ETHIO12.COM

አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት ” ጁንታው” እጅ ሳይገባ ተያዘ

” ጁንታው በተከፋይ አክቲቪስቶቹ አማካይነት የሚረጨው የውሸት መሆኑንን መረዳት ያስፈልጋል” ሲሉ የድል ዜና ያበሰሩት የመከላከያ ሚኒስትር የሃይል ስምሪት ሃላፊ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ናቸው።

ሀገራዊ ሀላፊነት ተሰጥቷቸው በአሜሪካ ይገኙ የነበሩ ሹመኞች ሀገር የሰጠቻቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በማለት ሱዳን ካርቱም ከሚገኙ የጁንታው አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ወደ ሀገር ውስጥ የመገናኛ መሳሪያዎችና መድሀኒቶችን ለማስገባት ተንቀሳቅሰው እንደነበር ያመለከቱት ጀነራሉ። ሁሉም ተደምሠዋል ነው ያሉት። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሕዝብ ተከፋዮች ሌላ ወሬ እንደሚያወሩም አስታውቀዋል

ከጁንታው ሃይል መካከል ማይካድራ ላይ ጭፍጨፋ ፈጽሞ ወደ ሱዳን የሸሸው ሃይል አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ ወደ ሁመራ ሊገባ ሲል በጅግናው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት መደምሰሱን ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ተናግረዋል።

Related stories   ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

“ለወራት አሜሪካና ሱዳን ከሚገኙ የጁንታው አባላት ድጋፍ እየተደረገለት ስልጠና ሲወስድ የነበረው ይህ ወንጀለኛ ሃይል” በተደጋጋሚ ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ ሲያድረግ እንደነበር ተጠቁሟል። “ይሁን እንጂ” አሉ ጀነራሉ ” ይሁን እንጂ ይህ ሙከራቸው በተደጋጋሚ በመከላከያ ሰራዊቱ ሲከሽፍ ቆይቷል” ብለዋል።

ከተደጋጋሚ ሙከራ በኋላም በቁጥር 320 የጁንታው ሃይል በሃምዳይት ሁመራ በኩል ትጥቅና የተለያዩ መድሃኒቶችን ይዞ ሊገባ ሲል ተደምሧል። ገሚስ የሚሆን የተማረኩ መኖራቸውን ተናግረዋል። አያይዘውም አሁንም ከኋላ የቀረ ሃይል እንዳለ አስታውቀዋል። ብርጋዴር ጀኔራል ተስፋዬ መከላከያ ሰራዊቱ አሁንም ይህንን ቀሪአ ሃይል ለመደምሰስ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

Related stories   በአቡነ ማቲያስ መልዕክት ሳቢያ – ሲኖዶስ በመቆጣቱ አስቸኳይ ስብሰባ ተደርጎ የተግሳጽና የማስተካከያ መግለጫ ሊሰጥ ነው

ብዛት ያለው የሬዲዮ መገናኛ ፣ ሳተላይት ስልኮችና የተለያዩ መድሀኒቶች መያዛቸውንም አመልክተዋል። ጁንታው በተከፋይ አክቲቪስቶቹ የሚረጨው የውሸት ዜና ብቻ በመሆኑ ህብረተሰቡም ይህን እንዲገነዘብ ጥሪ አቅርበዋል። ጀነራሉ አልጠቀሱትም እንጂ በአካባቢው የድንበር እንቅስቃሴ በሳተላይት ካሜራዎችና በራዳር የጥቃቅን ካሜራዎች የሚጠብቅ በመሆኑ ስጋት እንደሌለ የአየር ሃይል አዛዥ መናገራቸው ይታወሳል።



Exit mobile version