አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድርጅቶች የመረጃ መረብ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዳልሆነና የፖሊሲ አውጭዎች በትኩረትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡የበይነ መረብ ግንኙነት እየጨመረ መምጣት፣ በመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ ዝቅተኛ የዲጂታል እውቀት፣ የመረጃ መረብ ጥበቃ ባለሙያ እጥረት፣ ፍቃድ የሌላቸው ሶፍትዌሮችን መጠቀም የአፍሪካን የመረጃ መረብ ለመንታፊዎች እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡ ስለሆነም አፍሪካ ምነታፋውን እልባት ለማስያዘ ይቻል ዘነድ በህብረት መስራት እንዳለባት ኢትዮጵያ ጠይቃለች።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ ላይ አፍሪካዊያን ፖሊሲ አውጭዎች የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በትብብር እንዲሰሩ ጠይቃለች፡፡10ኛው አለም አቀፍ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ-አፍሪካ 2021 በበይነ መረብ እየተካሄደ ነው፡፡
ስብሰባው በመረጃ መረብ ደህንነትና የዲጂታል ጠላፊዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየመከረ ነው፡፡የአፍሪካን የመረጃ መረብ ደህንነት ሁኔታ ያብራሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሃመድ (ፒ ኤች ዲ) አፍሪካ በበይነ መረብ ግንኙነት ተደራሽነት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ብትሆንም በመረጃ መረብ መንታፊዎች በአመት እስከ 3.5 ቢሊየን ዶላር እንደምታጣ ተናግረዋል፡፡
ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት በ469 ሚሊዮን ገደማ የሞባይል መጠቀሚያዎች 456.3 ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ዝውውር እንደሚፈፀም ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህ እያደገ የመጣው የሞባይል የገንዘብ ዝውውር የመረጃ መረብ መንታፊዎች አይን ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል ብለዋል፡፡
አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድርጅቶች የመረጃ መረብ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዳልሆነና የፖሊሲ አውጭዎች በትኩረትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡የበይነ መረብ ግንኙነት እየጨመረ መምጣት፣ በመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ ዝቅተኛ የዲጂታል እውቀት፣ የመረጃ መረብ ጥበቃ ባለሙያ እጥረት፣ ፍቃድ የሌላቸው ሶፍትዌሮችን መጠቀም የአፍሪካን የመረጃ መረብ ለመንታፊዎች እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካን የበይነ መረብ ደህንነት ለማስጠበቅ ከአፍሪካ 2063 አጀንዳ ጋር በተጣጣመ መልኩ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንም አብራርተዋል፡፡ በሂደት ላይ ያለው የአፍሪካ የአይ ሲ ቲ አድገት ህግና ፖሊሲ፣ የኢንተርኔት መንግስት ሰነድ መዘጋጀቱ፣ የመረጃ መረብ ደህንነትና የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ (ማላቦ ኮንቬንሽን)፣ የመረጃ ደህንነት ዳሰሳ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን መጥቀሳቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ዓለም አቀፉ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ ትኩረቱን የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ አድርጎ በየአመቱ የሚካሄድ ስበሰባ ነው፡፡
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን ለጎን የትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞን አስተዳዳሪዎች የተባሉ ሁለት ዓይነት መረጃዎች እየሰጡ ነው። መንግስት ግን ስምምነት መኖሩን ዘርዝሮ እነሱ በሚሉት መልኩ ባለመሆኑ ” ትዕግስት ፍርሃቻ አይደለም” እያለ ነው።ከትናንት በስቲያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ እና… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና የሚያቀብሉና እነሱኑ የሚከተሉ ስምምነቱ መክሸፉንና መንግስት ውሉን እንደተወው፣ የሶማሌ ማንግስትም መንግስት በአደባባይ ስምምነቱን ማቆሙን እንዲያውጅ እንደሚያደርግ አስታውቀው እንደነበር ይታወሳል። ሌሎች አገራት ከሶማሌላንድ ጋር መሰል ስምምነትን ሲያደርጉ ዝምታን የመረጡ፣ የግብጽን፣ የኤርትራንና የሶማሌን የተቀነባበረ ሴራ ተከትለው ኢትዮጵያ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ዋስትና አፀና። ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ ከሀገር እንዳይወጡ እግድ እንዲጣል ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተጠርጣሪዎቹ የቀድሞ የህዝብ ትራንስፖርት የተሽከርካሪ ዘርፍ ኃላፊና የትራንስፖር ሎጂስቲክ ሚኒስትር አማካሪ የነበሩት ከድልማግስት ኢብራሂም፣ የትራንስፖርት ማህበራት አመራርና አባል ታምራት በየነ፣ ጌትነት በየነ እንዲሁም የመናኸሪያ የትራንስፖርት ስምሪት ኃላፊዎች… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹን መልሶ ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን ካውንስሉ ባደረገው ግምገማ ስለተገነዘበ” ነው። “የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ዜጎችን መልሶ ለመውሰድ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም” በማለት የካውንስሉ መግለጫው ያብራራል። የአስቸኳይ ጊዜ የጉዞ ሰነዶች በመስጠት እንዲሁም በፍቃድ እና ያለ ፈቃድም የሚደረግ… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረውየሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን ያስቸግራል … አንባቢ ስም ይስጠው። እኔ ስጽፈው ግን በሃፍረት ስሜት ነው። ያፈርኩት ደግሞ በደርስንበት የሞራል ውድቀት ነው። እንደ ማህበረሰብ ይሁን እንደ ቡድን በውል ባላውቅም ግን ወድቀናል። የወደቅንበት የሃፍረታችን ገደል ርቀቱ እንዲሁ በቀላሉ የሚወጣበትም አይመስልም። ሃፍረቴና ተስፋዬ በኩል ደረጃ እየተናነቁኝ ስለ አብሮ አደጎቼ ጻፍኩ።… Read more: “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው