Site icon ETHIO12.COM

እስራኤል ያነደደችው ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ ለምን?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ “ግንቦት 28 ቀን የድምጽ መስጠት እና ቆጠራውን አጠናቀን ምርጫውን መከወን እንደማንችል ተረድተናል” ማለታቸውን ቀድሞ አሶሴትድ ፕረስ ስጋና ደሙን ቀለቅሎ፣ ምኞቱ እንደሰመረለት አስቦ የዘገበው የሃሰት ዘገባ አነጋጋሪ ሆኗል።

እስራኤል ካነደድቻቸው ሚዲያዎች መካከል አንዱ የሆነው አሶሴትድ ፕረስ የሚባለው የአሜሪካ ሚዲያ የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ዋና ምክንያት ያለውን ሃሳብ አካቶ በስማ በለው የዘገበው ዘገባ እጅግ ሃሰት መሆኑንን ካውቀ በሁዋላም ቢሆን ለማስተባበል አለመሞከሩ የሚዲያውን አቋም ያሳየ እንደሆነ ዘላለም ሃይሌ ለዝግጅት ክፍላችን በላኩት መልዕክት ጠቁመዋል።

ነዋሪነታቸው አሜሪካ እንደሆነ ገልጸው ማስታወሻ የላኩት አቶ ዘላለም እንዳሉት አሶሲየትድ ፕረስ ምርጫው መራዘሙን ሲዘግብ፣ በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ምክያት ክልሉ ላይ ምርጫ ስለማይካሄድና የተወሰኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው አንሳተፍም በማለታቸው እንደሆነ በማመልከት ነው። አቶ ዘላለም ለድርጅቱ ኢሜል መላካቸውን ጠቁመው በኢሜል መልዕክታቸው ” ትግራይ የመራጮች ምዝገባ ሳይካሄድ እንዴት ምርጫ ይደረጋል” በማለት ጠይቀዋል። አይይዘውም የሚዲያው አዘጋጆች መታወአቸውን በዚህ ደረጃ ህዝብ እየታዘበው መሆኑንን ነግረዋቸዋል። ይህ እስከተጻፈ ድርሰ አቶ ዘላለም በኢሜል ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አላገኙም።

ምርጫው በተያዘለት ቀን ሊካሄድ እንደማይችል ይፋ ያደረገው ምርጫ ቦርድ እንደ ምክንያት ያቀረበው፣ የድምፅ መስጫ ወረቀት ህትመት ከተገመተው ጊዜ በላይ መውሰዱ፣ ለመራጮች ምዝገባ በተደጋጋሚ ተጨማሪ ጊዜ መሰጠቱና ለምርጫ ቁሳቁስና ሎጂስቲክ ስርጭት እንዲሁም ማጓጓዣ በቂ ጊዜ አስፈላጊ መመደብ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ከዚህም በላይ በአንድ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ ቀደም ሲል ሶስት የነበሩትን የምርጫ አስፈፃሚዎች ቁጥር እንዲጨምር በማስፈለጉ እንደሆነም ታውቋል። ምርጫ ቦርድ በወይዘሪት ብርቱካን አማካይነት ይህንን ብሎ ሲያበቃና በሃስቡ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ቅሬታ ሳያቀርቡ አሶሴትድ ፕረስ እንደ ምክንያት ያቀረበው የምኞት ዜና ሆኖ ተገኝቷል።

የጀርመን ድምጽ “ሊራዘም ይችላል” የተባለውን ምርጫ ” የኢትዮጵያ ምርጫ ግንቦት 28 አይካሔድም” ሲል ዕርዕስ ሰጥቶ ዜናውን ከባህር ማዶ አጉኖታል። ውስጡ ግን ” ሊራዘም ይችላል” የሚል ሃሳብ በግልጽ ተቀምጧል። ከዚ አንሳር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ምርጫ ማካሄድና ሁለተኛውን ሙሌት ማካሄድ የሁላችንም የትኩረት አቅጣጫና በሕብረት ርብርብ የሚደረገበት ዋና ጉዳይ ነው። ይህንን ካሳካን ብልጽግናችንን አወጅን ማለት ነው” ሲሉ የተናገሩበት ምክንያት ግልጽ አመላካች እንደሆነ ያሳያል።

ኢትዮጵያ ላይ ሚዲያዎች፣ ያደጉት አገራትና የውስጥ ተላላኪዎች በመናበብ ዘመቻ እያፋፋሙ እንደሆነ በተደጋጋሚ መገለጹ አይዘነጋም። ሕዝብም ከመቼውም ጌዜ በበለጠ ነገሩ እየገባው የዛሪውን ችግሩን ነገን በማየት ተቋቁሞ አገሩ ላይ የተቃታውን ዘመቻ እየመከተ እንደሚገኝ እየተገለጸ ነው።


Exit mobile version