Site icon ETHIO12.COM

በሃሰት መረጃ አገር ማተራመሱ የሚቀጥል ነው፤ “ህዝብ ሆይ ሃሰት እየሸመትክ አገርህን አታሸብር”

ቢቢሲ ይህን ” በቅጥፈት ተለቃቅሞ ተሰራ” የተባለውን መረጃ አየር ላይ ሲያውል የቀደመው አልነበረም። የግብጽ አፍ የሆነው አልሃራምም ሃሰተናውን መረጃ ለገበያ ለማቅረብ ተጣድፎ ነበር። ሁለቱም ዛሬ ድረስ ይቅርታ አልጠየቁም። ዘመቻው እንግዲህ እንዲህ አይን ያወጣ፣ ጥርሱን ያገጠጠ መሆኑንን ያረጋግጣል። ገና ዘመቻው ይቀጥላል።

ኬሎ ሚዲያ ደግሞ ጃዋር ከመሰረታቸው በግብጽ የሚተዳደርና የሚነዳ ተቀጣሪ ሚድያ አንዱነው። ይህን መረጃ ቀዶና ሰፍቶ ያዘጋጀለት ደግሞ ትህነግ ነው።

ትህነግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተለያዩ ወቅቶች የተናገሩትን ሃሳብ ለውቅቱ ማተራመሻ በሚመጥን መልኩ ገጣጥሞና ከሽኖ ለኬሎ ሚዲያ የሰጠው የትህነግ ሚዲያ በሌሎች ፍጹም እምነት ስለማይጣልበት ነው።

1.4 ደቂቃ የሚፈጀ የቅጥፈት መረጃ ሃሰት እንደሆነ ቢቢሲም ሆነ አልሃራም ጠንቀቀው ያውቃሉ። እንግዳ ጉዳይም አይደለም። እነሱ ብቻ ሳይሆን በትህነግ ጎራ የተሰለፉት የቲውተር ሰራዊቶችም ጉዳይን በደንብ ተረድተው፣ ሃሰት መሆኑ እየገባቸው ነው ሲያሰራጩ የነበረው።

አልሃራም በእንግሊዘኛ ለዓለም ሚዲያና ህብረተሰብ፣ በተለይም ዘመቻ እያቀጣጠሉ ላሉት መረጃ ሲሰጥ።

‘I would rather die than hand over power to them’: Ethiopian PM Abiy Ahmed in reported leaked audio ብሎ ርዕስ ሰጥቶ ነው።፡አልሃራም ከኬሎ ሚዲያ ወስዶ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ” ስልጣኔን ከምሰጣቸው ሞቴን እመርጣለሁ ብለዋል” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ለዓለም ዜናውን ሲያራባ፣ መንግስት በመረጃ አስደግፎ ሃሰት መሆኑንን ይፋ ያደረገበት ሰነድ እጁ ላይ ነበር። እኔ በግል ልኬላቸዋለሁ።

ኬሎ ሚዲያ በዩቲዩብ በዋናነት መሰረቱን ከተከለበት ግብጽና በግልጽ አድራሻቸው ከማይታወቁ ተባባሪዎቹ፣ እንዲሁም ከትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋር በመናበብ የሚሰራ ሚዲያ ነው። ኬሎ ሚድያ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከተቋቋሙ ሚዲያዎች መካከል አንዱ ነው። የዲጂታል ወያኔ ሚዲያዎች አካል የሆነው ይህ ሚዲያ ጃዋር በውጭ አካላት ድጋፍ ካቋቋማቸው ሚዲያዎች አንዱ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ግብጽ እንደምትደጉመው አውቃለሁ። የዛሬን አያድርገውና ሲዶለት ነበርኩ። አካሄዱ ከትህነግ ጋር የሚሞዳሞድና ኦሮሞ ላይ ክህደት የመፈጸም ሴራ ያነገበ ሆኖ ስላገኘሁት ለመራቅ ተገድጃለሁ። ስለ ክህደቱ ብዙ ማለት ይቻላል ግን ለጊዜው ልለፈው።

የተቋቋመበት ዓላማ ብዙ ቢሆንም ባስቸኳይ ለሕዝብ እንዲሰራጭ አሁን ስለተራባው ሚዲያና በመጪው ምርጫ ላይ ብዥታ ለመፍጠር የተፈለገበትን ምክንያት ልጠቁም።

