ETHIO12.COM

አሸባሪው ሕወሓት በመሸገበት ሁለት ቦታዎች በቅርቡ ታሪክ እንደሚደረግ ተገለጸ

ሰሞኑንን ጊታቸው ረዳና ሽንፈታቸውን ሙሉ በሙሉ ያመነው የቀድሞ ጻዳቃ ገብረትንሳኤ ስለወቅታዊ ቁመናቸው መግለጫ ቢሰጡም መንግስት አሸባሪው ቡድን በተሸሸገባቸው ሁለት ስፍራዎች መልሶ ማጥቃት በማድረግ ዘመቻውን እንደሚያጠናቅቅ አስታወቀ።

አሜሪካና አውሮፓዊያኑ ከሰባ ሰባትት ቀጥሎ ከአርባ ዓመት በሁዋላ በትግራይ ታይቶ የማይታወቅ ረሃብ እንደሚያሰጋ በመግለጽ ለትህነግ ሃይሎች መውጪያ ለማበጀት በሚተጋበት በአሁኑ ሰዓት፣ ተኩስ ማቆም ካልታወጀ በሚል ማስፈራሪያ በሚቀርብበት በዚህ ጊዜና የኤርትራና የአማራ ክልል ሃይሎች ይውጡ ተብሎ ቅጣት በተጀመረበት ወቅት መንግስት በሃላፊዊቹ አማካይነት ይህንን መናገሩ አነጋጋሪ ሆኗል።

በመግለጫው ወቅት ባይነሳም የጻድቃን ንግግርና ጥሪ ይህንኑ ፍርሃቻ ይመስላል። ጻድቃን ጦርነቱን ትህነግ እንደጀመረው አምኖ እንዳለው ከሆነ የመከላከያ ሰራዊት ዕረፍት አልባ ዱላ ማሰቢያ ጊዜና ዳግም ለመደራጀት ጊዜ እንዳልሰጣቸው፣ ባጭር ጊዜ ሚካናይዝድ የሚባለውን ሃይል እንዳመከነባቸው ሲያምኑ ማብራሪያቸው የጦር ጀነራል ሆነው የሰሩ አያስመስላቸውም ነበር።

“በድንገትና ባላሰብነው” እያለ ድንጋይ ካብ ተድግፎ ባስተላለፈው መልዕክት፣ በአራት አቅጣጫ የተከፈተባቸው ጥቃትና በድሮን የተከናወነው ድብደባ አንዴት ሊገርማቸው እንደቻለ ግን አልተተየቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ግን ” ጦርንርትን እንዳታስቡ፤ ካሰባችሁም በክላሽ ይሆናል ብላችሁ እንዳትገምቱ” በሚልደጋገመው ማስተንቀቃቸው ይታወሳል።

ጻድቃን እንዳለው ጦርነቱን ትህነግ መጀመሩ፣ የመጀመሪያው ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል ሲል ማስታወቁ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተናኛ ጥቃት፣ ጭፍጨፋና ዘረፋ ማካሄዳቸውን በኦፊሳል ያመነ ሁለተኛ ሰው አድርጎታል። ከስር የኢቢሲ ዜና እንዳለ ቀርቧል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ እና ወንጀል ምርመራ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመግለጫው አሸባሪው ሕወሓት ባለፉት ሶስት ዓመታት ሀገራዊ ለውጡን ለማደናቀፍ ሲሰራ መቆየቱ ሳይበቃው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ለማስታወስ ተነስቷል።

በአሸባሪው ቡድን ላይ ስለተወሰደው የሕግ ማስከበር እርምጃ እና ያንን ተከትሎ በክልሉ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ማብራሪያ የሰጡት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም በዚሁ ወቅት መንግስት በትግራይ ክልል ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ አቅም በፈቀደ እገዛ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሸባሪው ቡድን ክልሉን መልሶ ከመገንባት ይልቅ አገር በመበተን እንዲሁም የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትርና የመንግስትን ስም በማጠልሸት ውጤት አልባ ስራ ተጠምዷል ብለዋል፡፡ በክልሉ በሚካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሽብር ቡድኑ በስፋት በሚንቀሳቀስባቸው ሁለት ቦታዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻው በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ መንግስት ከዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለዜጎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን እያቀረበ ባለበት ወቅት ከአንዳንድ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አባላት መንግስት ርሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እንደሚጠቀም ተደርጎ የሚሰነዘረው ክስ መሰረተ ቢስ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በመጪው የመኸር ወቅት የክልሉ አርሶ አደሮች የግብርና ስራቸውን ሳያስተጓሉ እንዲቀጥሉ የማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦት ስራ መከናወኑንም ኃላፊዋ አንስተዋል፡፡የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌዲዮን ቲሞቲዮስ በበኩላቸው አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ባለፉት ሶስት ዓመታት አገራዊ ለውጡን ለማደናቀፍና ለመቀልበስ የሰራቸውን ወንጀሎች በመዳሰስ አሁን ላይ የሽብር ቡድን ተብሎ እስከ ተሰየመበት ድረስ ያለውን የመጀመሪያ ዙር የወንጀል ምርመራ ውጤት አብራርተዋል፡፡

በክልሉ በሽብር ቡድኑ በተፈፀሙ የጅምላ ግድያዎች እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በህዝብ እና መንግስት ንብረት ላይ በደረሰው ውድመት ዙሪያ የሚካሄደውን የወንጀል ምርመራ እየጠቀሱ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡በክልሉ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ሲካሄድ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ በማያስፈልግበት ሁኔታ ንፁሃን ዜጎች ገድለዋል በሚል የተጠረጠሩ 28 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተይዘው ጉዳያቸው በወታደራዊ ፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን ዶ/ር ጌዲዮን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በጾታዊ ጥቃትና አስገድዶ መድፈር የተጠረጠሩ 25 የሰራዊቱ አባላት በሕግ ጥላ ስር ሆነው የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡በክልሉ ትምህርትን ለማስጀመር እንዲሁም የስደተኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ እየተከናወኑ ባሉ እና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎች ዙሪያም ማብራሪያ ተሰጥቷል።


Exit mobile version