በሱዳን የስደተኛ ጣቢያ ከ170 በላይ የሚሆኑት የጁንታው አባላት ላልተፈለገ እርግዝናና ለአባላዘር በሽታዎች መጋለጣቸው ተገለፀ

ወደ ሱዳን በመሸሽ በስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ከሚገኙ ሴቶች አብዛኞቹ ለእርግዝናና ለአባላዘር በሽታ መጋለጣቸውን ስደተኛ ጣቢያዎቹን በቅርበት የሚያውቁትና በመከላከያ ሰራዊት የተማረኩት የህክምና ባለሙያና ወታደራዊ አመራር የሆኑት ሻምበል ተክለወይኒ ታረቀ አጋለጡ።

የስደተኛ ጣቢያዎቹ በሚገኙበት አካባቢ ምንም ዓይነት የወሊድ መከላከያ ባለመኖሩና ወንጀል ፈፅመው ወደ ሱዳን የሸሹ የትህነግ ታጣቂዎች በስደተኞቹ ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንደሚፈፀሙና በዚህም ያልተፈለገ እርግዝናና የአባላዘር በሽታዎች መስፋፋታቸውን ሲታዘቡ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

ሻምበል ተክለወይኒ ታረቀ ትውልዳቸውና ዕድገታቸው በሰሜን ምስራቅ ትግራይ ታህታይ አዲያቦ በባድመ አካባቢ ሲሆን ከሰራዊቱ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ በግል የህክምና ስራ ሲሰሩ ቆይተው በ2011 ዓ/ም ጁንታው ባደረገላቸው ጥሪ የልዩ ሀይሉን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።

በልዩ ሀይሉም የ6ኛ ሬጅመንት ሀኪም በኋላም የሬጅመንቱ ምክትል አዛዥ በመሆን በአዲጎሹና በአብድራፊ ቀጥሎም ወደ ደደቢት በመሄድ በአቃቤ ሰሀት ፣ በአድዋ ፣ በተንቤንና በህንፃፅ የጥፋት ተልዕኮ ሲፈፅሙ መቆየታቸውን ገልፀው ፣ በውጊያው እንደማያሸንፉ ሲያውቁ የተወሰኑ ታጣቂዎችን ይዘው ወደ ሱዳን ቢሸሹም በቡድኑ አመራሮች አስገዳጅነት ሌላ ተልዕኮ በመስጠት ወደ ሀገር ቤት መላካቸውን ተናግረዋል።

በስደተኛ ጣቢያዎቹ ያለው ህይወት በጣም አስቸጋሪ መሆኑን የሚናገሩት ምርኮኛው ፣ ተገድባ በተባለው ካምፕ በአይን ተላላፊ በሽታ ብዙ ስደተኞች መጠቃታቸውንና በሱዳን በሚገኙት አራቱም የስደተኛ ጣቢያዎች ተቅማጥና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች በብዛት እንደሚታዩም ተናግረዋል።

ሻምበል ተክለወይኒ ከሱዳን በመነሳት ከጁንታው ተልዕኮ ተቀብለው ከሶስት መቶ በላይ ታጣቂዎችን በመምራት ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ሲሞክሩ በመከላከያ ሰራዊቱ መማረካቸው ይታወሳል።

ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ብዙአየሁ ተሾመ defence force Fb

Leave a Reply