ETHIO12.COM

በጥብቅ ሲፈለጉ የነበሩ የአሸባሪው ህወሃት ቡድን አባላት ጅቡቲ ላይ በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ ገቡ

አገሪቱን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እና በጥብቅ ሲፈለጉ የነበሩ የአሸባሪው ህወሃት ቡድን አባላት በጅቡቲ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አመሻሹ ላይ አዲስ አበባ መግባታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በትግራይ ክልል በሰሜን ዕዝ ላይ እና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሰው ወደ ጎረቤት ሀገር ከሸሹ የአሸባሪ ቡድኑ አባላት መካከል 1ኛ.ሀብቶም ገብረስላሴ ወልዩ፣ 2ኛ. መሰለ ታመነ እሼቱ እና 3ኛ. ኮነሬል መሀመድ በሪሁ ኑር የተባሉት የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች በጅቡቲ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉትን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተጠርጣሪዎችን ተረክቦ ጉዳዩን በህግ አግባብ የሚያጣራ መሆኑን ገልጿል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የደህንነትና የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት በተለያዩ ጊዜያት በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው መያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸውን የህዋሃት አመራሮችና የጦር መኮንኖችን ከተደበቁት ስፍራ በማደን ለህግ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል። via ኢዜአ)

Exit mobile version