በኢትዮጵያ ላይ ሁሉም ነገር ቢደረግም ሊሳካ ባለመቻሉ አሁን የተያዘው የመጨረሻው አማራጭ ምርጫውን ማበላሸት ነው። በዚሁ ሚዲያ ምርጫውን ባለቀ ሰዓት ለመሰናበት የተዘጋጁና ዓለም በተለይም ሃያላኖቹ ምርጫውን እውቅና እንዲነሱት እየተሴረ ያለ ሴራ አለ። ይህ ሴራ ይበልጥ ጉልበት አግኝቶ ተግባራዊ እንዲሆን በቂ ምክንያት ያስፈልጋል።

ምርጫው ተበላሽቶ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም፣ ወያኔና ዛሬ ላይ በይፋ ወያኔንን እንደሚደግፉ፣ አብረው እንደሚሰሩ እየገለጹ ያሉት የኦሮሞ ታዋቂ ፖለቲከኞችና ጃዋርን ጨምሮ፣ በረከት ያቋቋመው የአማራ ድርጅት ተብዬ፣ ሌት ተቀን አገር ባማተራምስ ላይ የተመሰረተ ሚድያ የሚነዱትና ከሃዲው ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የሽግግር ጊዜ ሲቋቋም በዛው ኢትዮጵያን ” ደህና ሰንብቺ” ለማለት ግብጽ ኪሷን ገልብጣ፣ እጇን አርዝማ እየሰገረች ነው።

ግብጽ በምታፈነድደው መጠን ዋጋዋን ለመክፈል ደፋ ቀና የሚሉት ባለጠጎቹ ” ምርጫው ይቅርና ሁሉን ያካተተ የሽግግር መንግስት ይመስረት” ለሚለው መሰሪ አካሄዳቸው ድጋፍ ይሆን ዘንድ የብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ሲቀመጥ ድራማው ተሰራ። ስብሰባው ሲያልቅ ” አፈትልኮ የወጣ” በሚል ተቆራርጦ የተቀጣጠለው መረጃ ይፋ ሆነ። ኬሎ ሚድያ ይህን ሲይደርግ ዲቃላዎቹ ያለምንም ማመንታት ተቀባበሉት። የግብጽ ሚዲያዎች ለዓለም ገበያ ተጠቀሙበት።

የሚገመው ሃሰት መሆኑ ይፋ ከሆነና መረጃው ለማተራመስ ተግባር የተፈጸመ መሆኑንን ያወቁት ሚዲያዎች ማስተባበያ እንኳን አልሰሩም። በተፈጥሮ ሞት የሞቱትን አበረ አዳሙን ” ተገደሉ” ብለው የሰሩ ሚዲያዎች ከታማኝ ሃኪሞች ትክክለኛ ምስክርነት ሰምተው በቅጥፈታቸው እንደቀጠሉት ሁሉ የግጽ ሚዲያዎችም በተመሳሳይ ” ካፈርኩ አይመልሰኝ” በሚል ተላልኪያቸው ያጎረሳቸውን ዜና እንደሰቀሉት ነው።

የአባይን ግድብ መሙላትና ምርጫውን በትጋት ማስጨረስ ሁለት አበይት ጉዳዮች እንደሆኑ አስረግጦ በማስታወስ የተቋጨውን ስብሰባ “ስልጣኔን ከለቀኩ ሞቻለሁ፤ ምርጫውን አሸንፈናል” በሚሉ የሸፍጥ መልዕክቶች ለቃቅሞ ኬሎ ሚድያ ባዘጋጀው የሃሰተኛ መልዕክት እንደተዘጋ አድርጎ ሲያቀርበው አሳዛኙ ኤትዮጵያዊ ነን የሚሉ ሳያታሩ ይህንን ክፋት ማሰራጨታቸው ነው።

