Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደምትመረመር አሳሰበች

የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ኢትዮጵያ ከአሜሪካን ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት መልሳ እንድትገመግም ያስገድዳታል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በአሜሪካ መንግስት የተላለፉ የቪዛ ገደቦችና መሰል ውሳኔዎች የአገራቱን የተጠናከረ ወዳጅንት ከመሸርሸሩ ባለፈ ኢትዮጵያ ከአሜሪካን ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት መልሳ እንድትገመግም እንደሚያስገድዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩ በአሜሪካ መንግስት የተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ ጋር ያለውን ግኝኙነትና ትሥሥር በአዎንታዊ ደረጃ አጠናክሮ እያራመደ ባለበት፣ የሀሉትዮሽ ግንኙነቱንና ትስስሩን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ባለበት ወቅት፣ እንደዚህ አይነት ውሳኔዎች መሰወሰኑ አገባብነት የጎደለው መሆኑንን  ተገቢነት የውጭ ጉዳይ መግለጫ ያትታል።

መግለጫው ውሳኔው አግባብ አለመሆኑንን አምለክቶ እንዳለው “ አሜሪካ የውሰነሽው የቪዛ ማዕቀብ የሁለቱን አገሮች የረጅም ጊዜ የተጠናከረ ወዳጅነት የሚሸረሽር ተግባር ነው” ብሏል።

የሁለቱን አገሮች ጠንካራ ግንኙነት በሚያሳይ መልኩ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በቅርቡ የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክትኛ ተደርገው ከመጡት ጄፍሪ ፌልትማን ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ምክክር ማካሄዳቸውን መግለጫው በበጎ ጎኑ አንስቷል።

በተጨማሪም በአገሪቱ አዲስ የፖለቲካ ሽግግር ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀውን ብሔራዊ ምርጫ ለማካሄድ ኢትዮጵያ እየተዘጋጀች ባለበት፣ የአሜሪካን ድጋፍ በምትጠብቅበት በዚህ ወቅት በምርጫው ላይ መጥፎ ጥላ ሊያጠላ የሚችል ውሳኔ ከጅምሩ መታሰብ አልነበረበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል።

አሜሪካ ያደረገችው የቪዛ ክልከላም የአገሮቹን የረጅም ጊዜ የተጠናከረ ወዳጅንት የሚሸረሽር ተግባር መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፣ መንግስት የኢትዮጵያን ብልጽግናን ለማሳካት ከመላው የህብረተሰብ ክፍል ጋር ብሔራዊ ምክክርን እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፤ ይህም እየሆነ ያለው ያለማንም የውጭ አማካሪ አመልካችነትና ትዕዛዝ እንዳልሆን ጠቅሷል።

ከላይ ያነሳቸውን ነጥቦች ካስረዳ በሁዋላ መግለጫው ቀደም ሲል የመንግስትን አቋም ግልጽ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ዛሬም በድጋሚ “መንግስት በአሸባሪነት ከተፈረጀው ህወሃት ጋር በምንም አይነት ሁኔታ አይደራደርም” ብሏል። አያይዞም “ የሽብር ቡድኑን እንደገና ለማነቃቃት የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ሙከራ ውጤታማ የማይሆንና መንግስት የማይታገሰው ጉዳይም ነው” ሲል አቋሙን ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ቀደም መንግስት በግልጽ እንዳስታወቀው፣ አሁንም አሜሪካ በውስጥ ጉዳይ ላይ የምታደርገው ጣልቃ ገብነት ተገቢነት የሌለውና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጾ፣ “ ኢትዮጵያን ማንም የውስጥ ጉዳይዋን እንዴት እንደምታስኬድ የሚያሳያት አካል ሊኖር አይችልም” ሲል አስታውቋል።

መንግስት በትግራይ የሰብአዊ ድጋፍ ለመስጠት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እና ቁርጠኝነቱን በማሳወቅ ያልተቋረጠና የሙሉ ጊዜ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም መግለጫው አመልክቷል። በአሜሪካ መንግስት የተላለፉ የቪዛ ገደቦችን እና ሌሎች ጉዳዮች የሁለቱን አገራት ለዘመናት የቆየ ገንቢ ትስስርን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ ውሳኔ ነውም ሲል አስገንዝቧል።

ይህን መሰል ጫናዎች ከቀጠሉ ለዘመናት የቆየውን የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነቶች የሚጎዳ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካን ጋር ያለውን ሁለትዮሽ ግንኙነት መልሶ እንዲገመግም የሚገደድ ይሆናል ብሏል።

በመጨረሻም መግለጫው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያጋጠሟትን ችግሮች በሕዝቦቿ አንድነትና ድጋፍ በመሻገር ሰላሟን አስጠብቃ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ ትቀጥላለች ብሏል።


Exit mobile version