ETHIO12.COM

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የእዉቅና እና የምስጋና ፕሮግራም በደማቅ ስነ ስርአት ተከበረ

ፕሮግራሙ የወልቃይት ህዝብ ያለ ማንነቱ በጉልበት በአሸባራው ትህነግ ተገዶ ወደ ትግራይ ተካሎ ከነበረበት ዘመን በመስዋእትነት እና በእልህ አስጨራሽ ትግል ተላቆ ወደቀደመ አማራዊ ማንነቱ ከመመለሱ ጋር በተያያዘ ለዚህ ክብር ያበቁ የደከሙ፥ የተዋጉ እንዲሁም ክቡር መስዋእትነት ለተቀዳጁ ሁሉ እዉቅና እየተሰጠ እና ምስጋና ቀረበ ።

የምስጋና እና የእዉቅና ፕሮግራሙን የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የወልቃይት ጠገዴ ዞን ም/አስተዳዳሪ እንዲሁም የዞኑ የጸጥታ ሐላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ በእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስጀመሩ ሲሆን ለዚህ የማንነት ትግል ክቡር ህይወታቸዉን ለሰዉ ሁሉ የህሊና ጸሎት በማድረግ ፕሮግራሙን ይፋ አድርገዉታል

ኮሎኔል ደመቀ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸዉ የወልቃይት ህዝብ ለሶስት አሰርት አመታት ያለማንነቱ ባእድ ማንነት ተጭኖበት እንደከረመ የገለጹ ሲሆን ዛሬ ግን ለዘመናት ታፍኖ የነበረዉን አማራዊ ማንነት በቀያይና ጠያይም ልጆቹ መስዋእትነት ወደቀደመ አማራዊ ማንነቱ ተመልሷል ብለዋል። በመሆኑም በዚህ ስኬት ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናቸዉን አስተላልፈዋል።

ኮሎኔል ደመቀ በንግግራቸዉ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በልማትና በመልክአ ምድር አቀማመጥ እጅግ ምቹ እና የቀጠናዉ የልማት ኮሪደር በመሆኑ ለአከባቢዉ ሰላም ትኩረት ሰጥተን መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።

ኮሌኔሉ አክለዉ እንደገለጹት ትናንት የታየዉ ወልቃይትን ነጻ የማዉጣት ርብርብ ዛሬም በሰላም እና በልማቱ እንደሚያስፈልግ የገለጹ ሲሆን በባጀት ያለመለቀቅ ችግር ተገቢዉ የልማት የትምህርት እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንዳይካሔዱ እንቅፋት ሆነዋል ብለዋል።ስለሆነም በዞኑ ያሉብንን ችግሮች ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ተገቢዉን ሁሉ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ብለዋል።

በመጨረሻም ኮለኔል ደመቀ ለወልቃይት ህዝብ ማንነት መመለስ ድምጽ ለሆኑ ሁሉ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ክብርና ሞገስ ለዚህ የነጻነት ትግር ህወታቸዉን ለሰዉ ሰማእታት በማለት መልእክታቸዉን ቋጭተዋል።

ከኮሎኔል ደመቀ በመቀጠል አቶ አሸተን ደምለዉ የወልቃት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለትግሉ ሰማእታት ምስጋናቸዉን ያቀረቡ ሲሆን የወልቃይት ህዝብ ገና ትህነግ አገር መምራት ስትጀምር ነበር ትግሉን የጀመረዉ ብለዋል።

እንደ አቶ አሸተን ንግግር የወልቃይት ህዝብ በሰላማዊ ትግል ማንነቱን ሲጠይቅ የቆየ መሆኑን የገለጹ ሲሆን አፋኙ ትህነግ አፈና ባህሉ በመሆኑ የህዝቡን ድምጽ አፍኖት ቆይቷል ብለዋል።

በመጨረሻም ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና ለአማራ ልዩ ሐይል እና ህዝባዊ ሚኒሻ ምስጋናቸዉን ያቀረቡ ሲሆን የብልጽግና መንግስት የተመለሰዉን የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ህጋዊ እንዲያደርግላቸዉ እና የዞኑ ባጀት በፍጥነት እንዲለቅላቸዉ አጽንኦት ሰጥተዉ ጠይቀዋል።

የርእሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ በፕሮግራሙ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ክቡር ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በአስቸኳይ ስራ ምክንያት መገኘት አለመቻላቸዉን እና እሳቸዉን ወክለዉ መልእክት እንደሚያስተላልፉም ገልጸዋል።

አማካሪዉ የትህነግን ጨፍላቂነት እና ተስፋፊነት እንዲሁም በአካባቢዉ ያከናወነዉን ዘግናኝ ጭፍጨፋ አንድ በአንድ ዘርዝረዉ ያቀረቡ ሲሆን ዛሬ ግን አንዷን የማይካድራ ጭፍጨፋ ለአለም ማሳወቅ ባለመቻላችን ተበዳዮች በዳዮች ተብለን በትህነግ ፕሮፖጋንዳ ተጠልፈዉ እነ አሜሪካ መግለጫ እያወጡብን ይገኛሉ ብለዋል።

ስለሆነም በመላዉ አለም የሚገኘዉ የአማራ ምሁር ባለ ሃብት እና ማንኛዉም ተጽእኖ ፈጣሪ አካል ትህነግ በአማራ ህዝብ ላይ ያደረሰዉን ግፍ በማሳወቅ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን “ከተከዜ ወሰናችን ንቅንቅ አንልም” በማለት በወያኔ ግፊት በምእራባዉያ እየተካሔደ የሚገኘዉን ሴራ ዋጋ ቢስ ነው ብለውታል።

በፕሮግራሙ የእምነት አባቶች በመገኘት ከትህነግ ሰቆቃ ተላቆ ለዚህ ነጻነት የበቃዉን ማ/ሰብ እንኳን ደስ አለህ ብለዋል።

Exit mobile version