አንዱ ሲከሽፍ ሌላም የተዘጋጀ ድራማ ስለሚኖር ኢትዮጵያዊያን ልባቸውን እንዲጠብቁና የሚሰጣቸውን እንዲመረመሩ ሃሳብ ለመስጠት ይህቺን ብያለሁ። ልብ ያለው ልብ ይበል። ነካከተው ነካክተው አገር አልባ ሊያደርጉን ነውና እንጠንቀቅ። በተለይም ከኬሎ ሚድያ ጀርባ ያሉትን ባንዳዎች፣ ሚዲያውን ያቋቋመውን ተከፋይ፣ እንዲሁም የተከፋዩን ሃብት በስሙ የሚያነቀሳቅሰው ሰው ከየት የመጣ እንደሆን መርምሩ። በኢሬቻ በዓለ ላይ “ዳውን ዳውን ወያኔ ያለው ልጅ የትሄደና አመለጠ? ከዛ የሱ ወንድም እንዴት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ኦ ኤም ኤን ገንዘብ ቤት ሆነ? ከጃዋር ጋር ምን አገናኛቸው? ኦኤም ኤን በይፋ አገር ቤት እንደልቡ እየሰራ ባለበት ሁኔታ ለምን ኬሎ ሚድያን ግብጽ ላይ መትከል አስፈለገ? የዚህ ሁሉ ወጪ ምንጩ ማን ነው? ይህን መርመሩ።

ይህ ብቻ አይደለም ኬሎ ሚዲያ ይህን ቅጥልጥል ማስረጃ ብሎ ከማቅረቡ በፊት ጃዋርና ሌሎች የታሰሩ እንዲፈቱ ለመደራደር መሞከራቸውን ሲያትቱ ነበር። በዓለም ላይ የትኛው ሚዲያ ነው ” እገሌ ካልተፈታ ይህን መረጃ እለቃለሁ” ብሎ የሚጠይቅ? ያስገርማል፤ ያሳዝናል ደግሞም ያዝናናል።

በቅርብ ሌሎችም መረጃዎች እንደዚሁ እየተፈበረኩ ሊበተኑ ይችላሉ። ምን አልባትም ከዚህ በባሰ መልኩ በወንድማችን ሃጫሉ የተቀነባበረ ግድያ ወቅት አንዱ ሌላውን እንዲያጠፋ ሲደረግ እንደነበረው ቅስቀሳ ዓይነትም ሊሆን ይችላል። ኦሮሞን የእሳቱ ማቀጣጠያ ሜዳ ለማድረግ እየተሰራ ነውና ልብ እንበል፣ እንጠንቀቅ።

“እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” ጨዋታው ዛሬም ድረስ የሚደበድበውን ታርጌት አልሳተም። አብይ አህመድ ተለይተው የሚደበደቡት ለምን ይሆን? እሳቸውን ለመደብደብ እንዲመች አብረዋቸው የነበሩት ወገኖችና የለውጥ ሰዎች ለምን እንዲለዩዋቸው ተደረገ? ማንስ እንዴት ለያቸው? ወደፊት እመለስበታለሁ።ለዛሬ በችኮላ ይህን ካልኩ የግብጹ አፍ ያለውን ላክልና ላብቃ።

In a tweet, the Ethiopian prime minister’s office said the reported leaked audio of Ahmed during the Prosperity Party meeting last week was a “fake audio compilation put together by drawing on different unrelated remarks made by the PM.

‘No one will be able to form a government in the coming 10 years,’ Ahmed said, according to the reported audio file leak from last week, the authenticity of which was denied by the office of the PM on Monday

ጋዜጣ ከሺ በላይ ሞተዋል። ሁለት ሚሊዮን ተፈናቅለዋል። ዓለም በዚህ ሳቢያ ፊት የነሳቸው … ብሎ የተለመደውን ቅጥፈት ለማስደገፍ ተላላኪያቸው ትህነግ የፈጠረውን የትግራይን ቀውስ አክሎ ዜናውን አስውቦታል።

አህራም “ሾልኮ ወጣ” የተባለው መረጃ ሃሰት መሆኑንን አስታውቆ ” ግን” እንዲህ ብለዋል እያለ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ስም እያጠለሸ ዘገባውን ጨርሷል። የአገራችን ሰዎች ባንዳነት እዚህ ደርሷል። በሃሰት መረጃ አገር ማተራመሱ የሚቀጥል ነው፤ “ህዝብ ሆይ ሃሰት እየሸመትክ አገርህን አታሸብር”

ጋዲሳ ቦኩ ፊንፊኔ

ዝግጅት ክፍሉ – ጽሁፉ የጸሃፊውን አመለካከት ብቻ የሚወክል ሲሆን የተለየ ሃሳብ ላላችሁ መድረኩ ክፍት ነው


Exit mobile version