ ተቋማት ታዛቢዎችን ወደ ኢትዮጵያ ይልካሉ። 

በአሜሪካ በኩል ምርጫውን ለመታዘብ ፍቃደኝነታቸውን የገለጹት ኢንተርናሽናል ሪፐብሊካን ኢንስቲትዩት (IRI) እና ናሽናል ዲሞክራቲክ ኢንስቲትዩት (NDI) የሚባሉ ተቋማት እንደሆኑ ዲና ተናግረዋል። ከሁለቱ የአሜሪካ ተቋማት በተጨማሪ የሩሲያ ሲቪክ ሶሳይቲ ተቋምም ታዛቢዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልክም ገልጸዋል። 

የአሜሪካው ናሽናል ዲሞክራቲክ ኢንስቲትዩት በአለም ዙሪያ ያሉ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለማጠናከር የተቋቋመ ተቋም ነው። ይህንንም ለማረጋገጥም የመንግስት ተጠያቂነት እና የህዝቦች ተሳትፎ ላይ አተኩሮ ይሰራል። ከተመሰረተ አራት አስርት አመታት ለመድፈን የተቃረበው ይህ ተቋም፤ ላለፉት 25 ዓመታት በተለያዩ ሀገራት የምርጫ ታዛቢዎችን ሲያሰማራ ቆይቷል። ተቋሙ በዚህ ዓመት ሜክሲኮ እና አልጄሪያን ጨምሮ በሌሎች ሀገራት የሚደረጉ ምርጫዎች ለመታዘብ እቅድ ይዟል።

ሌላኛው የአሜሪካ ተቋም ኢንተርናሽናል ሪፐብሊካን ኢንስቲትዩት፤ በዋናነት ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች መካከል የምርጫን ፍትሃዊነት ማረጋገጥ አንዱ ነው። እንደ ተቋሙ ይፋዊ ድረ ገጽ ከሆነ፤ ኢንስቲትዩቱ ከ1976 ጀምሮ በ59 ሀገራት ውስጥ የተካሄዱ 128 ምርጫዎችን የመታዘብ እና ድጋፍ የማድረግ ስራ ሰርቷል። ከእነዚህም ሀገራት ውስጥ ናይጄሪያ፣ ጋና እና ግብጽ ይገኙበታል።

መጪውን ምርጫ በዋነኝነት እንደሚታዘብ የተነገረለት አፍሪካ ህብረት በበኩሉ የታዛቢ ቡድኑን በሀገሪቱ ያሰማራል ተብሎ እንደሚጠበቅ በዛሬው የውጭ ጉዳይ መግለጫ ላይ ተጠቅሷል። ህብረቱ የምርጫ ታዛቢዎቹን የሚልከው በሰላም አስጠባቂ ተቋሙ በኩል እንደሆነም ተጠቁሟል።  

የአውሮፓ ህብረት ለምን ሀሳቡን እንደቀየረ ራሳቸው መጠየቅ አለባቸው ያሉት ዲና ሙፍቲ፤ “የአሜሪካኖቹ መምጣት ገፋፍቷቸው ከሆነ አላውቅም” ብለዋል። በዘንድሮው ምርጫ ታዛቢዎቹን እንደሚልክ አስቀድሞ አስታውቆ የነበረው የአውሮፓ ህብረት ዕቅዱን ባለፈው ሳምንት መሰረዙን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ህብረቱ ታዛቢዎችን እንደማይልክ ከገለጸ በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ስድስት አባላት ያሉበትን የባለሙያዎች ቡድን እንደሚልክ ማስታወቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።  

የአውሮፓ ህብረት የባለሙያዎች ቡድን ለመላክ የተስማማው፤ በኢትዮጵያ በኩል የአቋም ለውጥ ተደርጎ እንደው የተጠየቁት ዲና፤ “ኢትዮጵያ አሁንም አቋም አልቀየረችም” ብለዋል። “የሚመጡት ባለሙያዎች በዚያው አቋም ነው። አንደኛ ያ የተባለው መሳሪያ፤ ቪሳት ነው የሚሉት፤ አይመጣም። ሁለተኛ ከምርጫ ኮሚሽን አስቀድመው መግለጫ አይሰጡም” ሲሉ ቃል አቃባዩ ምላሽ ሰጥተዋል። 

የአውሮፓ ህብረት ለምን ሀሳቡን እንደቀየረ ራሳቸው መጠየቅ አለባቸው ያሉት ዲና፤ “የአሜሪካኖቹ መምጣት ገፋፍቷቸው ከሆነ አላውቅም” ብለዋል።

Exit mobile version